የአቶ መለስ አስከሬን የት እንዳለ አይታወቅም::ስላሴ ቤተ ክርስቲያን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶ በጣም በትልቁ ተሰቅሏል: ደፍሮ የሚያነሳው ጠፍቷል!
የአቶ መለስ አስከሬን የት እንዳለ አይታወቅም::ከየት አምጥተው ሙዝየም ውስጥ እንደሚያስቀምጡት ጨንቁዋቸዋል:: አስከሬኑ ማን ጋር እንዳለ እስካሁን ማረጋገጫ አልተገኘም ::
ስላሴ ቤተ ክርስቲያን “የአቡነ ጳውሎስ ፎቶ ተነስቶ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶ በግራም በቀኝም ቦታ በጣም በትልቁ ተሰቅሏል” ደፍሮ የሚያነሳው ጠፍቷል!
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ግብዓተ መሬት ከተፈጸመ እነሆ 5 ቀናት አለፉ ፤ አስከሬናቸው ያረፈበት ቦታ ከዚህ በፊት የማንም አስከሬን ያላረፈበት ከቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በስተ ግራ በኩል ይገኛል ፤ በቴሌቪዥን እንደተመለከታችሁት የውስጡ ግድግዳ በሴራሚክ ተነጥፎ ሳጥኑ በክብር አፈር እንዳይበላው ታስቦ አስከሬኑ አርፏል ፤ ሳጥኑ ላይ ወደፊት ሙዚየም እንደሚሰራ ታሳቢ በማድረግ ብዙ ድንጋይ እና አፈር ሊያሸክሟቻ አልወደዱም ፤ ባይሆን ትንሽ ባዞላ ቢጤ ከላይ በማስቀመጥ ክፍተቱን በሲሚንቶ በመሙላት ከላይ የኢትዮጵያ ባንዲራን አልብሰዋቸዋል ፤
በቀብር ስነ ስርዓት አንድ ሰው ከሞተ በኋላ የተቀበረበት ቦታ አፈር መመለስ የተለመደ ቢሆንም ይህ ነገር ግን በጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን ላይ አልተደረገም ፤ ስርዓተ ቀብሩ ከተፈጸመበት ቀን አንስቶ በርካታ ፊደራል ፖሊሶች እና የመከላከያ ሃይሎች በቦታው ይገኛሉ ፤ አስከሬናቸው ያረፈበት ቦታ ላይ 2 ሜትር በ 3 ሜትር የሆነ ቤት በአሁኑ ሰዓት ተሰርቶበታል ፤በሩ መግቢያው ላይ የኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ ያለው ባለ 5 ኮከብ አርማ አርፎበታል ፤ ሰዎች አሁንም የተቀበሩበት ቦታ ድረስ እየሄዱ ሲያለቅሱ ተስተውለዋል ፤ ያረፉበትንም ቦታ ለማየት እስከአሁን ድረስ በርከት ያሉ ሰዎች ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሲመጡ ተስተውሏል ፤ ቦታው ላይ ምን ለመስራት እንዳሰቡ ባናውቅም መሰረተ ልማት ለመገንባት የሚያስችል ሸክላዎች ፤ ሲሚንቶዎች ፤ በርካታ ትላልቅ ብረቶች ፤ እንጨቶችና የተለያዩ መሳሪያዎች በቦታው ላይ እየተራገፈ ይገኛል ፤ አስከሬናቸው ሙዝየም ውስጥ ከተቀመጠ ለምን ይህን ሁሉ ነገር ይደረጋል? ሲሉ ሰዎች ሲያወሩ ይደመጣሉ ፤ ባሳለፍናቸው 4 ቀናት ውስጥ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ባይኖርም አሁን ግን አስከሬኑ ያረፈበትን በአማካይ 300 ካሬ የሚሆን ቦታ በላስቲክ የማጠር ስራ እየተሰራ ይገኛል ፤ ሀውልቱን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ነው እንዳይባል አስከሬናቸው ሌላ ቦታ ያርፋል ተብሏል ፤ ታዲያ ለምን ይህን ያህል ቦታ ማጠር አስፈለገ ? 4 ካሬ የማይበልጥ ቦታ ላይ ያረፈን አስከሬን ስራ ለመስራት ይህ ያህል ቦታ ማጠር አስፈላጊነቱ አልታየንም ፤ ወደፊት ይህ ቦታ የታጠረው ላስቲክ ተነስቶ ለቤተክርስትያኒቱ ምዕመናን የቀድሞውን ቅዳሴ የማስቀደሻ ፤ በዓል ማክበሪያ እና መሰል አገልግሎቶችን ይሰጣል ብለን አሁን መናገር አንችልም::
የአቡነ ጳውሎስ ፎቶ ያለበት ሸራ የቀብራቸው እለት በቤተክርስትያኑ በስተግራ በኩል መሰቀሉ ይታወሳል ፤ ከሁለት ቀን በኋላ ግን የአቡነ ጳውሎስ ፎቶ ተነስቶ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶ በግራም በቀኝም ቦታ በጣም በትልቁ ተሰቅሏል ፤ መጀመሪያ እኛ የአቡነ ጳውሎስን ፎቶ ሰቅለን ባናሳያቸው ኖሮ እነርሱም ፎቷውን ለመስቀል ጥያቄ ባላቀረቡ ነበር ፤ መሰቀሉን ለምን? እያልን ሳይሆን የተሰቀለበት ቦታ ግን አግባብ ነው የሚል ሀሳብ የለንም ፤ ፎቶው ዛሬ ከተሰቀለ 7 ቀን ሞልቶታል እስከመቼ እንደሚቆይ አይታወቅም ፤ የጥላሁን ገሰሰ ፎቶ የሞተ ሰሞን በእጁ ማይኩን ይዞ በትልቁ በግቢው ውስጥ መሰቀሉ የዛሬ 3 ዓመት ትውስታችን ነው ፤ የጥላሁንን ፎቶ ማይክ ይዞ በግቢው ውስጥ የተመለከቱ ጥቂት ሰዎች በሁኔታው ደስተኛ አለመሆናቸው በጊዜው ሲገልጡ ነበር ፤ ለምን ? ብለው ቢጠይቁም መልስ የሚመልስ ሰው አይገኝም ፤ ቤተክርስትያን ውስጥ በትልቁ እንዲህ አይነት ፎቶ መመልከት ለአማኙ ምን አይነት መንፈስ ውስጥ እንደሚያስገባው ማወቅ አይከብድም ፤ በጊዜው ጥቂት ወጣቶች “ኮንሰርት ያለበት ነው የሚመስው” እያሉም ሲቀልዱ ተስተውሏል ፤ ስለዚህ የቤተክርስትያንን ግቢ እኛው መደረግ ያለበትንና የሌለበትን ለይተን ማወቅ መቻል አለብን ፡፡
5ኪሎ ቅድስት ማርያም በሩ ላይ ቆመው ሲሳለሙ ከፊት ለፊት ያለው የአቡነ ጳውሎስ ፎቶ ይመለከታሉ ፤ አሁን ደግሞ ቅድስት ሥላሴ ሄደው እጅዎትን ወደላይ አንስተው ለማማተብ ሲሉ ከፊት የሚታይዎት ሌላ ነገር ነው ፤እነዚህ ነገሮች ከጊዜ ወዲህ የመጡ ተለጣፊ ነገሮችን እየለመድናቸው መጥተን ወደፊት ሌላ ነገር እንዳይፈጥሩ ፍራቻ አለን ፤ ከዓመታት በፊት የአቡነ ጳውሎስ በየቤተክርስትያኑ የተሰቀሉት ፎቶዎች ቅዱስ ሲኖዶስ ይነሱ ብሎ መወሰኑ የሚታወቅ ነው ፤ ማንሳት ሲያቅተን ለአእምሯችን ተገቢ ነው ብለን ነግረነው ካበቃን በኋላ አሁን ብናያቸውም ባናያቸውም ምንም ላይመስለን ይችላል ፤ ነገር ግን አግባብ አለመሆኑን ግን ማወቅ አለብን ፤ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ፎቶም ቢሰቀል አግባብ የሚሆነው አስከሬናቸው ያረፈበት ቦታ ቢሆን መልካም ነው ፤ እንደ አሁኑ ተደርጎ መሰቀሉ ግን አግባብ ነው አንልም(ከተሳሳትን እንታረማለን)፡፡
ቸር ሰንብቱ
Posted on September 8, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a Comment.


![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)
Leave a Comment
Comments (0)