‹‹ባለቤቴ ያለምንም ማስረጃ ከህጻናት ልጆች ተነጥላ ታስራብኛለች›› ጁነዲን ሳዶ

አውራምባ ታይምስ(አዲስ አበባ) – የኢትዮጵያ የስቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ጁነዲን ሳዶ፣ ባለቤታቸው ለ16 ቀናት ያህል ያለምንም ማስረጃ በመታሰራቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለከፍተኛ ጉዳት መዳረጋቸውን ገለጹ፡፡ አቶ ጁነዲን ዛሬ ቅዳሜ በታተመው ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ላይ እንደገለጹት ባለቤታቸው ሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ገብተው ስለወጡ ብቻ ተወንጅለው እስር ቤት መግባታቸው ተገቢ አለመሆኑን በምሬት ገልጸዋል፡፡

Junedin Sadoo

‹‹ኤምባሲ ገብታ ስትወጣ በተደጋጋሚ አየናት ከማለት አልፎ ከዚያስ የት ነው የምትሂደው? ገንዘብ ይዛ ወጥታ ገንዘቡን ምን ላይ ነው ያዋለችው? እቤትም ሆነ ውጭ ከነማን ጋር ግኑኙነት አላት? አሩሲ ስትሂድ ምንድን ነው የምታደርገው?›› ብለው መመርመር ነበረባቸው ያሉት አቶ ጁነዲን ‹‹ሌላው ቢቀር ሁልግዜ ከፓሊስ ጥበቃ ጋር ስለምትንቀሳቀስ ፖሊሶቹንም ጠርቶ ማነጋገርና የበለጠም እንዲያጠኑላቸው ማድረግ ሲችሉ ይሄ ሁሉ አልተደረገም ለ16 ቀናት ክህጻናት ልጆች ተነጥላ መታሰሯ በቤተሰቤና በኔም ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል›› ብለዋል፡፡ በአቶ ጁነዲን እምነት በአሁኑ ሰዓት ከአክራሪነት ጋር በተያያዘ ፖሊስ በባለቤታቸው ላይ ያገኘው አንዳች ዓይነት ማስረጃ የለም፡፡

About these ads

Posted on August 4, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a Comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: