የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የያዘ አውሮፕላን የቴክኒክ ችግር ገጠመው

 

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 917 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድንን ይዞ ወደ ቤኒን ትላንት ሰኔ 8፣ 2004 ዓም የሁለት ሰዓታት ጉዞ ካደረገ በኃላ በአውሮፕላን የቴክኒክ ችግር ምክንያት ተመልሶ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ለማረፍ መገደዱን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡

የእግር ኳስ ቡድኑ በነገው ዕለት ለ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከቤኒን ብሔራዊ ቡድን ጋር ላለበት ጨዋታ በረራ የጀመረው ትላንት ከጠዋቱ 4፡45 ላይ ነበር፡፡ አብራሪው የቴክኒክ ችግር እንደገጠመው ሲያውቅ ለተጨዋቾቹ ሳያሳውቅ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ መወሰኑን ምንጫችን ጠቁሞ በዚህ ምክንያት በቡድኑ አባላት ላይ መደናገጥ ወይም የሥነልቦና ችግር አልተከሰተም ብሏል፡፡

የበረራ ቁጥር 917 አዲስ አበባ ከተመለሰ በኃላ ጥገና ተደርጎለት ይኽው አውሮፕላን ከቀኑ 11፡05 ከአዲስ አበባ በድጋሚ ተነስቶ ቤኒን ከምሸቱ 4፡45 ላይ መድረሱን ምንጫችን ጨምሮ ገልጿል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በነገው ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 10፡00 ላይ ከቤኒን ብሔራዊ ቡድን ጋር ጨዋታውን ያካሄዳል፡፡

የኢትዮጽያ አየር መንገድ ወደ ቤኒን በረራ ሲያደርግ ትላንት የመጀመሪያው እንደነበርም ታውቋል፡፡ ቡድኑ ባለፈው ሳምንት በ2014 ብራዚል ለምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሴንትራል ሪፐብሊክ አፍሪካ ጋር በአዲስአበባ ስታዲየም ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 0 መርታቱ ያታወሳል፡፡ቡድኑ ቀደም ሲል ከደቡብ አፍሪካ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1 ለ 1 በመለያየት ካገኘው ነጥብ ጋር ተደምሮ ምድብ አንድን በአራት ነጥብ እየመራ ይገኛል፡፡

About these ads

Posted on June 16, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC and tagged . Bookmark the permalink. Leave a Comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: