ግርማይ ገብሩ የሚባል ሰው በአሜሪካ ድምጽ የሕወሃት ጥሩምባ መሆኑን ማንም አስቀድሞ ያውቀዋልና፣ የሚገርመው የለም።

ስለ ጠቅላይ ሚኒስትራችን መለስ ዜናዊ እስካሁን ብዙ ያልተናገርነው የምንናገረው ስላጣን ወይም ስለጠፋብን ኣይደለም፡፡ ስራ ላይ ስለሆንን ነው፤ ኣያችሁ እንሰራለን፡፡
ስራ ላይ ሆነን ግን የታመሙት ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻችንን በመንፈስም ይሁን እግዝኣብሔር ምህረቱን እንዲሰጥልን በየ እምነታችን እንፀልያለን፣ እናስባቸዋለንም፡፡ ይህን መልካም ምኞታችን ለሁሉም ፍጥረተ ኣዳመሄዋን ይድረስ፡፡
የሰው ልጅ በህይወት ዘመኑ ይታመማል፣ ይድናል ኣልያም ያልፋል፤ ይህ ረቂቅ የፈጣሪያችን ሚስጥርና ሃይል ነው፡፡ የታመመውን መጠየቅ፣ የቸገረውን መርዳት፣ ያዘነውን ማጽናናት ደግሞ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ነው፡፡ ይህንን ማሳሰብያ “ኢትዮጵያ በልባቸው ለሌለችና እነሱም በኢትዮጵያ ልብ ውስጥ ለሌሉ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ነን ባዮችን” ኣይመለከትም፡፡ ከእርግብ እንቁላል ዘንዶ መወለዱን እዚህ ላይ ልብ ይሏል፡፡

ኣንድን ኢትዮጵያዊ ለምሳሌ ታጋይ መለስ ዜናዊን ታመዋል ሲባል በሞት እንዲለዩ የተመኙ ወይም ደግሞ ለምን ኣልሞቱም ብለው ያዘኑ ኢትዮጵያውያን ነን ባዮች በርግጥም ባመለካከት ኣይድኑም እንጂ የህክምና እርዳታ ይገባቸዋል፡፡ እስኪ በቃቸው እንንገራቸው “የታጋይ መለስ ዜናዊ መሞት የማንንም እድሜ ኣያስቀጥልም”፡፡
ማንንም ወክዬ ኣይደለም እየተናገርኩ ያለሁት፤ ሁሌም ራሴን ነው የምወክለው፡፡ ታጋይ መለስ ዜናዊ እና ድርጅታቸው ለሚያራምዱት የፖለቲካ ዓላማ ማንም የመቃወም መብት ኣለው፤ እኔም በግሌ የማልደግፈው እና የማይዋጥልኝ ድርጊታቸው እየጮኹ ካሉት ግለሰቦች በይበልጥ መተንተን እችላለሁ፡፡ ነገሩ እየሆነ ያለው ግን የመቃወም ሳይሆን የመጥላት ኣባዜ ነው፡፡ በነገራችን ላይ መቃወም ትልቅ ችሎታንና ስነ ምግባርን ይጠይቃል፡፡
ማንም የሚኖረውና የሚሞተው በእግዝኣብሔር ፈቃድ ነው፤ ስለ ጠላኸው ብቻ ኣምላክ ግደልልኝ ብለህ ማመልከቻ ማቅረብ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የጎደለው ኢሰብኣዊ ኣቋም ነው፡፡ ታጋይ መለስ ላመኑበት በጽናት ታግሏል፤ ሰርቷል እየሰሩም ነው፡፡ ብቻቸው ሆነው የፈጠሩት ታኣምር የለም በግላቸው ያጠፉት ነገርም የለም፡፡ እንደ ማንኛውም የድርጅቱ ኣባል በሚሞገሱበት ይሸለማሉ፤ ባጠፉት ይወቀሳሉ፡፡ መለስ ከሌሉ የሚበታተን ኣገር የለም፤ ይኸው ታመው ታክመው እረፍት ላይ ናቸው፤ ኣገሪቷና ስርዓቱ ግን እንደነበር ቀጥሏል፡፡ ሲሰዉ ኣነሰም በዛም በሰሩት ለዘላለም ይዘከራሉ፡፡
ለመሆኑ ስንቶቻችን ነን የትግራይ ህዝብ ብያንስ ለተመዘገበው ለውጥ (በቂ ነው ባይባልም) ለኢትዮጵያ ህዝብ ባለ ውለታ መሆኑን ኣስረግጠን የምናውቀው? ለውጡ እንዲመዘገብ ዕድሜውን ሙሉ ላሳለፈ ግለሰብን እናመሰግናለን ማለት ደግሞ ባህላችን ነው፡፡
 
 ለመሆኑ ኣሜሪካን አገር ሆነው ጩኸት እያሰሙ ያሉት እንዲሁም ውዥምብር እየነዙ ያሉት ኣገራችን ናት ለሚሉዋት ምን ሰራን ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? አገርና መንግስት፣ ህዝብና የፖለቲካድርጅት ለይተው ያውቃሉ?
በኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በይበልጥ እየታየ ያለው የልማት ለውጥ የሁላችንም የስራ ውጤት ነውና እንዲቀጥል እንፈልጋለን፡፡ የጎደለውን ደግሞ ጠንቅቀን እናውቀዋለን እንዲሟላ እና እንዲስተካከል ደግሞ መብታችን ነውና እንታገላለን፡፡ ከሁሉም በላይ እንደ ሰው ልጆች መጠን እርስ በርሳችን እንከባበር፡፡ ማንም ማንን ኣይፈራም፤ እንኳንስ ጊዜ ሁሉንም ኣሳየን፡፡ ስም እየተሰጣጣን እየተቀባባን ይኸው ጊዜው ነጎደ፡፡ ካሁን በኃላ የተጀመረውን ለውጥ ባይደፈርስና እየተተካካን ወደፊት ብንቀጥል የሚሻል ይመስለኛል፡፡
ታጋይ መለስን እንደ ግለሰብ እግዝአብሔር ይማራቸው፤ በቅርቡ አገግመው በህይወት ዘመናቸው ትንሽ ጊዜ አግኝተው የተጀመረውን ስራ ለውጡን አይተውት እንዲያልፉ እመኝላቸዋለሁኝ፡፡ እርሳቸው እና ድርጅታቸው በያዙት ኣቋም ላይ ሙሉ ለሙሉም ቢሆን ተቃውሞ እና የተሻለ አማራጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ግን ተወደደም ተጠላም እምነቱ ይቀጥላል፡፡ ሰዎች ነንና ሰዎች መሆናችን ማሳየት መቻል አለብን፡፡                           

 አይ የኛ ነፃ ጋዜጠኛ ተብዬ! ብሎ ብሎ እንደሚሚ ስብሃቱ ጭልጥ ብሎ የጎጠኝነት መንገዱን ተያያዘው አይደል?!…

አይ የኛ ነፃ ጋዜጠኛ ተብዬ! ብሎ ብሎ እንደሚሚ ስብሃቱ ጭልጥ ብሎ የጎጠኝነት መንገዱን ተያያዘው አይደል?!… ለነገሩ ግርማይ ገብሩ የሚባል ሰው በአሜሪካ ድምጽ የሕወሃት ጥሩምባ መሆኑን ማንም አስቀድሞ ያውቀዋልና፣ የሚገርመው የለም።
በአገራችን በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሲረግፉ አሳዝኖት አንድም ጊዜ ትክክለኛ የዜና ዘገባ እንኳን ለመስራት ሳይደፍር፣ ዛሬ ደርሶ ሕዝባችን መለስ ዜናዊ “በቃ ይሙት!” ማለቱ ብቻ አሳስቦት ይህን ያህል የእርግማን ናዳውን ቢያወርደው ማንም የሚደንቀው የለም። ምናልባት “ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው” ይባላልና የኢትዮጵያ ሕዝብ እርሱን የሚያውቀውን ያህል ራሱን የማያውቅ ሰው ይሆናል።

ብሎ ብሎ ደግሞ ጭልጥ ባለ ሕወሃታዊ አነጋገር “ለመሆኑ ስንቶቻችን ነን የትግራይ ህዝብ ቢያንስ ለተመዘገበው ለውጥ (በቂ ነው ባይባልም) ለኢትዮጵያ ህዝብ ባለ ውለታ መሆኑን ኣስረግጠን የምናውቀው? ለውጡ እንዲመዘገብ ዕድሜውን ሙሉ ላሳለፈ ግለሰብን እናመሰግናለን ማለት ደግሞ ባህላችን ነው፡፡ ‘ ይለናል።
ስለየትኛው ለውጥ እንደሚያወራ ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ግልጽ አይደለም። ለርሱ ኢትዮጵያ ማለት ትግራይ ብቻ ማለት ካልሆነ በስተቀር ወያኔዎች ስልጣን ላይ ከወጡ ወዲህ በሌላው የአገሪቱ አካባቢዎች የሚኖረው ሕዝብ ከስቃይና ከመከራ ውጭ የተረፈው ነገር የለም።
ኢትዮጵያውያን በአመለካከት ሳይሆን በቋንቋና በብሄር ተከፋፍለው እንዲናጩ የተደረገው ከትግራይ ሕዝብ መሃል በፈሉ ቱሃኖች ነው።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአገሪቱ ገበሬዎች ለዘመናት ከኖሩበት የእርሻ መሬት በሃይል እየተፈናቀሉ በገዛ አገራቸው ላይ ቁራሽ መሬት አጥተው የትም ወድቀው ሲቀሩ መሬታቸው ከውጭ አገር ለመጣ ከበርቴ የተቸበቸበው በነዚሁ አካይስቶች ነው።
* “እግዚአብሄር የለም” ይላል የሚባለው ደርግ እንኳን ያላደረገውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የአገራችንም ቅርስ የሆነውን ከ1ሺህ ዓመት ያስቆጠረውን ታሪካዊውን የዋልድባ ገዳማትን ወደ ስኳር እርሻነት ለመቀየር ጥረት እየተደረገ ያለው በነዚህ ከትግራይ ሕዝብ መሃል በፈለቁ ጉዶች ነው። እንዲያውም በክርስቲያንነታቸው ይታወቁ የነበሩት የትግራይ ሰዎችና ካህናት ይህንን አስመልክቶ ለተቃውሞ እንኳን አለመነሳታቸው የሚያስተዛዝብ ነው። ይህ ሁሉ የሚደረገው ከወሎና ከጎንደር ተቆርሰው ወደ ትግራይ በተካለሉት ለም የእርሻ መሬቶች ላይ በተለየ ሁኔታ ትግራይ በምግብ እራሷን እንድትችል ለማድረግ ታስቦ እንጂ፣ ልማቱ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ታልሞ የታቀደ ቢሆንማ ለህንድና ለሌሎች አገር ዜጎች በርካሽ ዋጋ እየቸበቸቡት ባለው መሬት ላይ ሸንኮራቸውን መትከል ይችሉ ነበር። እንዲህ አይነቱ ነገር ሲፈፀም ያየነው በነዚህ የትግራይ ልጆች ነው።
* የእስልምና እምነት ተከታዮች በመንግስት ደረጃ “የለም! መከተል ያለባችሁ ይሄኛውን ሃይማኖት ነው” ተብለው ለዘመናት የኖረው የሃይማኖት ነፃነታቸው ተደፍሮ እየተደብደደቡ፣ እየተገደሉና እየተሳደዱ ያሉት በነኚሁ ጉዶች ዘመን ነው።
* አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚቀምሰው ዳቦ አሮበት በጠኔ እየተሰቃየ የሚገኘው በዘመነ ሕወሃት ነው።
* ከአንድ ብሄር የተውጣጡ ሰዎች ከአገሪቷ ከፍተኛ ስልጣን እስከቀበሌ ሹምነት ድረስ ያለውን እርከን ያለ አግባብ ተቆጣጥረውት የኢትዮጵያን ሕዝብ ያለ ይሉኝታ እንደጠላት አበሳውን እያሳዩት እንዳለ ያየነው በዘመነ ሕወሃት ነው። ቡናም ሆነ ሌላ የአገሪቷን ሃብት ወደውጭ ልከው የሚሸቅጡ፣ ሕፃናት ልጆቻችንን እየለቀሙ በጉዲፈቻ ስም ለፈረንጆቹ በውድ ዋጋ በመሸጥ የተሰማሩ፣ ወደ አረብ አገርም ሆነ ወደ ሌላው ኢትዮጵያውያን እሕቶቻችንን ለግርድና በመላክ ስራ ፈቃድ አግኝተው በዚህም በቀላሉ የማይገመት ገንዘብ በማጋበስ ላይ ያሉት ከትግራይ የወጡ የሕወሃት ሰዎች መሆናቸውን ማስረጃ በመጥቀስ አንድ በአንድ መተንተን ይቻላል።
* እረ ስንቱን ዘርዝሬ እጨርሰዋለሁ?! … ሌሎቻችሁ ጨምሩበት! … ግርማይ እንግዲህ እንዲህ አስከፊና መራራ ሕይወት እንድንገፋ የፈረደብንን መንግስት ያቋቋሙትን ሰዎች ነው ባለውለታችሁ ናቸው የሚለን።
አጅሬ ግርማይማ ከዚያም አልፈን የኢትዮጵያ ሕዝብ መለስን ሊያመሰግነው እንደሚገባ አስምሮልን አልፏል። ምናልባት እንደ ዘመኑ የጎጥ ልጆቹ የዋጠው ጮማ ልቡን ደፍኖት ይሆናልና አትፍረዱበት!! … አሁን በኔ ሞት! እውነት የኢትዮጵያ ሕዝብ መለስ የሚያስመሰግን ስራ ሰርቷል ብሎ ያምናል? ፍርዱን ለሁላችሁ ትቻለሁ!






  
About these ads

Posted on August 8, 2012, in ETHIOPIA ENGLISH. Bookmark the permalink. Leave a Comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: