Daily Archives: May 1, 2012

ይድረስ ለአቶ መለስ፤ አንድ ቀልድ ልንገርዎ…!

may 1 / 05/ 2004

በአንድ ቤተሰብ ውጥ የሚኖሩ ሰዎች ነበሩ። የቤተሰቡ ሃላፊ የሆኑት አባወራ ሲያገኙ በድፍረት ሲያጡም በሌላ ድፍረት ጠጥተው ሞቅ ብሏቸው ነው የሚገቡት። ስጠረጥር የዘንድሮ ኑሮ እንደምንም ብለው ሞቅታ ውስጥ ካልተደበቁ በስተቀር እንደማይቻል ገብቷቸዋል። አሁንም ስጠረጥር አባወራው በዱቤም ይሁን፣ በብድርም ይሁን፣ በቅልውጥ መጠጥ ቤት ካላመሹ በቀር በጊዜ ቤታቸው ቢገቡ የቤተሰቡ አባላት የሚጠይቋቸውን ጥያቄ መመለስ እንደማይችሉ  ስለሚረዱትም ይመስለኛል። ታድያልዎ ከእለተታ አንድ ቀን አንዱ ልጃቸው “ዛሬስ አባዬ ሲመጣ ጠብቄ የማናግረው አለኝ” ብሎ ሲጠብቅ፣ ሲጠብቅ፣ ሲጠብቅ ተስፋ ሊቆርጥ ትንሽ ሲቀረው መጡ…ማ…? አባወራው! ልጅም ገና እንደመጡ የተበጫጨቀ የትምህርት ቤት ዩኒፎርሙን እያሳያቸው “አባዬ… ይኸውልህ ትምህርት ቤት የምለብሰው ዩኒፎርም ይሄ ነው… ጓደኞቼ እብዱ እብዱ… እያሉ ያበሽቁኛል። ደሞ ደብተሬም አልቋል። ሌላ ደግሞ …” እያለ ጥያቄ ቢያከታትልባቸው ግዜ በሞቅታ እና በመልስ እጦት ውስጥ ያሉት አባት ምን አሉት መሰልዎ… “አንተ ልጅ ዘወር በል ፖለቲካ አታውራብኝ!” ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ቀልዱ አላስቆትም!? እንግዲያስ ከቀልብዎ አይደሉም ማለት ነውና ደግመው ያንብቡት። ዘንድሮ እንደሁ ባለስልጣኑ ቀልብ ነዋሪው ደግሞ ቀለብ በፅኑ የተቸገረበት ሁኔታ ነው ያለው (አሁን እኔው ሳቄ መጣ!) ይህንን ቀልድ ለምን አወራሁልዎ እንደው እስቲ ዘና ላድርጋቸው ብዬ ነውን? በፍፁም አይደለም አንበሳዬ… እህስ ይበሉና ይከተሉኝ ይምጡ አዲስ መስመር ላይ፤ አቶ መለስ የምሬን ነው የምልዎ ግራ መጋባት ይታይብዎታል። ትንሽ ይረጋጉ እንጂ… (አክብሬዎት እንጂ ሞቅታ ውስጥ ነው ያሉት!) ብዬ ልናገር ነበር። ነገር ግን ጠቅላይ ሚንስትሬ ነዎትና እንዲህ እንደዞህ አልልዎትም። Read the rest of this entry

%d bloggers like this: