Monthly Archives: April 2012
ሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣ ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል
april 30-2004
ዛሬም እየተገደልን ነው… ሲደብር! (አቤ ቶኪቻው)
april 30-2004
ሰሞኑን ከተሰሙ አስደንጋጭ ዜናዎች ውስጥ የሚከተለው ይገኛል…
“በዛሬዉ እለት በአርሲ አሳሳ ከተማ የጁምአ ሰላት ከተሰገደ በኋላ ሼህ ሱዑድ በአንድ መስጂድ ዳዕዎ አድርገዉ ሲወጡ በፓሊስ በመያዛቸዉ፤ የአካባቢዉ ሙስሊም ህብረተሰብ “ሼሁ ለምን ይታሰራሉ ምንም ጥፋት አልፈፀሙም” በሚል ለማስለቀቅ ሲሞክሩ ከፓሊሶች ጋር በተፈጠረዉ አለመግባባት ፓሊስ በከፈተዉ ተኩስ እስካሁን ባለዉ መረጃ መሠረት አምስት(5) ሰዎች መገደላቸዉና ብዙ ሰዎች መቁሰላቸዉን የአካባቢዉ ምንጮች ገለፁ:: ከተገደሉት ሰዎች መካከል ሼህ ኸድር የሚባሉ ታላቅ አሊም እንደሚገኙበትም ምንጮች ጨምረዉ ገልፀዎል:: እንደሚታወሰዉ ሼህ ሱዑድ ሻሸመኔ በተካሄደዉ ስብሰባ ላይ “ኢህአዴግን ለሀያ አመታት ስንደግፈዉ ኖረን አሁን እንዴት አሸባሪ አክራሪ ብሎ ይወነጅለናል” በማለት የተሰማቸዉን ቅሬታ በስብሰባዉ ላይ ገልፀዉ እንደነበር የሚታወስ ነዉ:: Read the rest of this entry
በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣ ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል
Monday, April 30, 2012
የኢትዮጵያ ብሎጎች ምን ጻፉ?
Posted on April 29, 2012
የአሁኑን ሳምንት የኢትዮጵያ ብሎጎች ክለሳ ስሰራ ትልቁ ተግዳሮቴ የነበረው አብዛኞቹ ካሁን በፊት በዘዴ ወኪል ሰርቨርን በመጠቀም የማነባቸው ብሎጎች አብዛኞቹ ወኪል ሰርቨሮችም ጭምር ስለታገዱ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ድረስ ማንበብ አልቻልኩም ነበር:: ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ በወኪል ሰርቨሮች በኩል ማንበብ ያቃተኝን ጽሁፍ ከሀገር ውጪ ያሉ ወዳጆቼ እንዳለ ገልብጠው በውስጥ የኢሜል አድራሻዬ በኩል እንደ ቅጥያ ዶክመንት ልከውልኝ ማንበብ ችያለሁ:: ሌሎች ያልታገዱ አዳዲስ ወኪል ሰርቨሮችንም እንድሞክራቸው ልከውልኝ መጠቀም ችያለሁ:: ስላጋጠመኝ ችግር እና የሳምንቱ አብይ ጉዳይ ሆኖ የብዙ ብሎግ ጻሀፊያንን ትኩረት ስቦ ስለነበረው የብሎጎች እገዳ ይህችን ታህል ካልኩ ሌሎች ምን እንዳሉ እስቲ ላቃምሳችሁ:: በፍቄን ላስቀድም በፌስቡክ ግድግዳው ላይ አጭር ጽሁፍ አስነብቦ በብሎጉ ላይ ኢትዮጵያ መንግስት መጠላቱን የሚያሳብቁ ምልክቶች በሚል ርእስ የጻፈውን ጽሁፍ ትይይዝ አስቀምጧል:: ሙሉውን ጽሁፍ ትይይዙን ጠቅ በማድረግ ይከፈቱት አልከፍት ካሎት በፍቄ በፌስቡክ ግድግዳው ላይ ያሰቀመጠውን ጽሁፍ በማንበብ ይሞክሩት: Read the rest of this entry
የመንግሥት ሌቦች አደራ-ቢስነትና ሕዝብ ኃላፊነት
Sun, 04/29/2012
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ስለመንግሥት ሌቦች እየተናገረ ነው፤ ሌቦቹን ግን እሱም አያውቃቸው፤ እነሱም እየሰሙት አይደለም፤ የመንግስት ሌቦች የተባሉት የሚግጡባቸው ዋናዎቹ መስኮች ታክስ፣ መሬትና የንግድ ውድድር መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጾአል፤ ከዚህም በላይ የተባሉትን የሌብነት መስኮች ከለምነት ወደበረሃነት ለመለወጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ኃላፊነት አለበት ያለ መሰለኝ፤ ሥልጣን ሳይኖር ኃላፊነት ከየት ይመጣል? እንግዲህ የፌዴራል ፖሊሱንና ሌላውን አልፎ፣ የደኅንነቱን ሰራዊት አልፎ፣ የጸረ-ሙስና ኮሚሽንን አልፎ፣ ዓቃቤ ሕግን አልፎ ሕዝብ እነዚያን ለምለም መስኮች ማድረቅ እንዴት ይችላል? Read the rest of this entry
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል በሚል የወጣውን መረጃ ተከትሎ ኤርትራ ውጥረት ውስጥ ገብታለች
Sunday, April 29, 2012
በአፋር አንድ ወጣት ተገደለ ሶስት ቆሰሉ
በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ
Friday, April 27, 2012




![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)