Daily Archives: April 24, 2012

ሰበር ዜና፡ በአዲስ አበባ አንድ ወጣት ራሱን ቤንዚን አርከፍክፎ አቃጠለ

Published On: Tue, Apr 24th, 2012                ሰበር ዜና                                                               

ዛሬ ከምሽቱ 11 ሰአት አካባቢ በአዲስ አበባ አራዳ ጊዮርጊስ አደባባይ /መሀል ፒያሳ/ ዳዊት የተባለ ወጣት / በግምት እድሜው 30 አመት ይሆነዋል/ ራሱ ላይ ቤንዝን አርከፍክፎ አቃጥሏል ሲል የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በፌስቡክ ገጹ ላይ ዘገበ። ተመስገን በዘገባው ዳዊት ራሱን እያቃጠለ ሳላ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ተረባርበው እሳቱን ያጠፉለት ሲሆን በአሁኑ ሰአት በየካቲት 12 ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ህክምና እየተደረገለት ነው ብሏል። የዚህን ዜና ዝርዝር መለስ ብለን እናቀርባለን።

የቴዲ አፍሮ አልበም ሽያጭ ሬከርድ አስመዘገበ

Published On: Tue, Apr 24th, 2012
 
 ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የተለቀቀው የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ‹‹ጥቁር ሰው›› አልበም በ300 ሺሕ ሲዲና በ120 ሺሕ ካሴት ሽያጭ፣ በአጠቃላይ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አሥር ሚሊዮን ብር ገደማ በማስገባት፣ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ታሪክ አዲስ ሬከርድ ማስመዝገቡ ታወቀ፡፡ ሽያጩ የተመዘገበው አልበሙን ከአዲካ ኮሙዩኒኬሽንና ኢቨንትስ ተቀብለው በማከፋፈል እየሸጡ ካሉት ከኤሌክትራና ከአምባሰል ሙዚቃ ቤቶች፣ እንዲሁም ከጣና ኢንተርቴይንመንት ነው፡፡ ኤሌክትራና አምባሰል ሙዚቃ ቤቶች በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች ለሽያጭ ሲያቀርቡ፣ ጣና ኢንተርቴይንመንት በሰሜን ኢትዮጵያ ያከፋፍላል፡፡

አዲካ ለሙዚቃ ቤቶቹ እያንዳንዱን ሲዲ በብር 17.50 እያንዳንዱን ካሴት ደግሞ በዘጠኝ ብር ሲያስረክብ፣ ገበያው ውስጥ አንዱ ሲዲ 25 ብር አንዱ ካሴት ደግሞ 13 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳ አንዱ ሲዲ በተወሰነለት ዋጋ እንዲሸጥ ቢታሰብም በየመንገዱ እስከ ሃምሳ ብር እንደተሸጠ ታውቋል፡፡ Read the rest of this entry

በጠራራ ጸሐይ ተዘረፍኩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ”(ድምጻዊ ተሾመ አሠግድ)

https://platform.twitter.com/widgets/hub.html

 

 

(ምንጭ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 38</em>) ነዋሪነቱ ሚኒሶታ የሆነው ስመ ጥሩው ድምጻዊ ተሾመ አሠግድ “በጠራራ ጸሐይ ተዘረፍኩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ” ሲል ለዘ-ሐበሻ ጋዜጣ በሰጠው  መግለጫ ላይ አስታወቀ።  ካለፈቃዱ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) የተባለው  ድምጻዊ የተሾመን “የኔ አካል” ወስዶ መሥራቱን አምርሮ ተቃውሟል። “አንድ ዘፋኝ የአንዱን ወስዶ ለሕዝብ ሲያቀርብ  ባለቤቱን ማስፈቀድ ይኖርበታል” ያለው ተሾመ “ጎሲ ከ20 ዓመት በፊት የተጫወትኩትን፦ <strong>“የኔ አካል የኔው ነሽ፤ ምን አወርስሻለሁ፤http://youtu.be/BdAluuid0KE አንጀቴና ልቤን ያው ትቼልሻለሁ”</strong>”  ዘፈኔን ካለፈቃድ በክሊፕ ጭምር ማውጣቱ ክፉኛ በድሎኛል” ካለ በኋላ “ድምጻዊው ጎሳዬ ቀለሙ የኔን ብቻ ሳይሆን ዘፈኑን የደረሱልኝን ገጣሚው ይልማ ገብረአብን እና የዜማ ደራሲውን አበበ መለሰን ሁሉ ተዳፍሯል። ይህንን ዘፈን በፈረንጆች በ1987 ዓ.ም አካባቢ ከነራሄል ዮሐንስ ጋር በጋራ ባወጣሁት አልበም ውስጥ ሳካትተው ግጥሙን እና ዜማውን የሰጡኝ እነርሱ ናቸው። በሙዚቃ ክሊፑ ላይ የነዚህ ስም አልተጠቀሰም። ይልቁንም የሌላ ሰው ስም በመጻፍ የኛን ሥራ የራሱ በማስመሰል አቅርቦ ሥራዬን ዘርፏል” ሲል ቅሬታውን አሰምቷል። “ወደ ሕግ ጋር መሄዴ የማይቀር ነው። ጉዳዩን ፍርድ ቤት አድርሼ እሞግተዋለሁ” ያለው ድምጻዊ ተሾመ አሰግድ “የኔ አካል” የተሰኘውን ሥራዬን ካለፈቃዴ ተነጥቂያለሁና ከዚያ በፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ፤ በጠራራ ጸሐይ ነው የተዘረፍኩት።” በማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰረቁ ዘፈኖች ሲወጡ ከኦርጂናሉ ዘፋኝ በይሁንታ መገኘቱን እና አለመገኘቱን ማረጋገጥ ይኖርበታል ሲል ጥሪውን አቅርቧል። “ድምጻዊ ጎሳዬ ቀለሞ (ጃኪ ጎሲ) የተሾመ አሰግድን ዘፈን መሥራቱን አምኖ በቪድዮ ክሊፑ ላይ ምስጋና አቅርቧል” Read the rest of this entry

የኤርትራው መንግስት በሞት መንገድላይ ናቸው ተባለ !

Published On: Tue, Apr 24th, 2012
 
 የኤርትራው ፕረዚዳንት በሞት መንገድ ላይ ናቸው እየተባለ የሚወራው ጭምጭምታ ወደ እውነታ የተቃረበ ነው የሚሉት ብዙዎች ናቸው ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል ። ከሰሞኑ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ለማለዳ ታይምስ ዝግጅት የደረሰን ጥቆማ   በፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምትክ የመጀመሪያ ልጃቸው የሆነውን አብርሃም ኢሳያስ አፈወርቂን ለመተካት ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል በይበልጥም የመከለካያ ሚንስቴር የነበሩት  ስብሃት ኤፍሬም የፕረዘንዳንትነቱን ቦታ ይይዛሉ ተብሎ የሚባል ጭምጭምታም አለ ። Read the rest of this entry
%d bloggers like this: