የ2011 20ዎቹ የኢትዮጵያ ሃብታሞችን ተዋወቁ
Friday, December 23, 2011 12:15 PM.
ኢትዮጵያን ሪቪው የተሰኘው ታዋቂ ድረ ገጽ በመረጃ መረቡ ላይ የጥናት ቡድኑን በመጥቀስ ሃያዎቹን የ2011 የኢትዮጵያ ከበርቴዎች ይኖራቸዋል ብሎ ከገመተው ገንዘብ ጋር አብሮ ይፋ አደረጋቸው። ከሃያዎቹ ከበርቴ ዎች መካከል አብዛኞቹ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ባለስልጣ ናት መሆናቸው ዘገባውን አጋልጧል። የከበርቴዎቹን ዝ ርዝር ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች በሚመች መልኩ አቅርበ ናል ይከታተሉት። 1ኛ. ሼህ መሃመድ አላሙዲ፦የሜድሮክ ኢትዮጵያ ባለቤት የሆኑት እኚህ ከበርቴ አስር ቢሊዮን ዶላር፤ 2ኛ. አቶ መለስ ዜናዊ፦ 3 ቢሊዮን፤ 3ኛ. “የሙሰኞች እናት” የሚል ቅጽል ስም የወጣላት የአቶ መለስ ባልቤት ሃዜብ መስፍን በትግራይ ሕዝብ ስም ከተቋቋመው ኤፈርትና ሌሎች ድርጅቶች በዘረፈ ችው ገንዘብ ሶስት ቢሊዮን ዶላር፤ 4ኛ. የቀድሞው የህወሃት መሪና አሁን ወጋገን ባንክን እየመሩ የሚገኙትና ቦስተን (አሜሪካ) ሳይቀር ቪላ ቤት ያላቸው አቶ ስብሃት ነጋ 2.5 ቢሊዮን ዶላር፤ 5ኛ. ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ፦ ከትዳሩ ጋር ሲፋታ በፍርድ ቤት አራት ቢሊዮን ዶላር ለባለቤቱ የከፈለው የቀድሞው በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃነ፤ የህወሃት የማ ዕከላዊ ኮሚቴና ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሆኖ እየሰራ ነው።2 ቢሊዮን ዶላር፤ 6ኛ. ሳሙኤል ታፈሰ፦ በኦሮሚያ ክልል ከመንገድ ግንባታ ጋር በተያያዘ በከፍ ተኛ ሙስና ውስጥ ተዘፍቆ ሆኖም ግን ከሃዜብ መስፍን ጋር የንግድ ሸርክና ስላለው በኢትዮጵያ ምድር ላይ ይቀ ልዳል የሚባለው የሰንሻይን ኮንስትራክሽን ባለቤት ሳሙ ኤል 1.5 ቢሊዮን ዶላር፤ 7ኛ. ስዩም መስፍን፦ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚ/ርና በአሁኑ ወቅት በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ ስዩም መስፍንን ኢትዮጵያን ሪቪው ድረ ገጽ ከማሪዋና እና ከሌሎች የተከለከሉ አደንዛዥ እጽ ዝውውሮች ጋር በተያያዘ ንኪኪ እንዳላቸው አጋልጧል። እንደ ድረ ገጹ ዘገባ ስዩም ሃብታቸው 1 ቢሊዮን ዶላር፤ 8ኛ. ኡመር አሊ ሽፋው፦ የነጃት ኢንተርናሽናል ባለቤት ናቸው። አሁን የሕወሓቱ የቡናውን ኤክስፖርት ንግድ ቢቆጣጠርባቸውም ያላቸው ሃብት 800 ሚሊዮን ዶላር፤ 9ኛ. አቡነ ጳውሎስ፦ ከተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ጋር ሽርክና እንዳላቸው የተጋለጠው እኚሁ ሊቀ ጳጳስ 600 ሚሊዮን ዶላር፤ 10ኛ. አባዲ ዘሙ፦ በትግራይ ሕዝብ ስም የሚነገድበትን ኢፈርት የተባለውን ድርጅት ይመራ የነበረው አባዲ ዘሙ ስልጣኑን በሃዜብ መስፍን ተቀምቶ ወደ ሱዳን ተገፍቶ በካርቱም የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆኖ ይሰራል። ሃብቱ 500 ሚሊዮን ዶላር፤ 11ኛ. እዮብ ማሞ፦ በዋሽንግተን ዲሲ ከ250 በላይ ጋዝ ማደያዎች ያሉት የካፒቶል ፔትሮሊየም ግሩፕ ባለቤት እዮብ ሃብት 500 ሚሊዮን ዶላር፤ 12ኛ. ከተማ ከበደ፦ ኬኬ ትሪዲንግና አልሳማ ሪል ኢስቴት በአ. አ.ን የሚመራው ይኸው ሃብታም 400 ሚሊዮን ዶላር፤ 13ኛ. ምንውዬለት አጥናፉ፦ የሕወሓት ቢዝነስ ኢምፓየሮችን በአንድ ወቅት ድርቅ ውስጥ ከቷቸው የነበሩትን ስታር ቢዝነስ ግሩፕ፣ ጣና ትራንስፖርት፣ መና ትሬዲንግና ኢትዮ ኢንቨስትመንት ግሩፕን ከሚያስተዳድሩት ባለቤቶች መካከል ባለብዙው ባለ አክሲዮን ምንውዬለት አጥናፉ 400 ሚሊዮን ዶላር፤ 14ኛ. ግርማ ብሩ፦ የቀድሞው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚ/ር አሁን በዋሽንግተን ዲሲ የመለስ ዜናዊ አምባሳደር ሆነው እየሰሩ የሚኙት አቶ ግርማ ብሩ በአክሲዮን የተለያዩ የንግድ ድርጅቶችን ይመራሉ። በከፍተኛ ሙስና ከሚጠረጠሩበት የደንበል ሲቲ ሴንተር ህንጻ ጀምሮ። አቶ ግርማ 300 ሚሊዮን ዶላር፤ 15ኛ. ታደሰ ሃይሌ፦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚ/ር ደኤታ በመሆን የሚሰራው ሕወሓቱ ታደሰ ሃይሌ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ገንዘቦቹን ያፈሰሰ ሲሆን፤ የኮንስትራክሽን እና የንግድ ካምፓኒዎች አሉት። ይህ ባለስልጣን 250 ሚሊዮን ዶላር፤ 16ኛ. ቴዎድሮስ ሃጎስ፦ በተለያዩ የሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ውስጥ በብዙ ገንዘብ አክሲዮን ያለው የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ አቶ ቴዎድሮስ ሃጎስ 200 ሚሊዮን ዶላር፤ 17ኛ. አብዱእላህ ባገርሽ፦ የሕወሓቱ ጉና በቡና ንግድ ላይ ከተሰማራ በኋላ እየተንገዳገዱ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች መካከል አንዱ ናቸው። ታዋቂ የቡና ላኪ ሲሆኑ ያላቸው ሃብት 150 ሚሊዮን ዶላር፤ አብዱእላህ ባገርሽ፦ የሕወሓቱ ጉና በቡና ንግድ ላይ ከተሰማራ በኋላ እየተንገዳገዱ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች መካከል አንዱ ናቸው። ታዋቂ የቡና ላኪ ሲሆኑ ያላቸው ሃብት 150 ሚሊዮን ዶላር፤ 18ኛ. ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፦ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚ/ር ሆኖ የሚሰራው ይህ ባለስልጣን ነጻ ሬድዮኖችን፣ ቴሌቭዥኖችንና ዌብ ሳይቶችን ጃም በማስደረግ ሥራ የመለስ አስተዳደርን እየረዳ የሚገኝ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ነጋዴ ነው። ደብረጽዮን 100 ሚሊዮን ዶላር። 19ኛ. በረከት ስሞዖን፦ የመለስ አስተዳደር የፕሮፓጋንዳ ዋና አለቃ ናቸው። በሪል ስቴት ስራ ተሰማርተው ብዙ ንብረት አፍርተዋል። አቶ በረከት 100 ሚሊዮን ዶላር፤ 20ኛ፦ የምሩ ነጋ፦ የደምበል ሲቲ ሴንተር ባለቤት ናቸው። ከሃዜብ መስፍን፣ ግርማ ብሩና ታደሰ ሃይሌ ጋር የንግድ ሽርክና አላቸው። እሳቸውም ልክ እንደሌሎቹ 100 የሚገመት ዶላር አላቸው ተብሎ ይገመታል።S
Posted on December 23, 2011, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a Comment.
![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)
Leave a Comment
Comments (0)