በአቢ ገብረሃና/ኖርወይ/
ከሰሞኑ የአፍሪካ ህብረት ባደረገው ሰብሰባ ከያዛቸው የመወያያ አጀንዳዎች አንዱ በአፍሪካ አህጉር የሰብአዊ መብት ረገጣ ለተደረገባቸው መታወሻ የሚሆን ኢንስቲቲዩት ማቋቋም መሆኑን ስሰማ በጣም ነበር የገረመኝ:: ይባስ ብለው የፕሮጀክቱ የበላይ ጠባቂ ሆነው የተሾሙት ፕሮፊሰር አንድሪያስ እሽቴ አላማውን ሲዘረዝሩ “…መታሰቢያነቱ በአፍሪቃ መንግስታት በእኛው በኢሰብአዊ አያያዝ የተረገጡትን ማስታወሻ ነው” ካሉ በሗላ የአፓርታይድንንና የደርግን የቀይ ሽብር ሰለባዎች ለአብነት ጠቃቅሰው ራሳቸውም የታሪኩ ተቁዋዳሽ የሆኑበትን የትናንቱን የጋምቢላ ፥የጂማ ፥የአዲሳ አበባ የበደኖውን ኦጋዲኑ፥ እረ ስንቱ… የወያኔ ኢሰብአዊ የመብት ረገጣ ውሃ ሲቸለሱበት ሳስተውል “ተምሮ መና! አለ ያገሬ ሰው አሁን ኢኚህ ሰው ፐሬዚዳንት በነበሩብት ትምሀርት ቤት ነበር የተማርኩት” ስል ራሴንም ሳልታዘበው አልቀረሁም ።
በዚህ ሁኔታ ስብሰለሰል ሳለ በትናንትናው እለት አንድ ወዳጀ “በእግር በፈረስ ሳፈላልግህ ነበር…” አለኝ ፊቱ በድነጋጤ ቡን እነዳለ ነበር “የወያኔንና የኖርወይን ጉድ ስማህ? ሲል ጠየቀኝ ፧ “ጆሮ አይሰማው የለ፡ እረ አልሰማሁም፤ ምን ተፈጠረ ደሞ?” ብየ መጠየቅ
“እረ ጉድ ነው! የኛው ሆዳም ጥቂት ጉርሻ ኖርዊጅያኖች ጣሉለት መሰል… ሰደተኞችን እንደፊስታል አንጥልጥላችሁ መልሱልኝ ኢትዮጵያዊ እንደዚህ መጠጊያ ይጣ? አለኝ::” ትክዝ እንዳለ ። “ይህ ነገር የተለመደው የወያኔዎች የማወናበድ ወሬ እንዳይሆን” ስል ወሬውን ላጣጥልበት በሞክርም ከነማስረጃው ይሕው አለኝ:: እኔም ይህንኑ የወያኔዎች ባህር ተሻጋሪ ተቅበዝባዥነት ላወጋችሁ ወደድኩ።
በአሁን ሰአት በሃገር ውስጥ ያለውን የሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰት የኢኮኖሚ ጭቆናና አፈና በመሽሽ ባገኙት ቀዳዳ በመጠቀም ከሃገር ወጥተው ከጎረበት ሃገራት እስከባህር ማዶ በመሰደድ አስከፊውን የስደት ህይወት እየገፉ የሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከእለት ወደ እለት እየጨመረ ይገኛል::
የኖርወይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሴክሪታር ቱርጌይር ላርሰን እና ከኢትዮጵያ በኩል ደግሞ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ጋር ስምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት ፎቶ በኖርወይ ፍትህና ኢመርጀንሲ ዲፓርትመንት
ታሪካዊ እውነታ
ኣጠቃላይ የኖርወይ የህዝብ ብዛት ወደ 4.99 ሚሊዮን ገደማ ይደርሳል:: ኖርወይ በአለም ላይ የሰብአዊ መብትን በማስከበር በግንባር ቀደምነት ከሚጠቀሱት ሃገሮች አንዷ ብትሆንም ቅሉ ግን በተግባር እየተደረገ ያለው ሃቅ የተገላቢጦሽ ነው:: Continue reading →
Like this:
Be the first to like this post.