የኢትዮጵያውን ቀን ተከብሮ ፣በደማቅ ክብረ በአል እንደነበረው ተጠቁሞአል ።
በየአመቱ የሚከናወነውን እና ልዩ የበአል ድምቀት ሰጥቶት የነበረው የኢትዮጵያኖች ቀን በታላቅ ክብረ በአል ተከብሮ ውሎአል ።በትላንትናው እለት የተካሄደውን የኢትዮጵያኖችን ቀን አስመልክቶ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያኖች እና ኢትዮጵያን ወዳጆች እንዲሁም ከኢትዮጵያ በማደጎ የሚያድጉ እና ያደጉ ኢትዮ አመሪካኖች ከአሳዳጊዎቻቸው ጋር በመሆን በዴይሊ ሴንተር በመገኘት በአሉን አክብረዋል ። በክብረ በአሉ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በመዲናዋ ሲውለበለብ የህዝብ መዝሙሯንም በአንድነት ከሃገሪቱ የህዝብ መዝሙር ጋር ተዘምሯል። የኢትዮጵያን አዲስ አመት አስመልክቶ በቺካጎ ማህበረሰብ የተሰየመውን እና በየአመቱ በመዲናዋ መሃል ቦታ ላይ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ቀንን በደማቅ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን በተለይም ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት እና የአፍሪካ ኮሚኒቲዎች በስፍራው በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።በትላንትናው እለት የድምጻዊ ካሳሁን ታዬ (ሶራ) በመታጀብ የበአሉን ድምቀት አሰደሳች በማድረግ ወጣት ተወዛዋዦች ባህሎቻቸውን እና የእለቱን የብሄር ብሄረሰቦች ውዝዋዜ ያደረጉ ሲሆን በዛሬው እለትም ቀጣዩን የባህል ጨዋታ በክሮሺያ ሴንተር በሰፊው እንደሚያደርጉ ከማህበሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ። በተለይም በኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አሶሴሽን ኦፍ ቺካጎ ዳይሬክተር የአዲሱን አመት አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት ህዝቦች ልዩነታቸውን አቻችለው ፣ለተጠናከረ ሰላም አንድ ላይ የሚጓዙበት መንገድ መፍጠር መቻል አለባቸው ፣ማንኛውም ሰው የፖለቲካ ልዩነቱን ወድኋላ በመተው ፣ከኮሙኒቲው ጋር በመሆን ወገኖቹን እና ሃገሩን በጥንካሬ መርዳት ይገባዋል ሲሉ ይህ ዘመን የእኛ ነው ሰርተንም የምንለወጥበት ፣ሰርተን እድገታችንን የምናሳይበት ፣ዛሬ ላይ ቆመን ነገን የምናስብበት ስለሆነ በአንድነት ፣በሰላም እና በፍቅር ወደ 2005 እንደንሸጋገር እጅ ለእጅ እንጓዝ የጋራ ድላችንም ይሁን ዘመኑን አሁንም የሰላም እና የደስታ ዘመን ይሁንላችሁ ሲሉ በግላቸው እና ኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማህበር ስም አስተላልፈዋል
Posted on September 8, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a Comment.
![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif?w=480)
![ETHflag_1__1_[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2012/09/ethflag_1__1_1.gif)


![60682_3922603203195_526663258_n[1] 60682_3922603203195_526663258_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8379/8653925962_694f997614_m.jpg)
![532059_547719218612772_154310823_n[1] 532059_547719218612772_154310823_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8101/8647940727_046dbca87f_m.jpg)

![524141_495401087180992_37321768_n[1] 524141_495401087180992_37321768_n[1]](http://farm9.staticflickr.com/8116/8645651087_09f9c14b6c_m.jpg)
Leave a Comment
Comments (0)