የሻማ ማብራት በግዳጅ በየመንገዱ ይከናወናል የሰርገኞችም ከሰርጋቸው ስራት ተበተኑ
በኢትዮጵያ ውስጥ የሃዘን ቀንን አስመልክቶ በየመንገዱ የሻማ መብራት ይዘው የማይጓዙ ከሆነ በወታደሮች በግዳጅ እየተሰጠ ይገኛል። አጠቃላይ ክለቦች የተዘጉ ሲሆን በተለይም የጊዜአዊ እለታቸውን በምሯሯጥ ላይ ያሉት የቺቺንያ ሰፈር ነዋሪዎች በግዳጅ ቤቶቻቸውን እንዲዘጉ ተደርገዋል ። እኛ እቅድ ሳይኖረን በግዳጅ ሃዘን አድርጉ መባል የለብንም እኛ ስለመሞቱ እናዝናለን አዝነናልም ይህ እንደ ሰባዊ ፍጡርነቱ ልንቀበለው የምንችለው ጉዳይ ነው የምትለው ወጣቷ በአሁን ሰአት ቀድሞ ወደ ነበረን ህይወት መመለስን እንሻለን የስራተ ቀብሩን መፈጸም በጉጉት ነው የምንጠብቀው ስትል አክላ ገልጻለች
በተልይም ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ሰርጋቸውን ሸገር መናፈሻ ያደረጉ ሙሽሮች ከሰርጋቸው በማስተጓጎል እና እድምተኞቹን በማባረር የሰርጉን ያደቅምላቸው የነበረውን ድምጻዊ ወደ ፖሊስ ጣቢያ መውሰዳቸው ከሙሽሮቹ ቤተሰቦች በተለይም ለማለዳ ታይምስ ተገልጾልናል ። በአሁኑ ጊዜ የመለስ ዜናዊን የሙት ቀን አስመልክቶ ማንኛውም ሰው እንደ ዜግነቱ ለመለስ ማዘን አለበት ተብሎ የንግድ ሱቆች ሳይቀሩ በጥቁር ልብስ ያጌጡ የንግድ ማስታወቂያ ጨርቆቻቸውን እንዲሰቅሉ ግዴታ እንደተደረገባቸው ገልጸዋል ። ለረጂም ሳምንት የስራተ ቀብራቸው የተራዘመው ጠቅላይ ሚንስትሩ የቅርብ ወዳጆቻቸውን ሁሉ እያስከተሉ መጓዛቸውን ተያይዘውታል።ሀዘኑ ፈሩን እየሳተና ወደ አልሆነ አቅጣጫ እየሄደ የመጣ ይመስላል
የኢቲቪ ስህተቶች
1 የጎዳና ተዳዳሪዎች “እሱን ብለን ነው ጎዳና የወጣነው..,,,,,,
2 “እንጀራ የበላሁት በአቶ መለስ ጊዜ ነው ”
ድሮ ሳር ነበረ የምትበላው ?
Posted on August 27, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a Comment.

![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)
Leave a Comment
Comments (0)