Daily Archives: June 3, 2012

የኑሮ ውድነት — “የግንቦት 20 ፍሬ”

6/3/12

የፖለቲካ ተቃውሞ ከተማ ያቆሽሻል ! (ፑቲን)
ወዳጆቼ … የግንቦት 20 ሃያ አንደኛ ዓመት የድል በዓል እንዴት ነበር? እኔ ከሁሉም የተመቸኝ ቴሌኮም በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለደንበኞቹ ያደረገው የአጭር መልዕክት (ቴክስት ሜሴጅ) ታሪፍ ቅናሽ (ዲስካውንት) ነው፡፡ የገባው ነጋዴ እኮ ነው! ምናለ እንደቴሌኮም ዓይነት አንድ ሁለት ቢኖረን፡፡ እኔ የምለው… አገር ውስጥ ገቢ ለታክስ ከፋይ ዜጎች ማበረታቻ ወይም ሆሊዴይ ታክስ አሊያም የሆነ የታክስ ዲስካውንት ነገር የለውም እንዴ? (ግብር አይደለም እዳ… ብቻ ምን ይሰራል?) በግንቦት 20 (ቢያንስ በዓመት አንዴ) እንዲቀንስልን የምንፈልገው ብዙ ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ፋሲካ ከ90 ብር ተተኩሶ 120 ብር ላይ ቂብ ብሎ የቀረው ጥሬ ስጋ በግማሽ ዋጋ ቢቀንስልን እንመርቀው ነበር – ዘላለም እንዲነግስ! በእርግጥ መንግስት አቅም ላይኖረው ይችላል (ከየት ያመጣል?) እነ IMF እና ዎርልድ ባንክ ግን ሊያግዙን ሊደጉሙን ይችላሉ … የአሁኑማ አለፋ… ለመጪው ካሁኑ ይታሰብበት! ከምሬ ነው … በግንቦት 20 ሽሮ መብላት ሙድ ያበላሻል፡፡ (እንዴ ቤቱ በዓል በዓል ሳይሸት?) እኔ የምለው ግን …የኑሮ ወድነቱ ላይ ዲስካውንት የሚደረግልን መቼ ነው? ይኸው ተስፋ የጣልንበትም ቀን እኮ አለፈ! (ግንቦት 20!) Read the rest of this entry

የኢትዮጵያ ሠራዊት በኤርትራ ጦር ላይ ጥቃት ፈጸመ

Sunday, 03 June 2012 00:00
By a Staff Reporter
        Hits: 1423 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባለፈው ሳምንት ኤርትራ የነፃነት ቀኗን ስታከብር በነበረበት ዕለት፣ ባድመ በሚገኘው የኤርትራ ጦር ላይ ጥቃት ማድረሱን ወታደራዊ ምንጮች ገለጹ፡፡  ጥቃቱ በትግራይ አካባቢ በቅርቡ በኤርትራ ጦር ታፍነው ለተወሰዱ ኢትዮጵያውያን አጸፋዊ ምላሽ ነው ተብሏል፡፡ Read the rest of this entry

ጥሩነሽ ዲባባ በኦሎምፒክ የሚያሳትፋትን ሰአት ከአስደናቂ ብቃት ጋር አስመዘገበች (ከፍሰሃ ተገኝ)

Published On: Sat, Jun 2nd, 2012
 
 
(ከፍሰሃ ተገኝ –የቀድሞው የኤፍኤም አዲስ ስፖርት አዘጋጅ) ድንቋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አሜሪካ ዩጂን ውስጥ በተካሄደው የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር አንደኛ በመውጣት
አሸንፋ በለንደን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በርቀቱ የሚወክሉት ሴት አትሌቶች መሀል አንዷ መሆኗን አረጋግጣለች። 5 ሺህ ሜትር ያህል ርቀት እንደሮጠች መሪነቱን የያዘችው ጥሩነሽ ርቀቱን ሮጣ ለመጨረስ 30 ደቂቃ ከ24.39 ሰከንድ የሆነ ጊዜ የወሰደባት ሲሆን ሰአቱም የአመቱ ፈጣን ሆኖ ተመዝግቧል። ኬኒያዊቷ ፍሎረንስ ኪፕላጋት ሁለተኛ ስትወጣ፤ Read the rest of this entry

አንገት ሲደፋ ምን ፈሰሰ?

Published On: Sun, Jun 3rd, 2012

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

ሰሞኑን አዲስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶግራፍ በብዛት በያለበት ይታይ ነበር፤ ያዘነ፣ የተከዘና አንገቱን የደፋ መለስ ዜናዊ! እኔን ቀልቤን የሳበው የጠቅላይ ሚኒስትሩን አንገት ሊያስደፋ የቻለው ነገር አይደለም፤ ወይም አበበ ገላው የተናገረው ነገር አይደለም፤ አበበ ገላው የተናገረውን ለመናገር ሙሉ መብት አለው፤ በተባለው ነገር የማይስማማ ሰው በማስረጃም ሆነ ያለማስረጃ የተባለውን ለማስተባበል መሞከር መብቱ ነው፤ የአሜሪካኑን ፕሬዚዳንት፣ ወይም የእንግሊዙን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲህ ያለ ሁኔታ ቢያጋጥማቸው፣ ወይም በጆርጅ ቡሽ ላይ አንዱ ኢራቃዊ እንዳደረገው ጫማውን እያወለቀ ቢወረውርም ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይኖርም፤ በ1928 ነው 29 አጼ ኃይለ ሥላሴ በቀድሞ የዓለም መንግሥታት ማኅበር መድረክ ላይ ሲናገሩ የኢጣሊያ ፋሺስቶች ያሰማሩአቸው ሰዎች ንግግሩን ለማደናቀፍ ጩኸትና ፉጨት ያሰሙ ነበረ፤ አጼ ኃይለ ሥላሴን አንገታቸውን አላስደፋቸውም፤ አበበ ገላው የወረወራቸው ቃላት ናቸው፤ ቃላቱ እውነትን የሚገልጹ ከሆነ በተግባራዊ ማረሚያ ይለወጣሉ፤ ቃላቱ ሐሰትን የሚገልጹ ከሆኑ እውነትን በሚገልጹ ቃላት ይደመሰሳሉ።

    አንገት ሲደፋ ምን ፈሰሰ?

  Mesfin Woldemariam (Prof.)

 እዚህ ላይ አንድ ሌላ ነገር እናስታውስ፤ በመስከረም ግድም  ይመስለኛል አቶ ኢሳይያስ አፈወርቅ በኒውዮርክ ነበረ፤ በዚያን ጊዜ በአንድ ስቴድየም ውስጥ የኤርትራ ተወላጆች ሁሉ (የቀረም ያለ አይመስልም!) በስቴድየሙ ታምቀው የኢሳያስን ዲስኩር ከሰሙ በኋላ አስተያየታቸውን እየሰጡና ጥያቄያቸውንም እየጠየቁ ሲወያዩ ነበር፤ ያስቀኑ ነበር፤ የኤርትራም ማኅበረሰብ እንደኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ውስብስብና ጉራማይሌ ነው፤ መሪው ህዝቡን ሳይፈራ፤ ሕዝቡም መሪን ሳይፈራ ተቀራርበው ለመወያየት መቻላቸው እኛን የትና የት ጥለውን እንደሄዱ አያሳይም የሚል አለ? ይህንን እውነት ቢያንስ የዛሬ አሥራ አምስት ዓመት ግድም ሪፖርተር የመጀመሪያውን መጽሔት ባወጣ ጊዜ ሽፋኑ የኢሳይያስ አፈወርቅ ፎቶግራፍ ነበር፤ Read the rest of this entry

%d bloggers like this: