ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በ88 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ያስገባቸው ሕመም ጉንፋን ቢጤ ነውና ለክፉ አያጋልጣቸውም እየተባለ በመንግስት ሰዎች ሲነገር ቆይቷል:: በአሁን ሰአት የፕረዚዳንት ግርማ ሞት የወያኔን ባለስልጣናት እንዳሰደነገጣቸው ተገልጦአል። ከቀዳዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመን ጀመሮ ለስልጣን ሩጫ ሲዋትቱ የነብሩት ፕረዚዳንት ወልደ ጊዮርጊስ በውትድርና አገልግሎት ረዘም ላለጊዜ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በደርግ መንግስትም ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው ሰው ነበሩ። ከ11 ዓመት በፊት በፕሬዚዳንትነት ስልጣን እንደተመረጡ; በከፋ ሕመም ተጋልጠው ወደ ሳኡዲ ለህክምና ሄደው የነበሩት ፕሬዚዳንት ግርማ በተደጋጋሚ ላለፉት 11 ዓመታት ለበርካታ ጊዜያት የሆስፒታል ኢመርጀንሲ ክፍሎችን ጎብኝተዋል ባሳለፍነው ሳምንትም በነበሩበት ሆስፒታል በከፍተኛ የጥበቃ ሃይሎች እየታገዙ የህክምና አገልግሎት በመከታተል ቢያሳልፉም እርሳቸው ግን ከመሞት ወደሗላ ሊሉ አልቻሉም ። ፕረዚዳንት ግርማ በአስራአንድ አመታት ውስጥ በሃገሪቱ የሚላኩትን ልኡካን በማስተናገድ ስራ ተጠምደው እና የጋርዮሽ ስራ ፊርማዎችን ሲያጸድቁ፣ ሲፈርሙ፣ እንዲሁም ተፈርመው የተላኩትን ብቻ ሲቀበሉ የነበሩ የገዢውን ፓርቲ አገልጋይ እንደነበሩ ይታወሳል።
ዝርዝር ዘገባ ይዘን እንቀርባለን
Posted on March 13, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. 1 Comment.

![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)
በጣም ነው ያዘንኩት ………….
ጌታ ነፍሳቸውን በ ገነት እንዲያኖራቸው ጸሎቴ ነው