Daily Archives: July 11, 2012
የስርአት ለውጥ መፈለግ ቅፅበታዊ ውሳኔ አይደለም!
ያለምገነት አላምረው
የወታደራዊው ስርአት ከተወገደ በሁዋላ የህዝብን ስልጣን በጠመንጃ አስፈራርቶና ዋሽቶ የወሰደው ውጥንቅጡ የጠፋበት ወያኔ መንግስት 21ኛ የጭቆናና የብዝበዛ አመቱን ወደፍፁም አምባገነንነት ተሸጋግሮ አከበረ ፡፡ የአቶ መለስ አገዛዝ የኢትዮጵያውያንን ህዝብ ትግል ውጤት( እነሱ የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው የታገለው ቢሉም) ተጠቅሞ ስልጣን ከጨበጠ ጊዜ ጀምሮ ከዕለት ዕለት ወደ ፍፁማዊ አንባገነንት በመሽጋገር ላይ ይገኛል:: Read the rest of this entry
የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በዝናብ ተጥለቀለቀ
Tags
ከፍተኛ ወጭ ተመድቦለት ግንባታውም በዚህ አመት የተጠናቀቀው እና ምርቃቱም በታላላቅ የአፍሪካ መሪዎች ባሉበት ተመርቆ በስራ ላይ የዋለው የአፍሪካ ህብረት ማእከል በትላንትናው እለት ምሽት በጣለው ከፍተኛ ዶፍ ዝናብ የህብረቱ አዳራሽ መጥለቅለቁ የደረሰን ዜና ዘገባ ያመለክታል ። ከ$200፣000 የአሜሪካን ዶላር ያወጣው እና የቀድሞውን ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘ-ኢትዮጵያ መሰረታዊ ታሪክ ያጠፋ ከመሆኑም በላይ በመታሰቢያነት ከታሰበ ሊሰራላቸው ከሚገባቸው የሚገባው ሰዎች መካከል ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ፣የኬንያው ጆሞ ኬኝያታ እና የግብጹ ጋማል አብዱል ናስር መሆን ሲገባቸው በምትኩ የአፍሪካ የአንድነት ታጋይ ተብለው የተሰየሙት“ በአፍሪካ አንድነት ከፍተኛ ትግል ላደረጉት በዶ/ር ክዋሚ ኑክሩማህ” ስም ሃውልት ተሰርቶ መታሰቢያ እንዲሆነላቸው የተደረገው ይሄው ሃውልት በቻይናውያን ትብብር ተሰርቶ መጠናቀቁን ባለፈው ጃንዋሪ 28 ቀን 2012 የቻይናው የፖለቲካ አድቫይሰር ጂያ ቂንጊል በተገኙበት ተመርቆ ለስራ መብቃቱ ይታወሳል :: Read the rest of this entry
ምን ያህል የዲግሪ ምሩቃን የኮብልስቶን ሰራተኞች?
“ኢትዮጲያ በበሬ ጠምዶ የሚያርስ አላጣችም መሪ እንጂ,,
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተምረው ዘንድሮ የሚመረቁ ተማሪዎች የመመረቂያ ልብስ (ጋውን) ለመውሰድ ሰሞኑን በግቢው ውስጥ ውር ውር ሲሉ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ተመራቂዎች በራሳቸው ላይ ጣል የሚያደርጉት ቀልድ መረር ያለ ነው፡፡ “እንኳን ወደ ስራ ፈትነት አለም ተቀላቀልክ” “እንግሊዝኛ ተናጋሪ ኮብልስቶን ሰራተኛ” ወዘተ ዓይነት ወትሮ ያልተለመደ በራስ ላይ ቀልድ የበዛ ይመስላል – በዩኒቨርስቲው ግቢ፡፡ ለነገሩ እንዲህ ያለው ቀልድ የተጀመረው በቅርቡ ነው – በኢቴቪ፡፡ በድግሪና በዲፕሎም እንዲሁም በማስተርስ ደረጃ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከዩኒቨርስቲዎች የተመረቁ ተማሪዎች ከመንግስት ስራ ጠባቂዎች ሳይሆኑ በኮብልስቶንና በእርሻ ስራ እንደተሰማሩ የሚያሳዩ ፕሮግራሞች በቲቪ መስኮት እየቀረቡ ነው፡፡በእርግጥ አንድ ሰው በዓለም ላይ የመጨረሻውን ከፍተኛ ትምህርት ተምሮም ኮብልስቶን አነጥፋለሁ ካለ መብቱ ነው የግድ በተማርክበት ትልቅ የትምህርት ዘርፍ መስራት አለብህ ተብሎ ግዳጅ አይጣልበትም፡፡Read the rest of this entry
ኃይሌ ገብረስላሴ ኤርትራ ኤንባሲ ምን ይሰራል!?
ኃይሌ ገብረስላሴ ኤርትራ ኤንባሲ ምን ይሰራል!?
ትላንት ሐምሌ 2/ 2004 ዓ.ም ታዋቂው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ኬኒያ በሚገኘው ኤርትራ ኤንባሲ መታየቱን ናይሮቢ የሚገኙ ኤርትራዊ ወዳጆቼ ነገሩኝ። ኃይሌ ገብረስላሴ ኤርትራ ኤንባሲ ምን ይሰራል!?
በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት የጭምጭምታ ወሬዎችን መናቅ አይገባም። ከዚህ በፊት ራሱ ኃይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ ሌሎችም ራሳቸውን “ሽማግሌ” ብለው የሚጠሩ ግለሰቦች ተሰባስበው በቃሊቲው እስር ቤት ሲመላለሱ ነበር። የሚል ጭምጭምታ በሰማን በማግስቱ ነው ነገሩ ሽምግልና መሆኑ የተሰማው። ማን ያውቃል አሁንም ኃይሌ ኤርትራ ኤንባሲ በታየ በነጋታው አቶ ኢሳያስ እና አቶ መለስ ሊሸማገሉ ነው የሚል ዜና እንሰማ ይሆናል። Read the rest of this entry



![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)




![934090_653692987990685_304344173_n[1] 934090_653692987990685_304344173_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8419/8907424400_e66413b735_m.jpg)
![969200_505600652838946_443296293_n[1] 969200_505600652838946_443296293_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8263/8906754167_0a2bacfe7d_m.jpg)