Daily Archives: March 1, 2012

በሕዝባዊ ንቅናቄ ሠላማዊ ትግል ያሸንፋል! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

March 1, 2012

በአገራችን  ኢትዮጵያ ኢህአዴግ  በሥልጣን ላይ በቆየባቸው ባለፉት ሃያ አመታት ውስጥ የተፈፀሙ ኢ-ሠብአዊ፣ ኢ-ዴሞክራሲያዊና ኢ-ፍትሓዊ ድርጊቶችን ስንቃወምና ስናጋልጥ ቆይተናል፡፡ ገዢው ፓርቲ ግን አንድም ጊዜ ስህተቱን ሲቀበልና  ሲያርም አልተስተዋለም፡፡ ይልቁንም የተለያዩ አሳሪና አስፈሪ አዋጆችን፣ መመሪያዎችን፣ ድንጋጌዎችን እያወጣና ለሕገ-መንግሥቱ እንኳ ሳይገዛ  ባደባባይ በተደጋጋሚ በማን አህሎኝነት  ከሕግ በላይ እየሆነ  ነው፡፡ ህዝብ በኑሮ ውድነት፣ በመልካም አስተዳደር እጦት፣ በሕግ የበላይነት አለመኖር፣ በሙስና መንሠራፋት፣ በዴሞክራሲያዊ መብቶች አለመከበር ወዘተ በሚደርስበት በደል  በየእለቱ ይጮሃል፡፡ Read the rest of this entry

የጠቅላይ ሚኒስትሩን አማካሪዎች በጨረፍታ ፪

March 1, 2012

ተመስገን ደሳለኝ

ይህ ርዕሰ ጉዳይ የተነሳው የዛሬ 15 ቀን ነበር፡፡ እናም ሳይደመደም በይደር ተላለፈ፡ ፡ ይደሩ በተቀጠረበት እለት የታተመው ደግሞ የህወሓትን 37ኛ የልደት በአል በማስመልከት የተዘጋጀ ልዩ እትም በመሆኑ ርዕሰ ጉዳዩ ተዘለለ። ሆኖም ተዘሎ አልቀረም ይኸው የዚህ እትም አጀንዳችን ሆነ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩን አማካሪዎች በጨረፍታ… ወደ አጀንዳችን ከመግባታችን በፊት አንድ አስደንጋጭ ወሬ የሳምንቱ ሰደድ እሳት በመሆኑ እሱን እናስቀድም። Read the rest of this entry

%d bloggers like this: