ሁሉን አቀፍ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ የጉባኤው አባል ያደረገን ያለእውቅናችን ነው!

ከዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን በሜልበርን የተሰጠ መግለጫ

Democracy for Ethiopia Support Group In Melbourneላለፉት 20 ዓመታት በህዝባችንና በሃገራችን ላይ የጥፋት ተልዕኮውን እየፈጸመ ያለውን ወያኔ መራሽ የኢትዮጵያ መንግስት የግንባር ሥጋ ሆነው የሚታገሉ ወገኖችን በገንዘብና በሞራል ለማገዝ በሚል ዓላማ ከ8 አመታት በፊት ሜልበርን በሚገኘው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ የተቋቋመው ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን በየወቅቱ በተለዋወጡ አመራሮቹ አስተባባሪነት የተቁቋመበትን ዓላማ በተገቢው ሲያከናውን ቆይቷል።አሁንም እያከናወነ ይገኛል።

የድጋፍ ቡድናችን ለማንም የፖለቲካም ሆነ የጎሳ ድርጅት ወይም ተቋም ወገናዊነት የሌለውና ዓላማውም ማንንም ከማንም ሳይለይ በየትኛውም መልክ ለዲሞክራሲያዊ ሥርአት ግንባታ የሚደረግን እንቅስቃሴ በሞራልና በገንዘብ ማገዝ ብቻ ነው።

ይህ በእንዲህ እያለ በቅርቡ ማለትም የፊታችን ሜይ 18 በኦታዎ ሁሉን አቀፍ ህብረት ለመመስረት በዝግጅት ላይ የሚገኘው አካል አስተባባሪዎች የድጋፍ ቡድናችንን በህብረት መስራች ጉባኤ አባልነት በተደጋጋሚ ሲጠቅሱ አስተውለናል።

በመሆኑም ሁሉን አቀፍ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴው በአባልነት ከያዛቸው ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት አንዱ ሆነን መገኘታችን ፡የሜልበርን ሕዝብ ከሰጠን ኃላፊነት ውጭ ብቻም ሳይሆን “ለማንምና ለምንም” ወገንተኛ አለመሆን የሚለውን የመተዳደሪያ ደንባችን የሚጥስ ሆኖ አግኝተነዋል።

ይህ ብቻም ሳይሆን ሁሉን አቀፍ ጉባኤው የድጋፍ ቡድናችን አመራሮች እንኳ ሳያውቁት ከአንድ ግለሰብ ጋር በነበረ ግንኙነት ላይ ብቻ ተመስርቶ ድጋፍ ቡድናችንን በአባልነት ይዞ መቆየቱ እጅግ አስገራሚ ሆኖብናል። ይህ መሆኑም የሚመሰረተውን ህብረት ጥንክካሬና በአባልነት አካትቻቸዋለሁ የሚላቸውን ሁሉ በጥርጣሬ እንድንመለከት አድርጎናል።

ይሁንና የድጋፍ ቡድናችን ጥቂቶች በፈጸሙት ስህተት አገር አቀፍ ህብረት ለመመስረት እየደከሙ ያሉትን ወገኖች ጥረት ላለማበላሸት ሲል ከላይ በዝርዝር የገለጽነውን ስህተት እንዲያርሙ፤ ማለትም የድጋፍ ቡድናችንን ከአባል ዝርዝር ውስጥ እንዲያወጡ በመጠየቅ ለጻፈው ደብዳቤ ተገቢ ምላሻ ሊያገኝ አልቻለም።

በመሆኑም ነገ በሚመሰረተው ህብረት ውስጥ ኃላፊነት የሰጠን የሜልበርን ኢትዮጵያዊ በማያውቀው መልክ መስራች አባል ተብሎ ከመጠቀሱ በፊት በዚህ መግለጫ ስህተቱን ለመላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይፋ ለማድረግ ተገደናል።

አሁንም በዚህ መግለጫ ልናሳውቅ የምንሻው

  • 1ኛ የድጋፍ ቡድናችን የህብረት ምስረታው ጉባኤ አባል እንዳልሆነ
  • 2ኛ የድጋፍ ቡድናችንን ወክሎ በጉባኤው የሚሳተፍ ሰው እንደሌለ ነው።

በመጨረሻም ማንንም ከማንም ሳንለይ በተቃዋሚው ጎራ ለተሰለፈው ወገን ሁሉ የምናደርሰው የሞራል ድጋፍና መልካም ምኞት ለሁሉን አቀፍ ጉባኤውም ይድረስ እንላለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

የዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን በሜልበርን ሥራ አመራር ኮሚቴ

ግንቦት 2 -2004 ዓ.ም

About these ads

Posted on May 10, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC and tagged , . Bookmark the permalink. Leave a Comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: