Daily Archives: June 5, 2012

የ‹‹አራት ኪሎው›› እና ‹‹የቃሊቲው መንግስት›› ወግ

Tuesday, June 5, 2012
  • ሁሉም እንስሳት እኩል ናቸው፤ አንዳንድ እንሰሳት ከሌሎቹ ይበልጥ እኩል ናቸው

ተመስገን ደሳለኝ ሲሳይ አጌና በቅርቡ በመጀመሪያ በጀርመን፣ ቀጥሎ በአሜሪካን ሀገር ‹‹የቃሊቲው መንግስት›› የሚል ርዕስ ያለው መፅሐፍ አሳትሟል። በእርግጥ መፅሐፉ እስከአሁን ሀገር ቤት መግባት አልቻለም (ምናልባት ወደፊትም ላይገባ ይችላል)
ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በኢትዮጵያ የነፃ ፕሬስ ታሪክ የጎላ አሻራ ካላቸው ጥቂት ጉምቱ እና ትንታግ ጋዜጠኞች አንዱ ነው። ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ በድህረ ምርጫ 97 በተነሳው አለመግባባት ስራ እስካቆመበት ዕለት ድረስ ‹‹ኢትኦጵ›› እና ‹‹አባይ›› የተባሉ ጋዜጦችን በባለቤትነት ይመራ ነበር። በተለይ ኢትኦጵ ጋዜጣ በእጅጉ ተወዳጅ ከመሆኗም ባሻግር በስርጭትም ግንባር ቀደም እንደነበረች ይታወሳል። Read the rest of this entry

አቶ ሽንኩ ከፍያለውና አቶ ዳኛቸው አያሌው የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው ከተገደሉ በኋላ አስከሬናቸው መሬት ለመሬት ሲጐተት ውሏል”

Street scene in Gondar

Street scene in Gondar (Photo credit: ollybenson)

Tuesday, June 5, 2012

በጐንደር ፖሊስ የሟቾችን አስክሬን በመኪና መሬት ለመሬት አስጐተተ ::

 - ከቀኑ 11 ሰዓት እስከ ንጋቱ ተዘቅዝቀው ዛፍ ላይ ተሰቅለው ነበር
- ቤተክርስቲያን አይቀበሩም ተብለው ሜዳ ላይ ተቀብረዋል
- የአካባቢው ህብረተሰብ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሮበታል
- በጐንደር ተቃዋሚዎች እየታሰሩ ነው
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ጐንደር ዞን ታች አርማጭሆ ሳንጃ ከተማ በተኩስ ልውውጥ የተገደሉ ሁለት ሰዎች አስከሬን በመኪና ላይ ታስረው ከተማ ውስጥ መሬት ለመሬት መጐተቱን ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡
ምንጮቻችን እንደሚሉት “አቶ ሽንኩ ከፍያለውና አቶ ዳኛቸው አያሌው የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው ከተገደሉ በኋላ አስከሬናቸው መሬት ለመሬት ሲጐተት ውሏል” ብለዋል፡፡
ምንጮች እንደሚሉት “አቶ ዳኛቸው አያሌው ከአንድ ግለሰብ ጋር በመጋጨቱ አካባቢውን ለቆ ሄዷል፡፡ ከመንግስት ጋር ፀብ አልነበረውም፡፡ Read the rest of this entry

በቤንች ማጂ ዞን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገደሉ

Tuesday, June 5, 2012
ግጭቱ አሁንም አልበረደም By Finote Netsanet news no. second year, no.45

በቤንች ማጂ ዞን ሜኒኑ፣ ጉልዲያ፣ ሜኒትሻሻ፣ ቤሮ፣ እሹርማ እና በኮይ ወረዳዎች ለወራት የቀጠለው ግጭት ዳግም ማገርሸቱን የአካባቢው ምንጮች ጠቆሙ፡፡
በተለይ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት በጥምረት በሚቆጣጠሯቸው ኮይ እና ቤሮ ሻሻ አካባቢዎች ከፍተኛ የፀጥታ ችግር እንዳለ የሚናገሩት ምንጮቻችን ግጭቱ ያገረሸው ግንቦት 12 ቀን 2004 ዓ.ም በአካባቢው ቢራ እና ለስላሳ የሚያከፋፍሉ አቶ አብርሃም የተባሉ ግለሰብ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱት ታጣቃዎች መገደላቸውን ተከትሎ እንደሆነ ዘግበዋል፡፡
ፍኖተ ነፃነት ያነጋገረቻቸው አንድ የዞኑ ባለስልጣን በአካባቢው አሳሳቢ የሆነ የፀጥታ ችግር እንዳለ አምነው፣ ችግሩ ከአራት ወራት በላይ እንዳስቆጠረ ተናግረዋል፡፡ እኚሁ የዞኑ ባለስልጣን ጨምረው እንደ ገደለፁት ካለፉት አራት ወራት ወዲህ መኪናዎች ወደ ተለያዩ የወረዳ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ በመንግስት ታጣቂዎች እንደሚታጀቡ አብራርተዋል፡፡ Read the rest of this entry
%d bloggers like this: