Daily Archives: December 12, 2011

የኢህአዴግ መንግስት መለያ ባህሪያት:- ከአቶ አስገደ ገብረስላሴ (የህወሓት መስራች የነበሩ ከመቀሌ)

የነበሩ ከመቀሌ)

1. ህግ የማያከብር መንግስት

የኢህአዴግ መንግስት የፍትህ የዳኝነትና የፖሊስ አካላት እንዲቋቋሙ አድርጓል፡፡ እነዚህ የፍትህ አካላት አንዳንድ የሚወስዱትን ህገ-ወጥ እርምጃ ሳይ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሳይሆን የኢህአዴግን መንግስት ለሚቃወሙ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች በአጠቃላይ የተለየ ሐሳብ የሚያራምዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመጫን የተመሰረቱ ይመስሉኛል፡፡ በማንኛውም ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ ፖሊስ መጀመርያ ግለሰቡን ..ከኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች.. አንዱ መሆኑን እና አለመሆኑን ከኢህአዴግ ባለስልጣናት ይሁንታ ካላገኘ የማሰር አቅም አይኖረውም፡፡ የፍትህ አካላትም ክስ የሚመሰረቱበትን የግለሰቡን ማንነት አስቀድመው ከኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች ውጭ መሆኑን ማረጋገጥ የግድ ይላቸዋል፡፡ ዳኞችም እንግዲህ በአንፃሩ ከኢህአዴግ መንግስት በአመለካከት ያልተለዩ ከሆኑ ወንጀል ቢፈፅምም ተጠርጣሪ ጠያቂ አለበት ማለት ይከብዳል፡፡ የፖለቲካ ታማኝነቱ ሳይታወቅ የተከሰሰ ..አባል.. እንኳ በችሎት ላይ እያለም ክሱ እንዲሰረዝለት የሚደረግበት አጋጣሚ አለ፡፡  የኢህአዴግ መንግስት ሁሉም ዜጋ በህግ ፊት እኩል ነው እያለ ሲፅፍና ሲናገር እንሰማለን፡፡ ኢህአዴግ ይህንን ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በአመለካከት ከኔ እስካልተለያየህ ድረስ ማለቱ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በአስተሳሰብ የተለየ እስካልሆንክ ሰው ብትገድል እንኳ በእርቅ ነፃ መውጣት ትችላለህ፡፡ ስልጣንህን ተገን በማድረግ የህዝብ ንብረትና ገንዘብ ብትዘርፍ ዘመነኛ ተብለህ ልትሸለማለህ ትችል እንደሆነ እንጂ ሙሰኛ አያሰኝህም፡፡ Read the rest of this entry

%d bloggers like this: