በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ

Friday, April 27, 2012
ኢሳት ዜና:- 

በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ  22 ሰዎች መሞታቸውና በርካቶች መቁሰላቸው ተዘገበ።  እንደ ፍኖተ-ነጻነት ዘገባ በሁለቱ ክልሎች የድንበር ነዋሪዎች መካከል ለተፈጠረው ግጭት ምክንያቱ የቦታ ይገባኛል :
የአካባቢው ነዋሪዎች  እንደገለጹት ከሆነ “በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ልዩ ሥፍራው “ጊዳ ኪራሞ” እና “ጊዳ አያና” በተባሉ ወረዳዎች ለተነሳው ግጭት መንስዔው፤ አቤንቱ፣ ቄሎ እና ዋስኪ በተባሉ አካባቢዎች የተፈጠረ የይገባኛል ጥያቄ ነው፡፡
ለዘመናት ተከባብረውና ተዋደው የሚኖሩት እነዚህ ህዝቦች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተደጋጋሚ እንደዚህ ዓይነት ግጭት ውስጥ መግባታቸው፤ የአካባቢውን ነዋሪዎች እጅግ ማሳዘኑ ታውቋል። “ከዚህ በፊት በ2000 ዓ.ም  በ አካባቢው የተፈጠረው ተመሣሳይ ግጭት  ለ200 ሰዎች ህይወት ሞት፣ ለበርካቶች መቁሰልና መፈናቀል ምክንያት መሆኑ አይዘነጋም።
“የአሁኑን ግጭት አሣሳቢ የሚያደርገው ግን ፤በደቡብ ክልል ቤንቺ ማጂ ዞን ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆችን የመንግስት ባለሥልጣኖች፦”ወደ አገራችሁ ሂዱ” በማለት ባባረሩ ማግስት የተከሰተ መሆኑ ነው”ብለዋል-አንድ የአካባቢው የአገር ሽማግሌ- ለኢሳት ዘጋቢ በሰጡት አስተያዬት። “እየሆነና እየተሰማ ያለው ነገር ሁሉ ጆሮን የሚቀፍ ነው፤ይህ ግጭት በባህርይው ኢትዮጵያዊ አይደለም” ሲሉም አክለዋል-የአገር ሽማግሌው።
በአሁኑ ጊዜ  የቆሰሉት በርካታ ሰዎች በለቀምት ሆስፒታል በመታከም ላይ ናቸው።   ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአካባቢው ነዋሪዎች፤ “ለዘመናት በጉርብትና በሠላም ይኖር በነበረው ሕዝብ መሀከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተፈጠረ ያለው ግጭት፤የኢህአዴግ የዘር ፖለቲካ የወለደው ነው”ማለታቸውን የፍኖት ዘገባ ያመለክታል።
 
About these ads

Posted on April 27, 2012, in AFRICAN NEWS, ETHIOPIA ENGLISH, WORLD NEWS and tagged , , , , , , , . Bookmark the permalink. Leave a Comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: