Daily Archives: March 18, 2012
ሰበር ዜና – የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የተነሣው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ሥር ዋለ
መጋቢት 8/2004 ዓ.ም፤ ማርች 17/2012/ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊበን ዝቋላ ወረዳ አዱላላ ከተማ የሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በሚገኝበት ተራራ በስተምሥራቅ አቅጣጫ ዛሬ፣ መጋቢት 8 ቀን 2004ዓ.ም ቀትር ላይ የተነሣው የእሳት ቃጠሎ ማምሻውን በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰማ፡፡ በቃጠሎው ሁለት ጋሻ መሬት የሚሸፍን ደን መውደሙ ተነግሯል፡፡
የገዳሙ መነኰሳት ከስፍራው በስልክ እንደገለጹት÷ ዛሬ ቀትር ላይ በገዳሙ ዙሪያ በሚገኘውና የመንግሥት ይዞታ በተደረገው ደን ውስጥ በተነሣው የእሳት ቃጠሎ ሁለት ጋሻ የሚሸፍን የደኑ ይዞታ እንደ ወደመ ተገምቷል፡፡ የገዳሙ ቤተ ክርስቲያን ከሚገኝበት ቦታ በግምት ከ3 – 4 ኪ.ሜ ርቆ የተነሣውን የእሳት ቃጠሎ ለማወቅ የተቻለው ይትጎለጎል የነበረውን ጭስና የእሳቱን ነበልባል ከተመለከቱ በኋላ መሆኑን መነኰሳቱ ለዜና ሰዎች ተናግረዋል፡፡ Read the rest of this entry
![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)