ቢረፍድም ዛሬ መጀመር አለበት !!!ከ- አብዶ ኑር የሱፍ – ኖርዌይ ኢሜይል- abnuye2001@gmail.com
ኧረ በህግ አምላከ እንዳንል በዳይም ፣ከሳሽም ፣ህግ-አውጭም፣ህግ-አስትረጓሚም እና ህግ- አስፈጻሚም አንድ አካል ሆነብን ፡፡ ወዴት እንተንፍሰው ? ለማን አቤት እንበል ? ወያኔ ለ21 አመታት ሀገር በማፍረስ እና በዘር ማጥፋት ተግባር ላይ በማን አለብኝነት መንፈስ እስከዛሬ ተሰማርቶ ቆይቷል ። በሌላ በኩል ሀገረ ወዳድ የሆኑ ንጹሃን ኢትዮጵያዊያኖችን እያሸማቀቀ ፣ እያሳደደ ፣ እየገደለ ብሎም የአሸባሪነት ታርጋ እየለጠፈ ወደ ዘብጥያ በመወርወር ኢትዮጵያ ሀገራችንን በተለመደው ዉሸቱ እና በጉልበቱ የስልጣን ጥማቱን ለማርካት ሲባዝን ይታያል ፡፡ የወያኔ አምባገነናዊ መንግስት በዉሸት የተካነ ፣አፋኝ ፣ገዳይ፣እውነት የሚያሰፈራው እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት እና የታሪክ ጠላት መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው ። የወያኔ አምባገነናዊ መንግስት ሰፊውን የኢትዮጵያ ህዝብ ዐይንህን ጨፍን እያለ ለማታለል የሚሞክርባቸው ትእይንቶች የኢትዮጵያን ህዝብ አንጀት ከማሳረር አልፎ በተደራጀ የማፊያ ቡደን መመራታችን አንገታችንን ካስደፋን ድፍን 21 አመታት አለፉን፡፡ ውድ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ ይህ የማፊያ ቡድን ለረጅም አመታት በከፋፍለህ ግዛው መርህ ሲያሰቃየን የኖረው በወያኔ ጥንካሬ ወይስ በእኛ ደካማነት ? ለዚህ መልስ በወያኔ ጥንካሬ እንደማትሉኝ ግልጽ ነው፡፡ ይህ ውሸትን ሃይማኖቱ ያደረገው የወያኔ አምባገነናዊ ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ ከስርአቱ የጭቆና ቀንበር እንዳይወጣ እና እኔ አውቅልሀለሁ እያሉ በሚመሩት የውሸት እና የጨለማ መንገድ ብቻ እንዲጓዝ በሚያደርጉት ጥረት ለስርአቱ ታማኝ የሆኑ ፣ ሆዳቸውን የመረጡ በጊዜው አጠራር ሆድ አደሮች እና ወደ ነፈሰበት የሚነፍሱ ግለሰቦችን በመጠቀም ሀገር ማፈራረሱን ፣ የሀገር ወዳድነት ሰሜት ማቀዝቀዙን ፣ የዜጎችን ስነ- ልቦና መስለቡን እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት እና ታሪክ ጠላት መሆናቸውን ቀጥለውበታል ፡፡ ወያኔ ጭፍራዎቹን እና አሽከሮቹን በተለያየ ጥቅማ ጥቅም በማሰር እና የአጃቢዎቹን ቁጥር በማብዛት የሚከተለውን አምባገነናዊ አመራር ህዝባዊ ለማስመሰል ፣ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም የበሰበሰ የፖለቲካ መርዙን ለሰፊው ህዝብ ለማዳረስ እና ህዝቡ ማንኛውንም አይነት የመብት ጥያቄዎችን እንዳይነሳ ከማድረጉ በተጨማሪ ገና ከጅምሩ የሃይማኖት ተቛማቶችን እና አባቶችን በመዳፋቸው ውሰጥ በማስገባት የፖለቲካ መጠቀሚያ ሲያድረግ የነበረው የወያኔ መንግስት አሁንም ይህንኑ ተግባር ዋና ስራው አድርጎ ቀጥሎበታል ፡፡ ይህ እርኩስ መንፈስ የተጠናወተው የወያኔ ቡደን እራሱ ያስቀመጣቸው የእምነት አባቶችን በመጠቀም ሃይማኖቱን የሚያከብረውን እና የሚወደውን የኢትዮጵያን ህዝበ ክርስቲያን እና የሙስሊሙን ማህብረሰብ በቁጥጥሩ ስር በማዋል የኢትዮጵያ ሀገራችንን ታሪክ ማቆሸሽ ብሎም የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ከሚያደርገው መፍጨርጨር በተጨማሪ ወደፊት በቤተ-እምነቶች እና የሃይማኖት አባቶች ላይ ጥቁር አሻራ ጥሎ ለማለፍ እንዲሁም ለእምነት አባቶቻችን ክብር እንዳይኖረን ለማድረግ የሚሰራውን ደባ እኛ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች እጅለእጅ ተያይዘን የሃይማኖታችን ብሎም የምንወዳት እናት ሀገራችን ጠላት የሆነውን ወያኔን በቃህ የምንልበት ጊዜ ቢረፍድም ዛሬ መጀመር አለበት ፡፡ የተነቃበት የወያኔ ሃይማኖትን የመከፋፈል ቁማር ለይስሙላ በተቀመጠው ህገ-መንግስት ላይ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ቢባልም ህጉ-መንግሰቱ እንደ እነ መለስ ዜናዊ እና ሕወሓት ፍላጎት የሚሻር ስለሆነ እጃቸውን በሃይማኖት ዉስጥ ጣልቃ በማስገባት ከዚህ በፊት የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያዊያንን ለመከፋፈል በጠነሰሱዋቸው ሴራዎች ምክንያት እንዳንቀራረብ እና የጋራ ችግሮቻችንን በጋራ መፍታት እዳንችል አድረጎ በማስቀመጥ ሀገር የማፍረስ ስራውን በማን አለበኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ከዚህ ቀደም የወያኔ አምባገነናዊ መንግስት የፖለቲካ ኪሳራ ወይም የፖለቲካ ትኩሳት ሲያጋጠመው የህዝቡን ሀሳብ ለማሰቀየር እና ትኩረት ለመሳብ ከሚጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ የነበረው የክርስትና እና እስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን ማጋጨት ነበር ። ወያኔ መስጊድ በማቃጠል ክርስቲያኖች አቃጠሉት እንዲሁም ቤተ -ክርስቲያን አቃጥሎ ሙስሊሞች አቃጠሉት,,,,ወዘተ እያለ እኛ በጎሪጥ እንድንተያይ እና እንደ ጠላት መቀራረብ እንዳንችል ማድረጉ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ፡፡ ይህም ተግባሩ በፍቅር እና በአንድነት የሚኖሩትን የእምነቶቹን ተከታዮች እንደ እግር እሳት ሲያንገበግበን ኖሯል ፡፡ በቅርብ ትውስታችን እንኳን የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ከህዝብ ከመሰወራቸው በፊት 99.6% የወያኔ ካድሬ በታጨቀበት ምክር ቤት ውስጥ ንግግር ሲያደረጉ እንደተለመደው « አንድአንድ አክራሪ ሙስሊሞች በኢትዮጵያ በሸሪአ የሚተዳደር መንግስት መመስረት ፍላጎት ያላችው እንዲሁም ጥቂት አክራሪ ክርስቲያኖች ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሀገር ብቻ ናት የሚሉ ,,,,, ወዘተ» እያሉ በለመደ አፉቸው የየእምነቱን ተከታዮች እርስ በእርሳቸው እንዳይተማምኑ እና በአንድነት እንዳይቆሙ ለማድረግ ያደረጉትን ሙከራ የሰማ ሰው ከዝንብ ማር አይጠበቅም ብሎ ከማለፍ ሌላ ምን ሊባል ይችላል ? ሰውየው እደለመዱት ለመከፋፈል ቢሞክሩም እኛ የኢትዮጵያ ህዝቦች እናት ሀገራችን የክርስቲያኑም ፣የሙስሊሙም፣የተለያዩ እምነቶችን የሚከተሉ እንዲሁም ምንም እምነት የማይከተሉ ወገኖች የጋራ መኖሪያችን መሆንዋን ጠንቅቀን የምናውቅ ነን ። ወያኔ እና በሃይማኖቶች ላይ ያለው ጣልቃ የመግባት ሱሰኝነት በአጼ መለስ ዜናዊ ሲመራ የነበረው የወያኔ ቡድን በሃይማኖቶች ውስጥ የበግ ለምድ እየለበሰ በመግባት የተኩላ ተግባሩን እያከናወነ ይገኛል ። ይህ የማፊያ ቡድን የሀገራችንን ታሪካዊ ገዳም የሆነውን ዋልድባን በልማት ስም ለማጥፋት ደፋ ቀናበማለት ላይ ነው ። ኧረ ለመሆኑ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ የሃይማኖት አባቶች በተለይ ሲኖዶሱ ስለ ዋልድባ ገዳም ምንም አስተያየት አለመስጠቱ ሲኖዶሱ ስለ ገዳሙ ህልውና አይመለከተውም ማለት ይሆን ? ወይስ ከእምነታቸው ፖለቲካው በለጠባቸው ? በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ የአህባሽ አስተምሮ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከውጭ ሃገር ማምጣቱ እና እምነቱነ እንዲከተሉት ማስገደዱ ለኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች ያለውን ንቀት የሚያሳይ ነው ። ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሙስሊም ህብረተሰብ የመጅሊሱ መሪዎች በወያኔ የተሾሙ እና በወያኔ ሳምባ የሚተነፍሱ መሆናቸውን ሙስሊም ህብረተሰብ ጠንቅቆ ያውቃል ። አለመታደል ሆኖ እንጂ በዚህ ሰዓት ነበር ለየእምነቶቻቸው መስዋዕት የሚሆኑ እና ከፖለቲካ ነፃ የሆኑ የሃይማኖት አባቶች የሚያስፈልጉን ። መሰረታዊ የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ጥያቄዎች ከኢትዮጵያ ሙስሊም ህብረተሰብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ዉስጥ ዋናው እና አንገብጋቢው የወያኔ መንግስት ከሃይማኖታችን ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እጁን ያንሳ ፣ የመጅሊስ አመራሮች የኢትዮጵያ ሙስሊምን የሚወክሉ ሰላልሆኑ ነፃ ምርጫ በራሳችን መንገድ እናድርግ እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎች ይገኙበታል ። ከላይ ላሉት ጥያቄዎች አግባብ ያለው መልስ ለማግኘት መፍትሄው ለሙስሊሙ ህብረተሰብ መብቱን መስጠት ሆኖ ሳለ ምርጫን በማጭበርበር የተካነው ወያኔ የራሱን ሰዎች በአመራርነት ለማስቀመጥ ምርጫውን በቀበሌ እንዲካሄድ ቢፈልግም በሙስሊሙ ህብረተሰብ ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በመምረጥ ካለፉት 8 ወራት ጀምሮ በሚያስድንቅ ፣ ጨዋነት በተሞላበት እና አስተማሪ በሆነ መንገድ ሰላማዊ ትግል እያደረገ ይገኛል ። ነገር ግን ስለ መብቱ የሚጠይቅ እና ሰላማዊ ትግል የሚያደርግ ህብረተሰብን ማየት የማይፈልገው ፤ ሰላማዊ እና ህዝባዊ ጥያቄዎች መጥፎ አቅጠጫ በማስያዝ ወደ እርስ በእርስ ግጭት በመቀየር የሚታወቀው አሸባሪው የወያኔ መንግሰት አሁንም የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄዎች ሌላ አላማ እንዳለው በማስመሰል ላይ ይገኛል። ይኸውም የሙስሊሙን ህብረተሰብ ተወካዮች ከአሸባሪ ቡድን ጋር ግንኙነት እንደፈጠሩ ፣ሀገር የማተራመስ ተልዕኮ እንዳላቸው ፣ ጥያቄው የጥቂት አክራሪ ግለሰቦች እንደሆነ,,, ወዘተ በማስመሰል ሰላማዊ ጥያቄውን ወዳልታሰበ አቅጣጫ መውሰዱን እንደ ዋና ስራ ተያይዞታል ። እውነታ የሚያሸብረው እና የሚያስደነግጠው ወያኔ የመብት እና የብዙሃን ጥያቄዎችን ለማጣጣል ብሎም ለመቀልበስ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን በእስር ቤት በማጎር እና በጉልበት የአሸባሪነት ገፀ ባህሪ በሀሰት በማላበስ አኬልዳማን የሚመስል ከንቱ እንዲሁም ከእውነት የራቀ የፕሮፖጋንዳ ፊልም በወያኔ ቴሌቪዢን እና ሬዲዮ እየተቀነባበረ የሙስሊሙን ማህበረሰብ እውነተኛ የመብት ጥያቄዎችን ለማዳፈን ፣የክርስቲያኑ ማህበረሰብ በሙስሊሙ ላይ እንዲነሳ ለማድረግ እና የኢትዮጵያዊያንን አንድነት ለመበታተን እየሞከረ ይገኛል ። ግን መቼም አይሳካለትም !