ይድረስ ለአቶ መለስ አና እየገባቸው እንዳልገባቸው ለሚሆኑ አንባ ገነን የወያነኔ ባለስልጣናት በሙሉ።
5/4/2012ኢትዮጵያዊ የመሆን ሁኒታችን አያጠራጠረ ከመጣ ብዙ አመታቶችን እያስቆጠርን ይመስለኛል ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ማለት በናንተ አመለካከት በአንድ ፓአርቲ ወይንም የወያኔ አባል ያልሆነ ሁሉ ኢትዮጵያዊ መስሎ አይታያችሁም ፤ወደ ቁምነገሩ ልግባና መንግስት እንዴት ነው የሙስሊሙ ጥያቂ አልገባ ያለው ሁሌም በሚሰጠው መግለጫ ብሎም በአቶ መለስ አንደበት ስሰማው የሚመልሱት ሌላ የተጠየቁት ሌላ ይህ አይነት አሰራራቸው የተለመደ ቢሆንም የአሁኑ የሙስሊሙ ጥያቄ ግን አንድና አንድ ነው፡፡እሳቸው ወይንም አብሮዋቸው የሚሰሩ ሆድ አደሮች ሙስሊሙ ለጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት ሳይሆን ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ሌላ ጥያቄን በጥያቄ የመለሳችሁ ነው የሚመስለው ጥቂቶች ናችሁ የሚል ነበር ሙስሊሙ ህብረተሰብ ግን እርሶና አበሮቾ ለጠየቁት ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ተሠጦት ብዙ ሚሊዮን መሆናችንን በተግባር አሳይተናል ፡፡እዚጋ አንድ ያልገባዎት እና ያልተረዱት ነገር ያለ ይመሰለኛል የስልጣን እድሚዎትን ለማራዘም የዘር ክፍፍል ተጠቅመዋል ይህ እስትራቴጅ ግን ለሀይማኖት ግን መጠቀም የማይታሰብ ነው፡ያም ሆነ ይህ በሀይማኖት ውስጥ ጣልቃ መግባት እድሜን ለማራዘም ሳይሆን እድሜን ለማሳጠር ስለሚያጋልጦ አንድም ቀን ብትሆን እድሜ ናትና ለጉዳዩ አስቸኩአይ መልስ መስጠት ተገቢ ነው እላለው፡ሙስሊሙ ህብረተሰብ ለጥያቄው መልስ እስካላገኘ ድረስ 100 ሺ ግዜ መግለጫም ሆነ አለኝ ብለው የሚተማመኑበትን ጦር አምጥተው ቢደረድሩ እኛ ሙስሊሞች ከአላማችን ያንዲት ነጥብ ያክል ወደውሀላ አንልም ጥያቄአችን አሁንም ቢሆን እደግመዋለው አልገባ ካልዎት ደጋግመው ያንብቡት፡እርሶ ሲገቡ ከርሶ ጋር ተከትሎ የገባ በእስልምና ሀይማኖት የሚነግድ አህባሽ የሚባል ቫይረስ ከላያችን ላይ ይውረድ ነው ጥያቄአችን ይህ ቫይረስ የራሱን እምነት የማስፋፋትም ሆን የማስተማር መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ይህን ማድረግ የሚችለው ግን በኛ በሙስሊሞች መስጅድ ት/ቤት ሸሪያ በመሳሰሉት በማንኛውም ነገር እኛን ሙስሊሙሞችን ሊወክለን አይችልም ፡ከሙስሊሙ ህብረተስብ ውጪ መንቀሳቀስ ይችላል እንደሌላው ሀይማኖት እራሱን ችሎ፡ እንግዲ ጥያቄአችን ይህንን ይመስላል፡ ሙስሊሙ ህብረተስብ ህግ እና ደንብን በማክበር ይመስለኛል ተቃውሞአችንን በመስጅዶቻችን ውስጥ እያሰማን 12 ኛ ሳምንታችንን ያስቆጠርነው፡ ኢቲቪ 4/4/2004 መግለጫ ብሎ በተናገረው ላይ የመንግስት ዝም ማለት ፍርሀት እንዳይመስላችሁ በማለት ተናገሮአልእናንተስ የሙስሊሙ ህዝብ በመስጅድ ውስጥ ታአፍኖ ተቃውሞ ማድረግ ፍርሀት ይመስላችሁ ይሆን ? እንደዛ አስባችሁ ከሆነ በጣም ተሳስታችሀል ፡ ማንኛውም ሙስሊም በሀይማኖቱ ለሚመጣበት ነገር ህይወቱን ከመስጠት ወደውሀላ እንደማይል ልትገነዘቡ ይገባል ፡ ይልቁንስ ባጣዳፊ ሁኔታ መልስ መስጠቱ ጠቃሚ ነው ብዪ እገምታለው። ከኡስማን አ/ሰመ
Posted on May 4, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC and tagged Addis Ababa, Ethiopia, Islam. Bookmark the permalink. Leave a Comment.
![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)
Leave a Comment
Comments (0)