የጐንደሩ ጉዳይ – የዐማራውን ኅልውና የማስከበሩ ትግል የመጀመሪያው ምዕራፍ

ሰሞኑን የሞሶሎኒ ዓላማ አራማጅ የሆነው ዘረኛው የትግሬ ወያኔ አረመኔአዊ አገዛዝ፤ ባለፉት 40 ዓመታት በወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ በተናጠል፤ በዐማራው ነገድ በጥቅል፤ የሚፈጽመው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋርሯል። በቅርቡም ባካሄደው ዘግናኝና ሰቅጣጭ ግድያና ሥቃይ፣ እስራት፣ እንግልትና የማንነት ነጠቃ፣ የጥቃቱ ሰላባና ዒላማ የሆነውን የወልቃይት፣ የጠገዴና የጠለምት ሕዝብ ትዕግሥት አሟጦ ወደለየለት ሕዝባዊ አመጽ መሸጋገሩን የብዙኃን መገናኛ መሣሪያዎች መዘገባቸው ይታወሳል።

የሕዝባዊ አመጹ አነሳስም ሕዝቡ አስቦና አቅዶ ያደረገው ሳይሆን፣ በአባይ ወልዱ የሚመራው የትግራይ ገዥ እና «የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር ሊቀመንበር»፣ «የዐማራ ክልል አስተዳደር» ተብየው ሳያውቅና ሳይፈቅድ፣ አፋኝ ነፍሰ ገዳዮቹን በማን አለብኝነት ወደ ጎንደር ከተማ ልኮ፣ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ሕጋዊና ሰላማዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባሎችን በደረቁ ሌሊት፣ ሰርቆና አፍኖ ለመውሰድ ባደረገው የአሸባሪነትና የውንብድና ሥራ፣ ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣ «የአገዛዝ ሥርዓቱ ያወጣው ሕግ ከሚፈቅደውና ከሚያዘው ውጭ፣ በሌሊት ማንም እንደሌባ አፍኖ ሊወስደኝ አይችልም» በማለት በወሰደው ሕጋዊ የተከላካይነት ርምጃ፣ በተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ፣ በቋፍ ላይ ለነበረው የሕዝብ ብሶት፣ አሸባሪውና ወንበዴው ወያኔ ቤንዚን በማርከፍከፉ የተነሳ የተፈጠረ ሕዝባዊ ማዕበል ነው።

የጎንደር ሕዝብ፣ አስተዋይ፣ ጨዋና የአብሮነት ስሜቱ የጠነከረ በመሆኑ እንጂ፣ ወያኔ ሆን ብሎ በቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣ ከወያኔ ጋር ንክኪ ብቻ ሳይሆን፣ የዘር ትስስር ባላቸው ላይ ይደርስ የነበረው ጥፋት መጠነ ሠፊ ሊሆን ይችል እንደነበር ብዙዎች ያምናሉ። በመሆኑም ሕዝቡ ቁጣውን የገለጸው፣ በሁሉም የትግሬ ተወላጆች ላይ ሳይሆን፣ የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች እና ሰላይ አሰላዮችን መርጦና ለይቶ ነው። ቁጣውን የገለጸውና ክንዱን ያነሳው፣ ትምህርት ሰጭ በሆነ መልኩ፣ ላለፉት 40 ዓመታት የወያኔ ሰላዮች፣ ተላላኪዎች፣ ገዳዮችና አስገዳዮች በመሆን ሕዝቡን ሲያሰቃዩ በነበሩና፣ ለወያኔ በሰጡት አገልግሎትና ሁለንተናዊ ድጋፍ፣ የልዩ ልዩ ጥቅሞች ተጠቃሚዎች በሆኑት ወያኔዎች ላይ ነው።

«ለሕዝብ ጥቅም፣ ለሰዎች ዕኩልነት፣ መብትና ነፃነት፣ ከሁሉም በላይ ለኢትዮጵያ አንድነት ቆመናል» ለሚሉና «በሕዝብ የበላይነት እናምናለን» ለሚሉ፣ «ወያኔ ዘረኛና አጥፊ ድርጅት ነው ብለው ከልብ ለሚያምኑ፣» የጎንደር ሕዝብ የወሰደው ራስን የመከላከል ርምጃ ተገቢና ለሌሎችም በአርኣያነቱ የሚጠቀስ እንጂ፣ የሚያስወግዝ አልነበረም። ሆኖም፣ «የማይመቱት ልጅ፣ ሲቆጡት ያለቅሳል፣» ዓይነት የሆኑት በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ የትግሬ ተወላጆች፣ አንዳንዶቹም ወያኔን አምጠው ወልደው፣ የትግሬ ዘር በነቂስ ዐማራውን በዘር ደመኛ ጠላትነት እንዲያይ፣ ፕሮግራም ጽፈው፣ አደራጅተውና መርተው ከዚህ አጥፊ ደረጃ ያደረሱ ቡድኖችና ግለሰቦች፣ የጎንደር ሕዝብ ራሱን የመከላከል ሰብአዊና ፖለቲካዊ ተፈጥሮአዊ መብቱን ተጠቅሞ በወያኔ አፋኝ ቡድኖች ተጎትቶ ላለመታረ,ድ ያደረገውን የመከላከል ርምጃ በማውገዝ፣ የባዶ በርሜል ጩኸት ሲጮኹ ተሰምተዋል። በዚህም የማስመሰል ተቃዋሚነታቸው ዕርቃኑን እንዲቆም አድርገዋል። የወያኔ አጋርነታቸውንና የዐማራው ነገድ ጠላትነታቸውንም ዳግም አሳይተዋል። የሚገርመውና የሚደንቀው እነዚህ ወገኖች ወያኔ ባለፉት 40 ዓመታት፦
o የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብን ማንነት ነጥቆ «ትግሬ ናችሁ» ከማለት ያለፈ፣ አጽመ እርስቱን በመንጠቅ ከሰባት መቶ ሺ በላይ ትግሬዎችንና የወያኔ ታጋዮችን አስፍሮ ሕዝቡን ለልመና ሲዳርግ፣

o በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብን ንብረታቸውን ወርሶ ሲገድል፣

o በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብን ሲያሰድድ፣

o በ1985 ዓ.ም. በአደባባይ ኢየሱስ ቤተክርስቲያ ላይ ለፀሎት በተሰበሰቡት ምዕመናን ላይ በመትረየስ ሩምታ ከ60 በላይ ገድሎ፣ በመቶ የሚቆጠሩትን ሲያቆስል፤

o በደደቢት ሠራዊት ከተማዋን አስከብቦ የጎንደርን ሕዝብ የደም ካሣ የመብራት ኃይል ማመንጫ ጄኔሬተር ነቅሎ ብዘት ከተማ ሲተክል፣

o የጎንደርን ሕዝብ የሚንቀሳቀስ ንብረት ነቅሎ ወደ ትግራይና ኤርትራ ሲያጉዝ፣

o ከ1983 እስከ 1985 ዓ.ም. ባሉት ዓመታት በበደኖ፣ በአሰቦት ገዳም፣ በወተር፣ በመቻሬ፣ በአርባጉጉ፣ ዐማራውና ክርስቲያኑ ከነሕይዎቱ ገደል ሲጣል፣ በገጀራ አንገቱን ሲቀላ፣ ነፍሰጡሮች ሆዳቸው በሳንጃ ሲቀደድ፣ እናቶች ጡታቸው ሲቆረጥ፣

o በወለጋ፣ በከፋ፣ በኢሉባቡር፣ በመተክል፣ ለዘመናት ይኖሩ የነበሩ ዐማሮች፣ ዐማራ በመሆናቸው ብቻ፣ ቤት ንብረታቸውን ተነጥቀው ሲባረሩ፣ ሲገደሉ፣ ታርደው ሲበሉ፣

o የዐማራውን ተፈጥሮአዊ የመራባት መብቱን በመግፈፍ በወሊድ ቁጥጥር ስም እንዲመክን ሲደረግ፣

o በአጠቃላይ ባለፉት 25 ዓመታት የወያኔ አገዛዝ 5 ሚሊዮን ዐማራ ከምድረ ገጽ ሲያጠፋ፣

o በጋምቤላ ሕዝብ ላይ የዘር ፍጅት ሲፈጽም፣

o በቴፒና በአዋሳ ንፁሐን ዜጎችን ሲገድልና ሲያሰቃይ፣

o በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ያላቋረጠ ግድያ፣ እስራትና መሬት ነጠቃ ሲያደርግ፣

o በሱርማ ተወላጆች ላይ እንደ ጥንቱ የባርነት ዘመን እንደ በቅሎ ቀይዶ፣ እንደ በሬ ጠምዶ፣ የምድር ሥቃይ ሲያሳያቸው፣

o በ1997 ዓ.ም. የብሔራዊና ክልላዊ ምርጫ ወያኔ በሕዝብ ድምፅ ተሸናፊ በመሆኑ፣ ሥልጣኑን ላለመልቀቅ በወሰደው የኃይል እርምጃ ባስከተለው ሕዝባዊ አመጽ፣ በአዲስ አበባ ከተማ በአጋዚ ሠራዊት ንፁሐን ዜጎች ጭንቅላትና ልባቸውን ተመትተው ለሞቱና ለቆሰሉ ኢትዮጵያውያን፣ «ለምን?» ብለው ያልጠየቁ ወገኖች ዛሬ፣ «ለምን ወያኔ ይደፈራል? እንዴት ተብሎ ወያኔ ይቆነጠጣል?» በሚል ስሜት፣ ወያኔና አጋሮቹ በጎንደር ሕዝብ ላይ የተለመደ የጥፋት ክንዱን እንዲያነሳ ጥሪ አቅርበዋል።

እስካሁን ይፋ ከተደረጉት መግለጫዎቻቸው፣ ወያኔ የባሕሪው የሆነውን የጥፋት ክንዱን፣ በተናጠል በጎንደር ሕዝብ ላይ፣ በጥቅል ደግሞ በዐማራው ነገድ ላይ እንዲያነሳና የዘር ፍጅት እንዲፈጽም ጥሪ ያቀረቡትና ለጥፋቱም ተባባሪ መሆናቸውን የገለጹት የትግራይ ተወላጆች የሚከተሉት ናቸው።

አንደኛ፦ «የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር – ዴሞክራሲያዊ ምትሕብብር ትግራይ» የተሰኘው የፖለቲካ ድርጅት፦
ይህ ድርጅት የወያኔ መሥራች አባሎች ብቻ ሳይሆኑ፣ የድርጅቱን ፕሮግራም ባዘጋጁ፣ በመሩና ባደራጁት አረጋዊ በርሄና ግደይ ዘርዓጽዮን የተመሠረተና የሚመራ መሆኑ ይታወቃል። እነዚህ ሰዎች በየግል የሥልጣን ሽኩቻ ከድርጅቱ ከሕወሓት እስከተባረሩበት 1977-78 ዓ.ም. ድረስ፣ ወያኔ በኢትዮጵያ አንድነት፣ ብሔራዊ ጥቅም፣ በሕዝቡ ሉዐላዊነትና ነፃነት ላይ ለፈጸው አገራዊ ክሕደት፣ በመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂዎች ከሚሆኑት መካከል ናቸው። ከሁሉም በላይ «ዐማራው የትግሬ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ነው! በመሆኑም የትግሬ ዘር ተደራጅቶ ዐማራውን ማጥፋት አለበት፤» የሚለውን የወያኔ ፕሮግራም በመጀመሪያ ደረጃ እንዲይዝ አንድ አድርገው የጻፉና በዚህም በወልቃይት፣ ጠገዴ እና ጠለምት ሕዝብ በተናጠል፣ በጥቅል በጎንደሬውና በዐማራው ነገድ ላይ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዲፈጸምበት መመሪያ ያዘጋጁ፣ መመሪያ የሰጡ፣ ሕዝቡን ለጥፋት የቀሰቀሱ፣ ያደራጁና የመሩ መሆናቸው በግልጽ ይታወቃል። አረጋዊና ግደይ ከድርጅቱ እስከተባረሩበት ጊዜ ድረስ፣ ድርጅቱን በሊቀመንበርነትና በምክትል ሊቀመንበርነት የመሩ፣ የድርጅቱን ፕሮግራም አርቅቀው ያጸደቁ፣ ወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት፣ እንዲሁም ከወሎ የነጠቁት ራያና ቆቦ፣ ሰቆጣ ወደ ትግራይ ግዛት እንዲካለል ካርታ ያዘጋጁ መሆናቸው ይታወቃል። ይህን «አናውቅም፣ አልሰማንም» የሚል ካለ፣ የአቶ ገብረመድኅን አርኣያን ቃለምልልሶችና ጽሑፎች እንዲያዳምጥና እንዲያነብ ይጋበዛል። ወዳጅና ጠላቱን ለይቶ የማያውቀው «ተቃዋሚ ነኝ» የሚለው ወገን፣ የእነዚህን መሠሪ ሰዎች ዓላማና ሤራ በቅጡ ሳያውቅ፣ ከነርሱ ጋር የፖለቲካ ሽርክና መግጠሙ ከማሳዘን አልፎ ያሳፍራል። የተቃዋሚው ጎራ ትግል ለድል አልበቃ ያለውም እነዚህን የመሰሉ ሰዎች ከማግለል አልፎ፣ ትግሉን እንዲመሩ እድል በመስጠቱ ነው።

የአረጋዊ በርሄ ቦርሳ ተሸካሚ የሆነውና የዚሁ ድርጅት አባል የሆነው፣ ወላጆቹ ባወጡለት ስም ዮሴፍ ዘለለው፣ ወያኔ ባወጣለት የጥፋት ስሙ ደግሞ መኮንን ዘለለው የተባለው ባንዳ፣ ከኤስ.ቢ.ኤስ. ሬዲዮ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ፣ « አማርኛ ወደ ወልቃይት ሄደ እንጂ፣ ወልቃት ትግሬ ነው» ብሎ መናገሩን የምናስታውሰው በከፍተኛ ቁጭት ነው። ተቃዋሚውን ለመሰለልና ለመከፋፈል የቆሙትን እነዚህን የመሰሉ ሰዎች በተቃዋሚው ጎራ ማሰለፍ፣ አንድም ወያኔንና ባሕሪውን አለመረዳት፣ ሁለትም እያንዳንዱ የትግሬ ትውልድ ለወያኔ ያለው አመለካከት ስስ መሆኑን አለመገንዘብ ነው። ይህ ደግሞ ራስን በራስ ከመግደል ተለይቶ የሚታይ አይደለም። (ይህ አባባል ግን ሁለቱን የዕውነተኞቹ የጥንቶቹ የትግራይ ሕዝብ ዓላማና ፍላጎት አራማጅ የሆኑትን በግልጽ ለወያኔ የጉረሮ አጥንት የሆኑትን አቶ ጌታቸው ረዳንና አቶ ገብረመድኅን አርኣያን አይመለከትም።)

ተቃዋሚው ዕውነት በቁርጠኝነት ወያኔን ለመታገል ከቆረጠ፣ ከእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ራሱን ማጽዳት አለበት እንላለን። ይህን እንድንል ያስገደደን፣ «በአረጋዊ በርሄና ግደይ ዘርአጽዮን የሚመራው «የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር» በ18/7/2016 «ጎንደር፣ የህዝቡ ትግል ሲግል-የኢህአዴግ ውድቀት ሲቀላጠፍ» በሚል ርዕስ ባሰራጨው መግለጫ፣ ወያኔን አጥብቀው የሚቃወሙ፣ የወያኔን ተልዕኮና ግብ ምን እንደሆነ በቅጡ የተረዱ ግለሰቦችና ድርጅቶችን፣ ከሁሉም በላይ ወያኔ የትግራይን ሕዝብ በነቂስ አደራጅቶ በኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያዊነትና በዐማራው ነገድ ላይ እያደረሰ ያለውን የዘር ፍጅት አጥብቀው የሚቃወሙ ወገኖችን፣ «የትግራይን ሕዝብ ከወያኔ ባለመለየት ሊያጠቁት ነው» በማለት፥ ለወያኔ መረጃ አቅራቢ፣ ሰላይ፣ ገዳይና አስገዳይ በሆኑት የትግራይ ተወላጆች ላይ የሚሰነዘረውን በሐቅ ላይ የተመሠረተ ክስና ወቀሳ በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደሆነ በማስመሰል ወያኔአዊ ተልዕኮውን ሊጭንብን ሞክሯል። እንዲህም ሲል ሊያስፈራራን ይሞክራል።

«የትግራይ ህዝብን የአምባገነኑ መደብ አጋር አድርጎ የሚያይ ሽባ አመለካከት ከሽባነቱ አልፎ የጋራ ትግሉን አደናቃፊ በመሆኑ አጥብቆ ይቃወመዋል። የኢሕአዴግ ገዥ ቱጃሮችን በማንበርከክ የሥልጣን ባለቤት ለመሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርገውን ትንቅንቅ ለመበረዝና የሚካሄደው ትግልን ተራ የብሔሮች ቅራኔ በማስመሰል አንዳንድ ቡድኖች ለፕሮፓጋንዳ፣ ለፖለቲካና ለንብረት ፍጆታ ሲሉ ትግሉን ጥላሸት ሊቀቡት የሚዳዱ አደናቃፊዎችም በጊዜ ሃይ ሊባሉ ይገባል።» ሲል ያስጠነቅቃል።

እነዚህን ሁለት አረፍተ ነገሮች አፍታትተን የያዙትን ፍሬ ነገር ከገለባው አበጥረን እንመርምር። «የትግራይ ህዝብን የአምባገነኑ መደብ አጋር አድርጎ የሚያይ ሽባ አመለካከት ከሽባነቱ አልፎ የጋራ ትግሉን አደናቃፊ በመሆኑ አጥብቆ ይቃወመዋል።» በመጀመሪያ ደረጃ ወያኔ የተደራጀው በዘር እንጂ፣ በመደብ ወይም በሀብት ክፍፍል ልዩነት ላይ አይደለም። በመሆኑም ደጋፊዎቹ፣ የሰው ኃይል ምንጩ፣ የገንዘብ ምንጩ፣ የመረጃ አቅራቢው፣ የሀሳብ ደጋፊው ትግሬ ነው። አባሎቹም በነቂስ ትግሬዎች ናቸው። ይህን አረጋዊ እና ግደይ ሊክዱን አይችሉም። ከካዱም «ክህደት የዘር ነው እንዴ?» ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል። ወያኔ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ይፋ እንደሆነው፣ በትግራይ ክፍለሀገር ውስጥና ውጭ ከሚኖረው ትግሬ የወያኔ አባል ያልሆኑት ከሃያና ኃምሣ አይበልጡም። እነዚህም መውጫ ያገኙት ሲሰደዱ፣ መውጣት ያልቻሉት ኃብት ንብረታቸውን ተወርሰው ለዘመናት በትግራይ እስር ቤቶች እንዲማቅቁ ተደርገዋል። አቶ አብርሃ በላቸው፣ አቶ ኃይሌ ኪሮስ አሰግድ፣ ወይዘሮ ዙፋን፣ ወይዘሮ ኤልሳ ተስፋየ ወዘተርፈ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ድርጅቱ ከምሥረታው ጀምሮ ዘረኛና ጎጠኛ ከመሆኑ የተነሳ፣ ለመጀመሪያዎች አምስትና ስድስት ዓመታት ምልመላ የሚያካሂደው ከአድዋ፣ አክሱምና ሽሬ ተወላጆች ብቻ ነበር። በዚህም የተነሳ ድርጅቱ ዐሽአ (ዐድዋ፣ ሽሬ አክሱም) በሚል ተለዋዋጭ ስም ይታወቅ ነበር። ይኸም ሆኖ የምልመላ ቅድሚያ የሚሰጣቸው በእናት በአባታቸው ትግሬ ለሆኑት ነበር። የነዚህን አውጃራ ተወላጆች መልምሎና በዓላማው ሥር ካሰለፈ በኋላ ወደሌሎቹ አውራጃዎች ሲጓዝ የምልመላ ቅድሚያ የተሰጠው አሁንም በእናትም በአባትም ትግሬ ለሆኑ፣ ቀጥሎ በአባታቸው ወገን ትግሬ ለሆኑ፣ እነዚህን የጥፋት ዓላማቸው ተሸካሚዎች አድርገው ሲጨርሱ፣ በእናት ወገን ትግሬ የሆኑትን መመልመላቸው ይታወቃል። ከዚህ አንፃር ወያኔ ከዘረኝነት አልፎ ለሴቶች ያለውን ዝቅተኛ አመለካከትና ልዩነት በግልጽ ያሳያል። በዚህ ሂደትም «ድፍን የትግሬ ተወላጅ፣ ወዶም ይሁን ተገዶ የወያኔ ዓላማ አራማጅ አልነበረም፣ አልሆነም» የሚሉ ካሉ ከዕውነት በተቃራኒ የቆሙ የጥፋት መልዕክተኞች ብቻ ናቸው።

የትግሬ ዘር ለወያኔ የሰው ኃይል፣ የገንዘብ፣ የመረጃና መሰል ጉዳዮች ምንጭ ባይሆን ኖሮ፣ ወያኔ ከዚህ ደረጃ መድረስ አይችልም ነበር። ይህን በተመለከተ ወያኔ ስልጣን በያዘ ማግስት መለስ ዜናዊ ለትግራይ ሕዝብ በመቀሌ አደባባይ «ከእናንተ በመወለዳችን ኮርተናል፣ ወርቆች ነን» ሲል የገለጸው ከሕዝቡ ያገኘው ድጋፍ ሠፊ እንደሆነ ያረጋግጣል። ከዚህም በተጨማሪ፣ የአውሮፓ የትግሬዎች ማኅበር በመግለጫው ይፋ እንዳደረገው፣ በ17 ዓመቱ የወያኔ ትግል 60,000(ስድሣ ሺህ) የትግራይ ወጣቶች በጦርነቱ መሞታቸውን፣ 170,000(አንድ መቶ ሰባ ሺህ) መቁሰላቸውን ይፋ አድርገዋል። እንግዲህ በሕይዎት ያሉትን ስንጨምር ነገዱ አለው ከሚባለው 5 ሚሊዮኑ ውስጥ አንድ ሚሊዮኑ በቀጥታ በትጥቅ ትግል መሳተፉንና ቀሪው በልዩ ልዩ መስኮች ድርጅቱን ይረዳ እንደነበር የማይሞተው ታሪካችን እያሳየን ነው። እና «የትግራይ ሕዝብ ለወያኔ አልረዳም» የሚለው አባባል ተራ ማጭበርበርና በሕዝብ ስም ድብቅ ዓላማን ለማራመድ ከመጣር ተለይቶ አይታይም። መባል ያለበት፣ «የትግራይ ሕዝብ ወዶም ሆነ ተገዶ፣ አምኖም ሆነ በጊዜው ስሕተት ለወያኔ መሣሪያ መሆኑ ዕውነት ነው። ይህ ደረቅ ሐቅ ነው። ግን ሕዝብን እንደሕዝብ በጠላትነት መፈረጁ ለፖለቲካዊ ትክክለኝነትና ለወደፊቱም የአብሮነት ጉዞ መልካም ስለማይሆን ሕዝቡን ከዋነኞቹ አጥፊዎቹ ልጆቹና የድርጅቱ አመራሮች እንለይ» የሚለው ነው። ይህን ለመለየት ደግሞ፣ ሕዝቡ ራሱ የልጆቹን ዕኩይና አጥፊ ተግባር ከምክር ጀምሮ እስከ ውግዘት ከዚያም በአካልና በሀሳብ ልክ እንደ ጌታቸው ረዳና ገብረመድኅን አርኣያ በይፋ ተቃውሞውን ማሳየት ይጠበቅበታል። ይህ በሌለበት ሁኔታ ሕዝቡን ከወያኔ ለይቶ ለማየት ከማስቸገሩም በላይ፤ ሕዝቡ በወያኔና ተባባሪዎቹ ላይ ቁጣውን ሲገልጽ «የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት ነው» ብሎ መፈረጅ፣ ከወያኔነት የተለየ አድራጎት አይደለም።

በሌላ በኩል «ወያኔ ኢትዮጵያን አጠፋ፣ ሕዝቡን በዘር ለያይቶ አገሪቱን በተነ፤ በዐማራው፣ በኦሮሞው፣ በጋምቤላውና በሱማሌው ነገዶች ላይ የዘር ፍጅት ፈጸመ» ብለው የሚጮኹትን ግለሰቦችና ቡድኖች የሚያራምዱትን አመለካከት «ሽባ » ከማለት አልፎ፣ «የጋራ ትግሉን ያደናቅፋል» በማለት የአዞ እንባ «ለጋራ ትግሉ ያነባል።» የእነዚህ ወገኖች አቋም በገሐድ የሚታይን የጥፋት እርምጃ መቃወም እንጂ፣ ጎጂ አመለካከት ወይም አጥፊ ርዕዮተ-ዓለም አይደለም። በነባራዊ ዓለም በገሐድ የሚታይን የጥፋት ጉዞ መቃወም «ሽባ» ካስባለ፣ አረጋዊና ግደይ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ በመቶ ኦመት በመገደብ፣ «ኤርትራ በኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት የተያዘችና ናት፤ በመሆኑም መገንጠል አለባት፤ የትግራይ ሕዝብ ራሱን ችሎ ይስተዳደር ነበር፣ ስለሆነም ከኢትዮጵያ መገንጠል አለበት፤» ብለው የጻፉና የተናገሩ ምን ሊባሉ ይሆን? ትውልድ ይታዘብ። በወያኔ ድርጊት ላይ የተቃውሞ ድምፅ ያሰሙትን ወገኖች በሽባ አመለካከት የፈረጁ ሰዎችና ድርጅቶች አቋም ስንመረምር፣ «ዝንጀሮ የራሱን ጠባሳ ሳያይ፣ በጓደኛው ይስቃል» የሚለውን አባባል ያስታውሰናል። እናም በሽባ አመለካከት የዘር ፖለቲካ ተወልደው ያደጉት አረጋዊና ግደይ ሌሎችን «ሽባ» ሲሉ፣ የራሳቸውን ማንነት ሕዝቡ የማያውቅ መስሏቸው ስለሚሆን ልካቸውን እንዲያውቁ ማድረግ ተገቢ ይመስለናል። ይህ አባባላችሁ ሕዝቡ የከረረ አቋም እንዲይዝ የምትገፋፉት እንጂ እንዲለዝብ የማያደርግ ስለሆን እንድታስቡበት ግድ ይላችኋል። ይህ አባባላቸው ሕዝቡ የከረረ አቋም እንዲይዝ የሚገፋፋ እንጂ፣ እንዲለዝብ የማያደርግ ስለሆነ፣ በወያኔዎችና በተላላኪዎቻቸው ላይ የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። «የማን ቤት ፈርሶ የማን ይበጅ፤ ያውሬ መውለጃ ይሆናል ኢንጂ!» የሚለውን የቆየ የአባቶቻችን ይትባህል ልብ እንድትሉ ልናሳስባችሁ እንወዳለን። ፋሲል ደመወዝ «አረሱት ሁመራን፣ አረሱት መተማን፣ ያውም የእኛን ዕጣ፣ እነርሱ ምን ያርጉ ከእኛ ሰው ሲታጣ» ሲል ያዜመው ዜማ ባዶ ሰሚ ያጣ ሙዚቃ እንዳይመስላችሁ። ከእኛም ሰው መኖሩን የሰሞኑ የጎንደር ሕዝብ ነውጥ፣ ያሳያችሁ ይመስለናል። ወያኔና ተከታዮቹ ምን ቢደረግ ልትሰሙ ብቻ ሳይሆን፣ ልትፈሩ እንደምትችሉ የሰሞኑ የትግሬዎች ማኅበራትና ድርጅቶች ውካታ እና እሪታ ከበቂ በላይ ማሳያ አያስፈልገውም። ስለሆነም የተነጠቅነው መብታችን፣ መሬታችን፣ ማንነታችን እስኪመለስ ድረስ በሚገባችሁ ቋንቋ ለማነጋገር እንደሚቻል ሕዝቡ ቁርጠኝነቱን አሳይቷችኋል፣ ለወደፊትም ይቀጥላል።