ታጋይ እንጂ ትግል አይሞትም ! ካለፈው ስህተቱ የማይማረው እና የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ቀን ከሌት የሚያልመው ወያኔ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን እና ሌሎች ከ 5 ሺህ በላይ ዜጎችን በየእስር ቤቶቹ በማሰር ፣ በመግረፍ ፣ ሴቶችን በመድፈር እና በአሸባሪነት የውሸት ክስ በመመስረት ኢ-ሰብዐዊ የሆነ ግፍ እየፈፀመባቸው ይገኛል ። ይሁን እንጅ በአሁኑ ጊዜ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሀይማኖቱን እና መብቱን ለማስከበር ቆረጦ የተነሳ በመሆኑ ነገሮች ከዚህ ወደባሰ ሁኔታ ከመግባታቸው በፊት በእስር ላይ የሚገኙትን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን እና ንፁሃን ዜጎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በመፍታት ለተነሱት የመብት ጥያቄዎች መልስ መስጠት ይኖርበታል ። የሃያማኖቱን መደፈር በፀጋ የሚቀበል ኢትዮጵያዊ እንደሌለም ሊረዱት ይገባል ። ህዝብ የመረጣቸው መሪዎችን በማሰር እና በአሸባሪነት በመወንጀል ሰላማዊ ትግሉን አስቆማለሁ ማለት የዋህነት ብቻ ሳይሆን ማን አለበኝነትም ነው ። ለዚህም ዋጋ ይከፍሉበታል !!! የተነሳው መሰረታዊ ጥያቄ በሁሉም ሙስሊም ህብረተሰብ ልብ ዉሰጥ ያለ ስለሆነ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ለመብቱ እና ለእናት ሀገሩ ዉድ ህይወቱን ሰዉቶ እሰከማለፍ ድረሰ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁነቱን እያሳየ ይገኛል። ወያኔዎች እንደሚያስቡት ታጋይን በማሰር እና በመግደል ትግሉን መገደል አይቻልም። ይህ አካሄድ የሙስሊሙን ህብረተሰብ የበለጠ የሚያጠነክረው እና ከሌሎች እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያኖች ጋር በመሆን የወያኔን እድሜ ለማሳጠር እና የኢትዮጵያውያንን የሃይማኖት ነፃነት ወደ አዲሰ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል ። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች የወያኔን ተንኮል እና ደባ ጠንቅቀን ስለምናውቅ ወያኔ ሊከፋፍለን ቢጥርም ለሺህ አመታት የተሳሰርንበትን የፍቅር ሰንሰለት ግን መበጠስ አይችልም ። የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ከጎን በመቆም በተግባር ወገናዊነታቸውን እያሳዮ ይገኛሉ ። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለታሪካዊ ገዳማችን ዋልድባ ህልውና አሏሁ አክበር ማለትም « እግዚአብሄር ታላቅ ነው» እያሉ በአደባባይ አጋርነታቸውን አሳይተዋል ። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ይህንን አንድነት እና የመከባበር መንፈስ ለመናድ እና አገር ለመበታተን የተነሳ ወያኔ የሚባል አሜኬላ ቢኖርም ከአባቶቻችን በወረስነው የአንድነት እና የመከባበር መንፈስ እጅ ለ እጅ ተያይዘን ቀፎው እንደተነካበት ንብ በጋራ ተነስተን የእምነታችንን ነፃነት ብሎም በሀገራችን የጠፋውን ፍትህ ፣እኩልነት እና አንድነት በማሰከበር ታሪካዊ ግዴታችንን እንወጣ ። አንድነታችን ኢትዮጵያ ከወደቀችበት የባርነት ቀንበር ለማላቀቅ እና ነፃነትን ለመጎናፀፍ ትክክለኛ አማራጭ ስለሆነ አሁንም በተጠናከረ ሁኔታ ሊቀጥል ይገባል ። TPLF LEADER ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
Posted on August 2, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a Comment.
![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)
Leave a Comment
Comments (0)