Daily Archives: March 12, 2012
የኢትዮጵያውያን ችግር በውጭ ሀገር
ከሦስት መቶ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያንና ደጋፊዎቻቸው ዛሬ በመዲናይቱ ኦስሎ አደባባይ ወጡ። ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር የኖርዌይ መንግሥት በሀገሩ የሚገኙ ኢትዮጵውያን ተገን ጠያቂዎችን በቅርቡ በግዳጅ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ለመመለስ የሚያስችለው አንድ ስምምነት ከሁለት ወራት በፊት
የኖርዌይ ጠቅላይ ሚንስትር የንስ ስቶልትንበርግ Read the rest of this entry
Ethiopia: Human rights work crippled by restrictive law
A law in Ethiopia is crippling human rights work in the country, forcing organizations to cut programmes, close offices and lay off staff, according to an Amnesty International report published today.
“Stifling human rights work: the impact of Ethiopia’s civil society legislation” describes how the 2009 Charities and Societies Proclamation puts in place restrictions on organizations working on human rights and allows for excessive government interference. The result is that people in the country have less access to independent human rights assistance. Read the rest of this entry
የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ጉዳይ ተገቢ መፍትሔ እስከሚያገኝ ድረስ ንቁ ክትትልና ያልተቋረጠ ትግል ያስፈልጋል! ኢሮብ-ማብሎ
የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ጉዳይ ተገቢ መፍትሔ እስከሚያገኝ ድረስ ንቁ ክትትልና ያልተቋረጠ ትግል ያስፈልጋል! click here maledatimes PDF
የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ጉዳይ ተገቢ መፍትሔ እስከሚያገኝ ድረስ ንቁ ክትትልና
www.ethioandinet.wordpress.com
ያልተቋረጠ ትግል ያስፈልጋል! ኢሮብ-ማብሎ የካቲት 2004 ኢትዮጵያዊያን የኣልጀርስ ስምምነትንና የሄግ ውሳኔን በሚገባ መረዳትና የኢትዮጵያና የኤርትራ የዳር ድንበር ጉዳይ ነቅቶ መከታተል ይገባቸዋል። የድንበሩ ግጭትና መፍትሔውን በሚመለከት በርካታ ኢትዮጵያዊያን፣ የሕግ ተመራማሪዎችና ሌሎች ምሁራን፣ በወቅቱ ሰፋፊ ሕጋዊና ታሪካዊ ጥናቶችን ማቅረባቸው ይታወሳል። የኢሮብ ተወላጆችም በግልና በቡድን የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛቶችንና የህዝባቸውን ሰብአዊና ዜግነታዊ መብቶችን ለማስከበር ሲሉ ታሪካዊና ወቅታዊ መረጃዎችን በማጣቀስ ሁናቴው በኢትዮዽያዊያንና በዓለም-አቀፍ ማህበረ-ሰብ በግልጽ እንዲታወቅ ይረዳ ዘንድ በስፋት ጽፈዋል፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወራሪው የሻዕቢያ ሠራዊት በህዝብ ላይ የፈጸመውን አስከፊ ግፎች በዓለምአቀፉ ማህበረ-ሰብ ግንዛቤ እንዲያገኙ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ደግሞ የኢሮብ መብት ተሟጋች ማህበር (ኢ.መ.ተ.ማ) በሻዕቢያ ሠራዊት ተጠልፈው ተወስደው ጠያቂ መንግሥት በማጣት እስከዛሬ ድረስ መዳረሻቸው ያልታወቀ ከ100 በላይ ዜጎችና በአልጀርስ ስምምነት መሠረት የተወሰነውና የሄግ ብይን ተብሎ የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግሥት ያለ-ቅድመሁኔታ በተቀበለው መሠረት ድንበሩን ለማካለል ከሻዕቢያ ጋር ለመነጋገር ተደጋጋሚ ጥሪ ስለሚያቀርብባቸው የኢሮብ ህዝብ የሚኖርባቸውና ሌሎች ሰፋፊ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛቶችን በተመለከተ የፍትሕ-ያለህ ማለትን አላቋረጠም፣ ፍትሓዊ እልባት እስኪገኝ ድረስም ትግሉን አያቋርጥም። Read the rest of this entry
ለመሞት ዝግጁ ነኝ — አቶ አንዱዋለም ከቃሊት የላኩት ደብዳቤ
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አቶ አንዱዋለም አራጌ ከቃሊት እሥር ቤት፣ ለፍትህና ለሪፖተር ጋዜጣ አዘጋጆች በላኩት ደብዳቤ፣ በወህኒ ቤት የደረሰባቸዉ የግድያ ሙከራ በስፋት ያተቱ ሲሆን ፣ በወህኒ ቤቱ ለደረሰባቸው የግዳያ ሙከራ የወህኒ ቤቱ አስተዳደሮች እጅ እንዳለበት የተለያዩ መረጃዎችን በማቅረብ ለማሳየት ሞክረዋል።
ደብዳቤዉን የጻፉት በማንም ላይ ጥላቻ ወይንም በቀል ኖሯቸው ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እየደረሰባቸው ያለዉን እዉነት እንዲያውቅ እንደሆነ የገለጹት አቶ አንዱዋለም «ግራና ቀኛቸዉን ለይተዉ ከማያወቁ ልጆቼ ተለይቼ ዘመኔን በሙሉ በወርደት ለመጨረስ ብቻ ሳይሆን ለመሞትም ዝግጁ መሆኔን አሳዳጆቼ እንዲያወቁት እወዳለሁ።» ሲሉ ያላቸዉ ቁርጠኝነት በግልጽ አስቀምተዋል። አቶ አንዱዋለም የጻፉትን ሙሉ ደብዳቤ ከዚህ በታችን አስፍረናል
www.ethioandinet.wordpress.com
ለተከበሩ የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ ለተከበሩ የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ
ወንድማዊ የአክብሮት ሰላምታዬ ይድረስዎ Read the rest of this entry


![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)