Daily Archives: July 18, 2012

አቶ መለስ መግለጫ ተሰረዘ

meles_zenawi3አቶ መለስ ዜናዊ በከፍተኛ ሕመም ላይ መሆናቸውን ሲደብቅ የቆየው የኢትዮጵያ መንግስት ከሰሞኑ በምክትል ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካኝነት “አቶ መለስ ህመማቸው የሚያሰጋ አይደለም፤ በጥቂት ጊዜያት ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ” የሚል መግለጫ መሰጠቱ ይታወሳል። ትናንት የመንግስት ባለስልጣናት አቶ መለስ ዜናዊ ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጡ የተገለጸ ቢሆንም መግለጫው ተሰርዟል። እንደ ኤ.ፍ.ፒ(AFP),Yahoonews ያሉ የውጭ ሃገር ሚዲያዎች ሳይቀር መለስ በአስጊ ሁኔታ ላይ በብላስልስ እንዳሉ በመዘገብ ላይ ናቸው። Read the rest of this entry

የሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ በፌዴራል ፖሊስ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ምንጮቻችን ገለፁ።

የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ መሐሙድ በወረዳ 17 ወርቁ ሕንፃ አጠገብ ከሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ የሃይማኖት አታሼ ቢሮ ግምቱ ከሃምሳ እስከ መቶ ሺ ብር የሚገመት የታሰረ ገንዘብ እና በዓረብኛ የተፃፉ መፅሐፍት ይዘው ሲወጡ በፌዴራል ፖሊስ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ምንጮቻችን ገለፁ። Read the rest of this entry

የማለዳ ወግ . . . ድጋፍ በዝምታ የተገለጸበት በጅዳና የተለያዩ አረብ ሃገራት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ክራሞት !

 በአንዋር አዎሊያ ቅጽር ግቢ በመሰባሰብ በመንግስት አካሄድ ላይ ቅሬታቸውን በማሰማት” ህገ መንግታዊ መብታቸን ይከበር !” ሲሉ ለስድስት ወራት ድምጻቸውን ያሰሙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ካሳልፍነው ሳምንት መጨረሻ ወዲህ ከረር እይለ የመጣ ይመስላል፡፡ እዚህ እኔ በምኖርበት ጅዳም እየተጋጋለ የመጣው ሁኔታ  ያሳሰባቸው ወዳጆቸና በየአጋጣሚው እያገኘሁ ያነጋገርኳቸው ነዋሪዎች አጫውተውኛል፡፡ ባሳለፍነው እሁድ በጅዳ ኮሚኒቲ አዳራሽ ያየነው የአዎልያ በሚሰበሰቡ ምዕመናን ላይ የተሰነዘረውን እርምጃ በማውገዝና ኮሚቴዎች የተደገፉበት ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ በዚሁ ወቅት ከሶስት መቶ በሚበልጡት: …. Read the rest of this entry

የመብት ጥያቄያችንን እስከ ፍጻሜው ለስኬት ለማብቃት መታገል ግድ ይለናል!

 

 

 

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ዉድ ሙስሊም ወገኖች! እንደምንናችሁ!? አልሀምዱሊላህ ሁላችንም ሰላም ነን፡፡ እናንተስ? የሰላማዊና ህገ መንግሥታዊ መብት የማስከበር እንቅስቃሴያችን እስከዚህ ደርሷል፡፡ ሰሞኑን እያንዣበቡ ያሉት ሂደቶች፣ የመንግሥት ሚዲያ አቀራረብና የምንሰማቸው መረጃዎች ሂደቱ ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊሸጋገር የተቃረበ ይመስላል፡፡ ሕዝባችንም ስለኛ ደህንነት በስጋት ተዉጦ ይከተላል፡፡ ይህም ኮሚቴውንና ንቁ ተሳታፊዎችን በመወንጀል የመክሰስና የማሰር ቀጣይ እርምጃ ሊከተል መሆኑን ያሳያ…ል፡፡ መብት በማሰከበር ትግል ዉስጥ ይህ ከጥንት ጀምሮ ሊከሰት የሚችል እና ስንጠብቀው የነበረ ነው፡፡ የህዝባችንን ወኔና ቆራጥነትን ስንመለከት 17ቱ ኮሚቴዎች ብንታሰር ሕዝቡ ለሌሎች 34 ኮሚቴዎችን መርጦ ትግሉን ይቀጥላል ብለን ነው የምናምነው፡፡ 34ቱ ቢታሰሩ ሕዝቡ 68 ሌሎች መሪዎችን መርጦ ትግሉን ይቀጥላል፡፡ ትግሉ እንዲሁ ይቀጥላል…፤ በትግል ሂደት የመጀመሪያ መሪዎች ሊጠቁ. ሊሰናከሉና ሊታሰሩ ይችላሉ፡፡ Read the rest of this entry

አንድ ብስጭት፤ ኢቲቪ ሀይማኖቱ ምንድነው!?

እስቲ ቆይ ወደ ርዕሰ ጉዳያችን ከማምራታችን በፊት አንድ ዋዛ ብጤ እናምጣ አሁን በቅርቡ አንድ ወዳጄ አንድ ፈታኝ ጥያቄ ጠይቆኝ ነበር። ምን አለኝ መሰልዎ “አቶ መለስ እና ኢቲቪ ተጣልተዋል እንዴ!?” አለኝ ሲቀጥልም፤ “ያኔ ጋሽ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ገና ትንሽ ሲወራባቸው “ፕሬዘዳንቱ በህክምና ላይ ናቸው አትደናገጡ!” ብሎ የነገረን ቴሌቪዥናችን ዛሬ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጊዜ ዝም ማለቱ ምን ቢያስቀይሙት ነው!?”  ብሎኛል። Read the rest of this entry

መለስ ላልተወሰነ ጊዜ ስራ አይጀምሩም፤ ግርማ ብሩ፣ ሥዩም መስፍንና በረከት ስምኦን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጎብኝተው ተመልሰዋል

በ21 ዓመታት የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በጤንነት ችግር በ19ኛው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ ያልተሳተፉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸው ተሰማ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ የውጭ ሕክምና ክትትላቸውን ጨርሰው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱም ምንጮች ገልጸዋል፡፡

Azeb Mesfin, wife of Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi, leaves the venue of general assembly, Organization of African First Lady against HIV/AIDS meeting,on July 16,2012 during the 19th African Union summit in Addis Ababa. (Photo Getty Images) Read the rest of this entry

%d bloggers like this: