ከእርምጃዉ ጀርባ ያለዉ ምክንያት ምንም-ሆነ ምን ዉሳኔዉ በአካባቢዉ ለሚኖረዉ ሕዝብ ጥቅም ሲባል ይለወጣል የሚል ተስፋ ነዉ-ያለን።አሁን ባለንበት ደረጃ እርምጃዉ በርዳታ ፈላጊዎች ላይ ሥለሚያደርሰዉ ተፅዕኖ ለመናገር ገና ነዉ።ትናንት ነዉ የተፈፀመዉ
29 11 11
የሶማሊያ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አ-ሸባብ ደቡባዊ ሶማሊያ የሚሠሩ የርዳታ ድርጅቶችን ማገዱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አወገዘ።የአ-ሸባብ ታጣቂዎች ትናንት ደቡባዊ ሶማሊያ ዉስጥ ይሰሩ የነበሩ የተባበሩት መንግሥታትና የተለያዩ የርዳታ ድርጅቶች ንብረትን ዘርፈዋል፥ ቢሯቸዉንም ሰበብረዋል።እርምጃዉን ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙንን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፉ ድርጅት ባለሥልጣናት አዉግዘዉታል።የድርጅቶቹ መታገድና መዘረፍ ለረሐብ ለተጋለጠዉ የሶማሊያ ሕዝብ የሚሠጠዉን እርዳታ ያስተጓጉለዋል የሚል ሥጋት አሳድሯል።ነጋሽ መሐመድ ናይሮቢ የሚገኘዉን የተባበሩት መንግሥታት የሠብአዊ ርዳታ ማስተባባሪያ ፅሕፈት ቤት ባልደረባን አነጋግሮ ያጠናቀረዉ ዘገባ አለ።ናይሮቢ ሆነዉ-ለሶማሊያ ሕዝብ የሚላከዉን ርዳታ የሚመሩና የሚያስተባብሩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሥልጣናት እንደሚሉት ከትናንት በፊት ለድርጅታቸዉ የደረሰ ማስጠንቀቂያ-ማሳሰቢያ ማስታወሺያም የለም።ትናንት ሁሉም ሆነ። Continue reading





