Police brutally beat up and arrest University students

 May 12, 2012
Police brutally beat up and arrest morethan 60 University students in Debremarkos. Read more

ትላንት ለተቃውሞ በወጡ የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የመንግስት ታጣቂዎች በጥይትና በዱላ በወሰዱት እርምጃ ከባድ ጉዳት መድረሱን የአውራምባ ታይምስ ምንጮች ገለፁ፡፡ ባለፈው ዕሁድ የተቀሰቀሰው ዓመጽ መንስኤው በምግብ ጥራት መጓደል ቢሆንም ተቃውሞው ከዚህ አልፎ ፖለቲካዊ መልክ እንደያዘ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዕሁድ ጧት በተቀጣጠለው በዚህ ተቃውሞ አብዛኛው ተማሪ ቁጣውን የዩኒቨርስቲውን መስታወቶች በመሰባበር እንደገለፀ የሚናገሩት ምንጮቻችን ምሽት ላይ በድንገት ወደ ግቢው የገቡት ታጣቂዎች ተማሪዎቹ ላይ ከመጠን ያለፈ ኃይል በመጠቀም ጉዳት እንዳደረሱ ገልፀዋል፡፡ በወቅቱ በታጣቂዎች በተወሰደው እርምጃ ከ60 ያላነሱ ተማሪዎች መታሰራቸውና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ላይ ድብደባ እንደተፈጸመ ስሙን መግለጽ ያልፈለገ ተማሪ ለአውራምባ ታይምስ ገልጾአል፡፡ ተማሪው በወቅቱ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ከፍተኛ የተኩስ እሩምታ እንደነበረና በዚህ እርምጃም አብዱራህማን መሀመድ የተባለ ተማሪ በጥይት ተመትቶ መውደቁን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጾአል፡፡ ተማሪው በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት በደብረ ማርቆስ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ በመከታተል ላይ እንደሚገኝና ሀኪሞች ለሚዲያ ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰጡ ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል፡፡ ባለፈው ሰኞም ከጠዋት ጀምሮ ‹‹የታሰሩ ተማሪዎች ይፈቱ›› የሚል ጥያቄን ይዞ የቀጠለው ተቃውሞ ቀስ በቀስ ከዩኒቨርሲቲው ውጪ መስፋፋቱን ከከተማው ያገኘናቸው መረጃዎች አመላክተዋል፡፡ ተቃውሞው በደብረ ማርቆስ ከተማ ጎዳናዎች ላይ በቀጠለበት ወቅት በርካታ የከተማው ነዋሪዎችም ትዕይንቱን ተቀላቅለው ጥያቄው ወደ ፖለቲካዊ ተቃውሞ መሸጋገሩን የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ በዚሁ እርምጃ ኦፕራሲዮን የተደረጉ ተማሪዎች እንደሚገኙና ይህንኑ ተከትሎ በደብረማርቆስ ከተማ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን የሚገልጹት እነዚህ የአይን እማኞች መንግስት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ቢያስተላልፉም አብዛኛው ተማሪ እስካሁን ትምህርት እንዳልጀመረ ለመረዳት ተችሏል፡፡

About these ads

Posted on May 12, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a Comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: