Daily Archives: February 27, 2012
ሕይወታቸው እያለፈ ያሉት ዜጎች በሕጋዊ መንገድ የሚጓዙት ጭምር መሆናቸውን ማኅበሩ አስታወቀ
Februar 27/2/2012
መጓዝ የሚቻለው ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኩዌትና ዱባይ ብቻ ነው
ከኢትዮጵያ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ሥራ ፍለጋ የሚጓዙና ሕይወታቸው እያለፈ የሚገኙት ዜጎች፣ በሕገወጥ መንገድ የሚጓዙት ብቻ ሳይሆኑ በሕጋዊ መንገድ በተለያዩ አየር መንገዶች የሚጓጓዙት ጭምር መሆኑን፣ የኢትዮጵያ የውጭ ሥራ ስምሪት አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲዎች አሰማሪ ማኅበር ሥራ አመራር ቦርድ አስታወቀ፡፡
የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መዝገቡ አሰፋ የካቲት 14 ቀን 2004 ዓ.ም. እንደገለጹት፣ በአሁኑ ጊዜ ለማንኛውም ተጓዥ በተለያዩ አየር መንገዶች የአንድ ወር ቪዛ ይዘጋጅላቸዋል፡፡ ሕጋዊ ስለሆኑ በአየር መንገድ ተሳፍረው ወደ ሱዳን፣ ጂቡቲና ወደተለያዩ አገሮች ይጓዛሉ፡፡ ከአገራቸው በሕጋዊ መንገድ የወጡ ዜጎች መዳረሻ አገር ሲደርሱ ቅብብሎሹ ውስጥ ገብቶ የሚቀበላቸው አካል ሕገወጥ ነው፡፡ Read the rest of this entry
የየመኑ አብደላ ሳላህ ወደ አዲስ አበባ ሸሽተዋል ተባለ
February 27, 2012
Ethiopia Zare(ቅዳሜ የካቲት 17 ቀን 2004 ዓ.ም. February 25, 2012)፦ በህዝባዊ የተቃውሞ ማእበል ከስልጣናቸው የተወገዱት የየመኑ ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳላህ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የገቡ ሲሆን ወደ የመን ተመልሰው እንደማይሄዱም እየተገለጸ ነው። Read the rest of this entry
‹‹ኢሕአዴግን ለማሸነፍ የግማሽ ዓመት እንቅስቃሴ ብቻ በቂ ነው››
February 27, 2012

አቶ ገብሩ አስራት፣ የዓረና ትግራይ ሊቀመንበርና የመድረክ አመራር አባል
በአሁኑ ጊዜ ኢሕአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ከሚያወዛግቡ ጉዳዮች አንዱ የፖለቲካ ምኅዳር መጥበብ ነው፡፡
ምርጫ 97ን ተከትሎ ኢሕአዴግ ‹‹አንድ ለአምስት›› በሚል በአርሶ አደሩ የኅብረተሰብ ክፍል የዘረጋው ኔትወርክ የግለሰቦችን ነፃነት የሚጥስ መሆኑን ተቃዋሚዎች ይገልጻሉ፡፡ ገዥው ፓርቲ የመንግሥትን ተቋምና ንብረት በመጠቀም የፖለቲካ ሥራ መሥራቱም የውድድር ሜዳውን ሚዛናዊ እንዳይሆን አድርጐታል ይላሉ፡፡ ኢሕአዴግ በበኩሉ ኅብረተሰቡን በፈቃደኝነት በተመሠረተ መንገድ በቡድን በማደራጀት የልማት ተሳታፊ እንዲሆን ማድረጉ በሕዝብ ደረጃ ተቀባይነት እያስገኘለት እንደመጣ ይናገራል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ባለው ተጨባጭ የፖለቲካ ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ኃይሌ ሙሉ የቀድሞውን የሕወሓት/ኢሕአዴግ ታጋይና የአመራር አባል፣ የአሁኑን የዓረና ትግራይ ሊቀመንበርና የመድረክ አመራር አባል የሆኑትን አቶ ገብሩ አስራትን አነጋግሯቸዋል፡፡ Read the rest of this entry
የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት “እኔ ከተከሰስኩ ወ/ሮ አዜብ መስፍንም መከሰስ አለባቸው” አሉ (በመምህሩ መልካሙ)
February 27, 2012
የአፍራሽ ግብረ ኃይል ሰለባዎች
February 27, 2012

የቦሌ ክፍለ ከተማ ሰሞኑን ሕገወጥ ግንባታ በሚል ምክንያት ከነባር ግንባታ ጋር ተዋህደው የተሠሩና የተቀጠሉ ግንባታዎችን ሲያፈርስ ሰንብቷል፡፡
የክፍለ ከተማው አፍራሽ ግብረ ኃይል ሰለባ ከሆኑት መካከል ከቦሌ መድኃኔዓለም ወደ ቦሌ ድልድይ በሚወስደው መንገድ በስተግራ በኩል ጎን ለጎን የሚገኙት ላ ፓሪዚያንና ቢግ ሾው ሬስቶራንት የተሰኙት የንግድ ቤቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ላ ፓሪዚያን አቢሲኒያ ሕንፃ ሥር ቀደም ሲል ስዊስ ካፌ የነበረበትን የተከራየ ሲሆን፣ ቤቱን አስውቦ ሥራ ከጀመረ ሦስት ወር አይሞላውም፡፡ ቤቱን ለማስዋብ ሦስት ወራት ፈጅቶበታል፡፡
ሌላኛው የአፍራሽ ግብረ ኃይሉ ሰለባ ከላ ፓሪዚያን አጠገብ የሚገኘው ቢግ ሾው ሬስቶራንት ነው፡፡ ይህ ሬስቶራንት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ሁለት ጊዜ ነው እንዲፈርስ የተደረገው፡፡ ባለፈው ረቡዕ በፖሊስ የታጀበው የክፍለ ከተማው አፍራሽ ግብረ ኃይል በመቶ ሺሕ ብር የሚቆጠር ገንዘብ የወጣባቸውን ግንባታዎች በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ወደ ፍርስራሽ ለውጠዋቸዋል፡፡ Read the rest of this entry
![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)




![934090_653692987990685_304344173_n[1] 934090_653692987990685_304344173_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8419/8907424400_e66413b735_m.jpg)
![969200_505600652838946_443296293_n[1] 969200_505600652838946_443296293_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8263/8906754167_0a2bacfe7d_m.jpg)