Daily Archives: May 7, 2012

(ሰበር ዜና) የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ ከሓላፊነታቸው ተነሡ

may 5/7/2012
 
·  የዋና ሓላፊው መነሣት በቤተ ክህነቱ የጨለማ ቡድን የተቀነባበረ ነው፤ የአቡነ ጳውሎስ ስውር ትእዛዝና የአቡነ ገሪማ የተለመደ አድርባይነት እንዳለበትም ተረጋግጧል
·   የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ “እኔ በማላውቅበት ኹኔታ የመምሪያው ሓላፊ ሊቀየሩ አይችሉም” በማለት ርምጃውን ተቃውመዋል
·  “ተግባሩ በቤተ ክህነታችን እየኾነ ያለው አሳሳቢ ኹኔታ መገለጫ ነው” /ማኅበረ ቅዱሳን/
(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 29/2004 ዓ.ም፤ May 7/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ከአሿሿማቸው እና ከተሾሙበት ጥቅምት ወር 2003 ዓ.ም አንሥቶ መነጋገርያ የኾኑት በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው ከሓላፊነታቸው መነሣታቸው ተሰማ፤ Read the rest of this entry

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ያልተጠበቀ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ሰራተኞች አስጠነቀቁ

የኢሳት አማርኛ ዜና» በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ያልተጠበቀ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ሰራተኞች አስጠነቀቁ

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ሳምንታት ሸኚዎች ወደ ውስጥ ገብተው ዘመዶቻቸውን እንዳይሸኙ ክልከላ መጣሉን በተደጋጋሚ ስንዘግብ ቆይተናል። የአየር  መንገድ ሰራተኞች እንደሚሉት መንግስት እግዱን የጣለው የሽብር ጥቃት እንደሚፈጸም መረጃው ስለደረሰው ነው። ይሁን እንጅ አንዳንድ ወገኖች መንግስት ወደ ሳውዳ አረብያ  የሚጎርፉትን ወጣት ሴቶች ህዝቡ እንዳያያቸው የተጠቀመበት ስልት ነው ሲሉ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣት ሴቶች በቦሌ አየር ማረፊያ ሲስተናገዱ በፊልም የተደገፈ መረጃ አቅርበዋል። ኢሳት ከአንዳንድ ሰራተኞች ባገኘው ጥቆማ መንግስት በሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ እንዲሁም የምእርባዊያንን ድጋፍ እንደያዘ ለመቆየት ምናልባትም የተቀናበረ የፈጠራ የሽብር ጥቃት ራሱ አዘጋጅቶ ራሱ ሊፈጽም ይችላል የሚል ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል። Read the rest of this entry

በደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ እያካሄዱ ነው ፣ከፍተኛ ነውጥም ተነስቶአል ከ300 ተማሪዎች በላይ በአማራ ክልል ፖሊስ ታስረዋል።

may 5,7,2012

በደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ከፍተኛ የተማሪዎች የነውጥ እንቅስቃሴ እየተካሄደ መሆኑን  ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል በትላንትናው እለት የተጀመረው የተማሪዎች እረብሻ ዛሬ ረገብ ብሎ ቢዉልም መንግስት የምንፈልገውን እስካላስተካከለልን እንቀጥላለን በማለት ዉሳኔአቸውን ሲገልጹ ውለዋል  ። የዚህ የተማሪዎች ነውጥ ጉዳይ  የተነሳበትን መንስኤ በትምህርት ቤት ዉስጥ የሚገኘው የምግብ ጥራት ከፍተኛ የንጽህና ጉድለት ያለበት ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ተማሪዎች ለምግብ ወለድ በሽታ መጋለጣቸውን አንዳድንድ ተማሪዎች ጠቁመዋል ። መንግስት የትምህርት ቤቱችን ጥራት ፋሲሊቲ አሟልቻለሁ እያለ የሚደሰኩረው ውሸት ነው ምንም የተሟላ ነገር የለም በባዶ ነው ትምህርት ቤት ዉስጥ ጊዜአችንን የምናሳልፈው ይህ ደግሞ የእውቀት መገብያ እንጂ እድሜ ማሳለፊያ ወይንም መዝናኛ ክበብ አይደለም ያሉት ተማሪዎቹ መስተካከል የሚገባቸውን ነገሮች ሳይፈታላቸው ሃሳባቸውን መለወጥ እንደማይፈልጉ ጠቁመዋል ። የማለዳታይምስ ዘጋቢ አቡጊዳ ከስፍራው እንደዘገበው ከሆነ በአሁን ሰአት  የተወሰኑ ተማሪዎች ወደ ግቢ በሰላማዊ መንገድ ገብተዋል…..በርካታ በግምት ከ300 ተማሪዎች በላይ ታስረዋል….እጅግ በጣም ብዙ ንብረት ወድሟል…..አንድ አንድ ተማሪዎች አምልጠው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደዋል…..ለተማሪዎቹ የትራንስፖርተ አገልግሎት ለመስጠት ሲሯሯጡ የነበሩ ደላላዎችም ታስረዋል….በሌላም በኩል ከባህርዳር ወደ ደብረማርቆስ የተላከው ልዩ እዝ የመከላከያ ወታደር እና  የፖሊስ ሰራዊት ወደ ግቢው በመግባት ተማሪዎቹን አፍሶ እንደወሰደ የደረሰን ሪፖርት ያመለከታል ።ይህ የተማሪዎች ነውጥ በዚሁ ከቀጠለው ወደ ሌሎች ትምህርት ቤቶች እንዳይዛመት ተሰግቶአል ሆኖም ግን ከተዛመተ የገዢውን መንግስት አጣብቂኝ ውስጥ ሊከተው እንደሚችል አንዳንድ ግለሰቦች ግልጸዋል ።በተለይም እስላም ክርስቲያን አማራ እየተባለ በተለያዩ ነገሮች ላይ ምንግስት ጸብ የጫረባቸው ነገሮች ሁሉ ከኑሮው ጋር ተደማምሮ ህዝቡን ለአመጽ እየገፋፋው እንደሆነ እና ህዝቡም አማራጭ አጥቶ ዝምታውን እንደመረጠ ስማቸው እንዳይገለጽ የፖለቲካ ተንታኝ ተናግረዋል።

አቶ ሽመልስ ከማል እንኩ ሰላምታ!

may5/7/2012

ባለፈው ግዜ መንግስት ቅድመ ምርመራ ወይም የሳንሱርን ትንሳኤ ሊያመጣው እንደሆነ ፍንጭ አግኝተናል ብለን አንዳንድ ጩኸቶችን ጮኸን ነበር። በጩኸታችን ማግስት የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በመላው አለም ተከበረ። ከመላው አለም አክባሪዎች ውስጥ “ወጉ ለምን ይቀራል” ብላ ኢትዮጵያም አንዷ ሆና ነበር።

በክብረ በዓሉ ላይ አቶ ሽመልስ ከማል ካልታሰሩ ጋዜጠኞች ጋር አንድ መድረክ ላይ ተገናኝተው ነበር አሉ። ታድያ አንድ ጥያቄ ተወነጨፈባቸው። “መንግስት ቅድመ ምርመራ ወይም ሳንሱርን ድጋሚ እያመጣው ነው፤ ይኸው “ብርሃንና ሰላም የምታሳትሙትን አይቼ ቀልቤ ካልወደደው እንቢ የማለት መብት አለኝ” የሚል ውል እያስፈረመን ይገኛል።” ብለው ነግረዋቸው ነበር። ታድያ አቶ ሽመልስ ምን አሉ?

“ይሄ የብርሃንና ሰላም ድርጅት ያወጣው ህገ ደንብ ነው እኛ በዚህ ላይ የለንበትም!” ብለው እርፍ! እኛስ ምን እንላቸዋለን… Read the rest of this entry

Allahu Akber!! Yemejis ameraroch mulu lemulu kesltanachew endinesu tewesene

Published: May 7, 2012 by AhmityFiled under:   AHBASHViews: 925 Tags:

አላሁ አክበር!አላሁ አክበር! የመጅሊስ አመራሮች ሙሉ ለሙሉ ከስልጣናቸዉ እንዲነሱ ተወሰነ::የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ወይም የመጅሊስ አመራሮች ሙሉ ለሙሉ ከስልጣናቸዉ እንዲወርዱ ዉሳኔ መተላለፍ ተሰማ:: ይህ ዉሳኔ የተላለፈዉ ባሳለፍነዉ ሀሙስ ሲሆንለመጅሊስ አመራሮች ይህ መራር ዜና በአቶ ፀጋዬ በርሄና በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተርዶ/ር ሽፈራዉ አማካኝነት ይፉ ተደርጎል:: በዉሳኔዉም መሠረት አሁን በስልጣን ላይ የነበሩት አመራሮች በሙሉ ከስልጣናቸዉ እንዲነሱና ስልጣናቸዉን እንዲያስረክቡ መወሰኑ ተገልፆል:: Read the rest of this entry
%d bloggers like this: