Daily Archives: August 1, 2012
ከመለስ ሞት በኋላ በወያኔዎች አካባቢ እየተሰሙ ያሉ የውጭ ጉዳይ ዜናዎች
በሙሉነህ ዮሃንስና የውጭ
ጉዳይ ምንጮች የተጠናከረ (ጁላይ 31 2012)
አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ መለስን
ሲያስታምም ከርሞ ከብራስልስ ወደ አዲስ አበባ
እየተመለሰ ነው!
አምባሳደር ሙሉጌታ አለምሰገድ ባጣዳፊ ቤተሰቡን
ወደ ጣሊያን አሸሸ!
አሜሪካን ሃገር በአምባሳደርነት ማእረግ ያሉ አራት
ዲፕሎማቶች ከአበበ ገላው ጋር በተያያዘ ጠቅልለው
እንዲመለሱ ታዘዙ!
መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብና የባለስልጣናት
ቤተሰቦች ወደ ኬንያ እየተሸጋገሩ ነው! Read the rest of this entry
Meles Zenawi: Ethiopian leader ‘getting better’

“አቶ መለስ አንድ ነገር ቢሆን ኢህአዴግ ችግር ይገጥመዋል” – ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀድሞው ፕሬዚዳንት
(ሰንደቅ ጋዜጣ)የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት እና በአሁኑ ወቅት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አሁን በሥራ ላይ ያለውን ሕገመንግሥት ካረቀቁት ምሁራን መካከል አንጋፋው መሆናቸው ይታወቃል። ከጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ መታመም በኋላ እየተነሱ ባሉ ሕገመንግሥታዊ ጥያቄዎችና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ፍሬው አበበ በቢሮአቸው ተገኝቶ አነጋግሯቸዋል። Read the rest of this entry
የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳት ከ17 ወራት እስራት በኋላ በነፃ ተለቀቁ
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ምክትል ፕሬዚዳት ዶ/ር ታዴዎስ ቦጋለ ድርጅቱ እንዳይጠቀምበት በተከለከለ ክብ ማህተም ተጠቅመዋል በሚል ተከሰው አንድ ዓመት ከስምንት ወራት ጽኑ እስራ ተፈርዶባቸው ለ17 ወራት ከታሰሩ በኋላ ሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም. በነፃ ተለቀቁ፡፡
ዶ/ር ታዴዎስ ለቅጣት የበቁበት ምክንያት፣ የመኢአድ ገንዘብ ያዥና የመዝገብ ቤት ኃላፊ የነበሩትን አቶ ግርማ ነጋ፣ የድርጅቱን ማህተም ቆልፈውበት ከአዲስ አበባ ውጪ ይሄዳሉ፡፡ በወቅቱ ማህተሙን ለሥራ የፈለጉት የድርጅቱ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል ወደ አቶ ግርማ ሲደውሉ፣ አቶ ግርማ ሊመጡ ባለመቻላቸው ለምርጫ ቦርድ ብቻ (ለድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚዎች ሳያሳውቁ) አሳውቀው አዲስ ማህተም በማስቀረፅ፣ ከጥር 7 ቀን 2003 ዓ.ም በኋላ የበፊቱ ማህተም በሥራ ላይ እንዳይውል ያደርጋሉ፡፡ በመቀጠልም ጥር 15 ቀን 2003 ዓ.ም በድርጅቱ መግቢያ በር ላይ ‹‹ስብሰባ ማድረግ ክልክል ነው›› በማለት በአዲሱ ማህተም ተጠቅመው ማስታወቂያ ይለጥፋሉ፡፡ Read the rest of this entry
![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)