ሁለተኛው ሀሳብ «የኢሕአዴግ ገዥ ቱጃሮችን በማንበርከክ የሥልጣን ባለቤት ለመሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርገውን ትንቅንቅ ለመበረዝና የሚካሄደው ትግልን ተራ የብሔሮች ቅራኔ በማስመሰል አንዳንድ ቡድኖች ለፕሮፓጋንዳ፣ ለፖለቲካና ለንብረት ፍጆታ ሲሉ ትግሉን ጥላሸት ሊቀቡት የሚዳዱ አደናቃፊዎችም በጊዜ ሃይ ሊባሉ ይገባል።» የሚለው የተጥመለመለ ሀሳብ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ኢሕአዴግ የሚባል ድርጅት የለም። ኢሕአዴግ የሚባል ድርጅት አለመኖሩን ሥብሃት ነጋ በተለያዩ ሬዲዮ ጣቢያዎች ባደረገው ቃለ ምልልስ ነግሮናል። በመሆኑም ኢሕአዴግ የወያኔ የሕዝባዊ ድርጅቶች ስብስብ የሆነ መሣሪያ እንጂ፣ ገዥው ድርጅት ሕወሓት/ወያኔ ነው። ይህን አረጋዊና ግደይ ይጠፋቸዋል ተብሎ አይጠረጠረም። የልጅነት ዕድሜአቸውን ያሳለፉበት የወያኔ ድርጅትና በዚህም ተጠቃሚ የሆነው ብዙኃኑ የትግራይ ሕዝብ እንዲነካባቸው ስላልፈለጉ፣ የጥፋቱን የአንበሣ ድርሻ ለአሽከሮቹ ለማሸከም በማቀድ የተጠቀሙበት የማታለያ ዘዴ ነው። የሚታለል ካለ! በነአረጋዊ አገላለጽ የሚያሳዝነውና እነርሱንም ከከፍተኛ ግምት ውስጥ የሚጥላቸው «–የሚካሄደውን ትግል ተራ የብሔሮች ቅራኔ በማስመሰል አንዳንድ ቡድኖች ለፕሮፓጋንዳና ለንብረት ፍጆታ ሲሉ ትግሉን ጥላሸት ሊቀቡት የሚዳዱ አደናቃፊዎች በጊዜ ሃይ ሊባሉ ይገባል፤» የሚለው ነው።

አረጋዊ በርሔና አጋሩ ግደይ ዘርኣጽዮን የሚመሩት ድርጅት ሮማን ፕሮቻስካ የተባለው የኦስትሪያ-ሐንጋሪ ቆንሲል የሞሶሎኒ መልዕክተኛ ሆኖ፣ እኤአ በ1935 ባሳተመው መጽሐፍ «ኢትዮጵያ የብሔረሰቦች እስር ቤት» እንደሆነች፣ አሳሪውም «ዐማራው» እንደሆነ፣ «ለእያንዳንዱ ብሔር የመገንጠል መብት ቢሰጠው ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንደማትኖር» የጻፈውን፣ ዋለልኝ መኮንን እንደ ደረቅ ሐቅ ተቀብሎ፣ በተማሪው እንቅስቃሴ ውስጥ ነዝቶ ዛሬ በአገራችንና በዐማራው ነገድ ላይ የደረሰውን ጥፋት የወለደ መሆኑ ይታወቃል። የዚህ ዓላማ አራማጅ የሆነው ወያኔና መሥራቹ አረጋዊ፣ «የኢትዮጵያ መሠታዊ ችግር የብሔር ጭቆና ነው። ጨቋኙም ዐማራ ነው። የትግሬ ብሔር በነቂስ ተደራጅቶ ዐማራውን ማጥፋት አለበት» የሚል ፕሮግራም አዘጋጅቶ፣ በአገሪቱና በዐማራው ነገድ ላይ ከፍተኛ የጥፋት ተግባር ከፈጸሙ በኋላ፣ ሕዝቡ የጥፋት ጉዞውን ለመግታት ሲንቀሳቀስ፣ እንቅስቃሴው በጥፋት ኃይሎችና ቡድኖች ላይ ትኩረቱን ሲጥል፣ በብሔሮች መካከል ያልነበረውን ቅራኔ እንደነበር አድርገው ስለው በዐማራውና በሌሎች ነገዶች ላይ የዘር ፍጅት ከተፈጸመ በኋላ፣ «የሚካሄደው ትግል ተራ የብሔሮች ቅራኔ በማስመሰል» የሚለው አገላለጽ፣ ፍፁም ክህደት ከመሆኑም በላይ ተራ ማጭበርበር ነው። ፍረዱ ወገኖቼ፣ ዛሬ በአገራችን ውስጥ ከወያኔ ጋር የሚደረገው ግብግብና ትንቅንቅ የመደብ ትግል ነው? የርዕዮተ ዓለም ነው ፍትጊያ ወይ? ትንቅንቁና ግብግቡ በነገዶች መካከል አይደለም ወይ? ወያኔ የትግሬን ዘር አደራጅቶና አስታጥቆ በአጋዚ ሠራዊት የሚጨፈጭፈው ዐማራ፣ ኦሮሞ፣ ሶማሊ፣ አኙዋክ፣ ኑኤር፣ ወዘተርፈ የመደብ ጠላት ነው? መቼም አረጋዊና መሰሎቹ «አዎ!» እንደሚሉን አንጠራጠርም። ገና ጧት ወያኔ በረሃ ሳይገባ ትግሉን «በብሔሮች መካከል ማድረግ እንዳለበት» አምኖና ወስኖ፣ በዚህም «የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር» የሚል ስም ሰጥቶ ነገዱን በዙሪያው አሰልፎ በሌሎች ነገዶች ላይ ጦርነት አውጆ፣ የዘር ፍጅት ከፈጸመ በኋላ፣ ፍጅቱ እሳቱን ወዳነደዱት ክፍሎች ሲዞር፣ ከቅራኔ አልፎ ተፃራሪ ደረጃ ሲደርስ፣ «ትግሉን ተራ የብሔሮች ቅራኔ በማስመሰል» ማለት ምን ማለት ነው። ዐማራው፣ ኦሮሞው፣ ሶማሌውና መሰሉ ሲሞት ለነገ አረጋዊ የጽድቅ ሥራ ነው። እነዚህን የገደሉ ሰዎች «ተው! ግድያችሁን አቁሙ፤ በልክ ሁኑ፣ ሕግ ይዳኛችሁ!» ሲባሉ፣ ወንጀል እና በትግሬ ዘር ላይ እንደተዘመተ ዕኩይ ተግባር ሊቆጠር ነው። ይህ ዓይነቱ አቋም ነው የትግሬን ትውልድ የሌሎች ነገዶች ተወላጆች ከጥርጣሬ አልፈው «ሁሉም የወያኔ አባሎችና ተባባሪዎች ናቸው» ብለው እንዲያስቡ የሚያስገድደው።

