Daily Archives: May 10, 2012

ሁሉን አቀፍ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ የጉባኤው አባል ያደረገን ያለእውቅናችን ነው!

ከዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን በሜልበርን የተሰጠ መግለጫ

Democracy for Ethiopia Support Group In Melbourneላለፉት 20 ዓመታት በህዝባችንና በሃገራችን ላይ የጥፋት ተልዕኮውን እየፈጸመ ያለውን ወያኔ መራሽ የኢትዮጵያ መንግስት የግንባር ሥጋ ሆነው የሚታገሉ ወገኖችን በገንዘብና በሞራል ለማገዝ በሚል ዓላማ ከ8 አመታት በፊት ሜልበርን በሚገኘው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ የተቋቋመው ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን በየወቅቱ በተለዋወጡ አመራሮቹ አስተባባሪነት የተቁቋመበትን ዓላማ በተገቢው ሲያከናውን ቆይቷል።አሁንም እያከናወነ ይገኛል። Read the rest of this entry

የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎቹ ላይ እያደረሰ ያለውን የመብት ረገጣ እና እስራት በአስቸኳይ ያቁም!

በሀይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባቱን እና ዜጎችን ማፈናቀሉን ያቁም!!

በብራሰልስ ከኢትዮጵያዊያን የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅ ድርጅቶች የተሰጠ መግለጫ ሜይ 03፣ 2012 ብራሰልስ፣ ቤልጀም

አገራችን ኢትዮጵያ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ጎዳና መከተሏ፣ የህግ የበላይነት ስለመረጋገጡ እና የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበራቸው እየተደሰኮረልን ሁለት አስርት አመታትን አስቆጥረናል። ይሁንና በእነዚህ ሁለት አሥርት ዓመታት ዉስጥ ያየነው እና እያየንም ያለነው እውነታ ከዚህ የመንግስት ፕሮፓጋንዳ ተገላቢጦሽ ነው። አገሪቱ የምትገኝበት ሁኔታ የዲሞክራሲ እምርታ ይቅርና ጭላንጭሉንም አይታለች ለማለት የሚያስደፍር አይደለም። ከፓርቲ አንባገነንነት አልፎ የግለሰቦች ወይም የጥቂት ቡድኖች አንባገነናዊነት እውን የሆነባት አገር ከሆነች ዉሎ አድሯል። መንግስት ራሱ ያጸደቀውን ህገ-መንግስት ሳይቀር በመጣስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ እያደረገ ያለውን ግፍ አጠናክሮ ቀጥሎበታል። በዚያው መጠን የህዝብ እሮሮ፣ ስቃይና መከራ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መጥቷል። በኢትዮጵያ ሰፊ ህዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት እየመነመነ መጥቶ እርቃኑን የቀረው ስርዓት አሁንም ለህዝቦች ፍላጎት ጆሮ በመስጠትና የአገሪቱን አጠቃላይ ደህንነት ከግምት በማስገባት ድርጊቱን ከማሻሻል ይልቅ አፈናዉን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህም የተነሳ፦ Read the rest of this entry

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠና ባልጨረሱ ፖሊሶች ተደበደቡ

Thursday, 10 May 2012
-በጥይትና በከባድ ድብደባ የተጎዱ ተማሪዎች ህክምና ላይ ናቸው
-የከተማው ነዋሪም ተቃውሞውን ተቀላቅሏል
ትላንት ለተቃውሞ በወጡ የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ታጣቂዎች በጥይትና በዱላ ጉዳት ማድረሳቸውን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ ከትላንት በስቲያ እሁድ ሚያዝያ 28 እና ትላንት ሰኞ ሚያዝያ 29 በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ሊከሰት የቻለው ተማሪዎች ተጓደለ ያሉትን የምግብ ጥራት በመቃወማቸው እንደሆነ ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ Read the rest of this entry

Breaking News : Students Protest in Bahir Dar and Gonder Universities

Wednesday, May 9, 2012

By Derese Tariku, for De Birhan

09 May 2012
Following the protests and arrest of students of Debre Markos University, northern Ethiopia, the students of Bahir Dar University and Gonder University have began protests. It has been confirmed that both Poly and Peda Campuses of Bahir Dar University (BDU) and Tewodors and Maraki Campuses of Gonder University (GU) have spent the whole day today (09May 2012) in protest. “The students protest is spreading like a wildfire” said a student from Maraki Campus, GU.  Regional police force and Federal police are approaching the campuses.
Several students have been injured and arrested following “rights related” protests by Debre Markos University  students in the past two days.
There are over 40,000 students in both Bahir Dar and Gonder Universities enrolled under the regular program.
Details to come…
%d bloggers like this: