የክበበው ገዳ እና የመስከረም በቀለ የኮሜዲ ትርዒት በሚኒሶታ
February 14, 2012
(ዘ-ሐበሻ)፦ ተወዳጆቹ ኮሜዲያኖች ክበበው ገዳ እና መስከረም በቀለ በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ስቴቶች እየተዟሩ የሚያሳዩትን የኮሜዲ ትሪዒት በመቀጠል በሚኒሶታ የፊታችን እሁድ ፌብርዋሪ 19/2012 እንደሚያቀርቡ ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ የደረሰው መረጃ አመለከተ:: በሶል ዲዛይን እና በምነውሸዋ ኢንተርቴይመንት አማካኝነት የተዘጋጀው ይኸው የኮሜዲ ዝግጅት 275 N Lexington PKwy St. Paul MN 55104 ላይ በሚገኘው ሴንትራል ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ ውስጥ ሲደረግ የመግቢያ ዋጋውም 30$ እንደሚሆን አዘጋጆቹ ገልጸዋል። ክበበው ገዳ በኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት አማካኝነት ሰርቶት የነበረውና በሕዝብ ዘንድ “ምነው ክበበው ቀልድ አለቀበት እንዴ?” ተብሎ የተወቀሰበት ሥራ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ወጥቶ የነበረ ሲሆን ተወዳጁ ክሜዲያን ከ8 ዓመት በፊት የተሰራ የኮሜዲ ስራው እንደ አዲስ ስራ መውጣቱን ገልጾ ሕዝቡ በእኔ ላይ ያለውን እምነት የሚሸረሽር ስለሆነ ሕዝቡን ይቅርታ እጠይቃለሁ ማለቱ ይታወሳል። ኦክቶበር 4 ቀን 2004 በአዲስ አበባ በሃርመኒ ሆቴል በሀበአብ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት አማካይነት ለጋዜጠኞች ሰጥቶት በነበረው መግለጫ ከ8 ዓመት በፊት በ45 ሺህ ብር የሸጥኩት ለዚያን ጊዜ የሚሆን ኮሜዲ ያኔ መውጣት ሲገባው አሁን መውጣቱ በአዲሱ ስራዬ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል ያለው ኮሜዲያኑ፣ አዲሱ ስራም በዚሁ ምክንያት አልወጣም ኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት እኔን ሳያማክር በ1995 ዓ.ም. የገዛውን ስራዬን ለመሸጥ ሲነሳና አዲሱን ስራዬን ለመጠቀም ሲወስን በተመልካቹ ዘንድ ከሚፈጥረው ስሜትና ትርጉም አንጻር ሊጠነቀቅና እኔንም ሊያማክር፣ ቢያንስ ሊያሳውቀኝ ይገባ ነበር ብሏል፡፡ “ኤሌክትራ ቢያማክረኝ በአሮጌው ምትክ አሁን የስራዬን እድገት የሚገልጽ አዲስ ስራ እሰጠው ነበር” ሲል መናገሩ ይታወሳል፡፡ ክበበው ሴንት ፖል ሚኒሶታ ከመስከረም በቀለ ጋር በሚያሳየው በዚህ ትርዒት ላይም ሕዝቡን እንደሚክስ የገለጸ ሲሆን፤ ከአርቲስት መስከረም በቀለ ጋርም የሰሩትን አዲስ የኮሜዲ ድራማ ሚኒሶታ ላይ እንደሚያሳይ ገልጿል። የሚኒሶታ ወገኖቻችን እሁድ ፌብሩዋሪ 19 ደርሶ ሁለቱን “ጋላክቲኮ” ኮሜዲያን እስከምታዩዋቸው ድረስ ከሁለቱም አስቂኝ ሥራዎች መካከል አንድ አንዱን በቪዲዮ ቀጥሎ በዘ-ሐበሻ ስም እንጋብዛለን። ከክበበው ተወዳጅ ቀልዶች መካከል “አማረኝ”
ከመስከረም በቀለ ተወዳጅ ቀልዶች መካከል “የአሜሪካ ደብዳቤ”
Posted on February 14, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a Comment.
![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)
Leave a Comment
Comments (0)