እስላም ክርስቲያኑ አንድ ሆነ ህመማቸው
…march 23/2012
የዚህ ፅሁፍ ሀሳብ ትንሽ ምክር፤ በሚለው ፅሁፍ ትንሽ ነካ ነካ ተደርጓል። ስለዚህ ይሄኛውን “ለዝርዝሩ…” ተብሎ እንደቀረበ ቁጠሩት።
ከዚህ በፊት በአንድ ጨዋታችን ላይ ሙሰሊም ወንድሞቻችንን ስለ አህባሽ ሁኔታ፣ ስለ መጅልሱ አኳሃን እና ስለ መንግስት ምላሽ ጠይቄ ክርስቲያን ወንድሞቻችሁ “አይዟችሁ እናንተ ቤት ያለው ችግር እኛም ቤት አለ እና በርቱ እንበረታለን” ብለዋችኋል ብዬ መልዕክት አስተላልፌ ነበር።
“መሬዎቻችን የጦጣ እና ዝንጀሮ ተረት እየሰሙ ስለሚያድጉ ብልጣብልጥነት ያጠቃቸዋል” የሚል ፅሁፍ የት እንዳነበብኩ ተዘነጋኝ። የኢህአዴግ ባለስልጣናት ደግሞ ሌላ ተረት ሰምተውም የሚያውቁ አይመስሉም። ብልጣብልጥነቱን በጣም ያበዙታል። የሚል አስተያየት ከየቦታው ይሰማል። እውነትም ታድያ ብልጣብልጥነታቸውን በአስተዳደራቸው ብቻ ሳይሆን በሀይማኖት ውስጥ በሚያደርጉት ስልታዊ “ጣልቃ ገብነት” ሁሉ ያሳያሉ።
ሁሴን ከድር (ለዚህ አጭር ጨዋታ ሲባል ስሙ ተቀይራል።) የልብ ወዳጄ እና አብሮ አደጌ፣ አረ ታላቅ ወንድሜም ጭምር ነበር። ስለ አህባሽ ከነገረኝ ቆይቷል። “የሙስለሙን እምነት የሚበርዝ አስተምሮት መንግስት ሊያስገባ አስቧል። እናም የሙስሊሙ ወጣቶች ይህንን ለመቃወም ዝግጅት እያደረጉ ነው!” ብሎኝ ነበር።
እውነትም የተሳካ ዝግጅት አድርገው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ፣ በተቀናጀ እና በሰለጠነ መልኩ ጥያቄያቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ። በዚህም አጥጋቢም ባይሆን አንዳንድ ውጤቶችን እያስመዘገቡ ነው።
መንግስት የአህባሽ እምነት በሙስሊሙ ውስጥ ሰርፆ እንዲገባ ፍላጎት እንዳለው የነገረኝን፤ የሁሴንን ሀሳብ ባለፈው ግዜ ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ጋዜጣ ላይ ባቀረበው ማስጃ እናጠናክረው።
ዶ/ር ሰሚር የተባሉ ሊባኖስያዊ የአህባሽ ሰባኪ ወደ ኢትዮጵያ አህባሽን ለመስበክ መጥተው ነበር መቼም ዶ/ሩን የጋበዛቸው መጅሊሱወይም የአንዱ መስጊድ ኢማም እንዳይመስልህና እንዳትሳሳት፡፡
ምክንያቱም ሰባኪውን የጋበዘው አውራው ፓርቲ ነውና፡፡ ለዚህም ምስክር ይሆን ዘንድ ከዶ/ሩ ንግግር ልጭለፍልህ፡- “When I was invited by D.r Shiferaw. I took some time to check the situation in Ethiopia before meeting with you… I believe the Ethiopian government Prime Minister Meles Zenawi, Shiferaw The Minister Of Federal Affairs and other Ministers understand the issues very well and they are taking the proper and wise steps. I thank all of them for their hospitality” (በዶ/ር ሽፈራው ተጋብዤ ከመጣው በኋላ ከእናንተ ጋር ከመገናኘቴ በፊት በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ለማወቅ ሞክሬአለሁ…የኢትየጵያ መንግስት፣ ጠቅላይ ሚስትር መለስ፣ የፌደራል ጉዳዮች ሚንስትሩ ዶ/ር ሽፍራው እና ሌሎችም ሚንስትሮች ጉዳዩን በደንብተረድተውታል ብዬ አስባለሁ፡፡ መደበኛና ትክክለኛውን መንገድም መርጠው ስለተደረገልኝ አቀባበልም አመሰግናቸዋለሁ) ይህንን ነው እያልኩህ ያለሁት፡፡
ብሎናል ተሜ ደጋግመን እጁ ይባረክ እንላለን።
ታድያ ተዉ በእምነታችን ጣልቃ አትግቡብን ያሉትን እነ ሁሴንን መንግስት ሆዬ፤ “አክራሪ”፣ “አሸባሪ”፤ “ወዘተ” ሁሉ ብሎ ወነጀላቸው። እናም በየዜናው “የተለየ የፖለቲካ ጥቅም የሚፈልጉ አክራሪዎች…” እየተባሉ ይጠቀሱ ጀመር። በአንድ ድምፅ “ወይ ጣጣችን!” ብለን እንገረም።
በሙስሊም ወዳጆቻችን እንዳዛ ስንብከነከን አሁን ደግሞ ዘመቻው ወደ ክርቲያኖቹ ሆኗል። እኔ የምለው ድሮ ድሮ ኢህአዴግ በትግል ሜዳ አንድ ቦታ ነፃ ሳያወጣ ወደሌላ አይዘምትም ነበር። ታድያ አሁን አንዱን ሳይወጣ ወደሌላ እየዞረ ራሱስ ጣጣ ውስጥ የሚገባው ምን ሆኖ ነው።
ክርስቲያኑ ወገናችን እጅግ አድርጎ የሚያከብረው ቅዱስ ቦታ “ዋልድባ” ላይ አደጋ ተጋርጧል። ለስኳር ምርት ሲባል የአባቶች ቀብር ተፈንቅሏል። በዚህም፤ የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ድረሱልን እያሉ በመጮህ ላይ ናቸው። ጩህታቸውንም በርካታ ክርስቲያን ወገኖች እየተቀባበሉት ይገኛሉ።
እኒህን መነኮሳት ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን “የተለየ የፖለቲካ ጥቅም የሚሹ መነኮሳት” ብሏቸዋል። ልብ አድርጉልኝ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ምንኩስና ማለት ከእግዜር ጉዳይ ውጪ እንኳንስ የፖለቲካ ጥቅም እና ፍላጎት፤ ለምግብ እና መጠጥ እንኳ ደንታ የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው። ለዚህም ነው ራሳቸውን ከአለም ጣጣ አግልለው በገዳም የሚኖሩት። እነዚህ ናቸው እንግዲህ “የተለየ የፖለቲካ ጥቅም ያላቸው መነኩሴዎች” የተባሉት። ኢቲቪ ዜና አንባቢዋ እራሷ አፏ እንዴት እሺ ብሎ ተናገራላት…?
የሆነ ሆኖ አሁን መንስግስታችን ሀይማኖቱቹን በሙሉ እየተነኮሰ የራሱን አብዮታዊ ዴሞክራሲ እምነት እያስፋፋ ይገኛል። የሚል ወቀሳ ከሁለቱም ዋና ዋና እምነቶች እየቀረበበት ነው። ለወትሮው ከፋፍሎ በመግዛት የሚታወቀው ኢህአዴግ አሁን ግን ሀብቱም በዛ መሰል፤ ሙስሊምና ክርስቲያኑን ጅምላውን ካልሸመትኳችሁ ጅምላውን ካልሸጥኳችሁ እያለ ይገኛል… (እያሉ ይተቹታል፣ ተችተውም አይተዉት ይታገሉታል! እየተባለ ነው።)
ገጣሚዎችም
እስላም ክርስቲያኑ አንድ ሆኖ ህመማቸው
- Share this:
Posted on March 23, 2012, in AFRICAN NEWS, ETHIOPIA AMHARIC, ETHIOPIA ENGLISH, WORLD NEWS and tagged Accessories, Facebook, Kleiner Perkins Caufield & Byers, Mark Pincus, Military, Shopping, Twitter. Bookmark the permalink. Leave a Comment.

![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)
Leave a Comment
Comments (0)