በመሆኑም በነአረጋዊ በርሔ ድርጅት የወጣውን የመግለጫ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ ለጎንደር ሕዝብ ድጋፍ የወጣ ሳይሆን፣ አጥፊውን የወያኔ ቡድን ሕዝቡ እንዳይቃወም ለማስፈራራት፣ «ወያኔን ከነካችሁ እኛ አለንባችሁ» በሚል ስሜት እንድንገነዘበው አድርጎናል። ስለሆነም በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ፣ ከሁሉም በላይ ወጣቱ የዐማራ ትውልድ «የትግራይ ዴሞክራሲዊ ትብብር» የተሰኘው ድርጅትና መሪዎች ከመለስ፣ ከስብሐት፣ ከዐባይ ፀሐየ እና መሰሎቻቸው የማይለዩ፣ የወያኔ አገዛዝ እንዲቀጥል በአማራጭነት የተሰለፉ መሆኑን አውቆ እንዲታገላቸው ጥሪአችን እናቀርባለን። በተለይ «ሸንጎ» የተሰኘው የድርጅቶች ስብስብ ይህንም ድርጅት አቅፎ የያዘ በመሆኑ ቆም ብሎ ራሱን በመፈተሽ ትብብሩን ከዕውነትኛ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር እንዲያደርግ እንጠይቃለን።

ሁለተኛ፦ በአውሮፓ የትግሬዎች ማኅበር፦

ይህ ማኅበር የጎንደሩን ሕዝባዊ አመጽ በመቃወምና ወያኔ በሕዝቡ ላይ የጥፋት ክንዱን እንዲያነሳ፣ ንብረታቸው ለወደመባቸው የወያኔ አባሎችና ሰላዮች አስተዳደሩ ካሣ እንዲከፍል ጥሪ ያደረገውና ለዚህም ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ ያሳወቀ ነው። ይህ ዘረኛ የትግሬዎች ማኅበር Friday, 15th of July 2016 በተጻፈና «በቅርቡ በጎንደር ከተማና አካባቢዋ በተከሰተው አውዳሚ ሁከት አስመክቶ (አስመልክቶ ለማለት ይመስላል) የተሰጠ መግለጫ፣» በሚል ርዕስ ባወጣው የእሪታ መግለጫ፣ የወያኔ ቱባ ባለሥልጣኖችና ተማርን የሚሉ ልጆቹ በብዙኃን መገናኛ መሣሪያዎች ፊት እየቆሙ፣ «ሕወሓትን እና የትግራይን ሕዝብ» መለየት አይቻልም እያሉ የነገሩን ደረቅ ሀቅ መሆኑን እንድንገነዘብ፣ በወያኔና በሕዝቡ መካከል ልዩነት እንደሌለ እንድንረዳ አድርጎናል። ይህ ማኅበር ባወጣው በዚህ መግለጫው እንዲህ ይለናል፦

«—-ኩሩና ታጋሽ የትግራይ ህዝብ ለዓመታት ሲጠነሰስ የቆየ ጥላቻ በቅርቡ በጎንደርና አካባቢዋ በሂወቱና ንብረቱ አሳፋሪና አሳዛኝ የሆነ ከባድ የጥፋት ድርጊት ሲከናወን ለመመልከት በቅተናል። ስልጣን እንጂ የሃገር፤ የሕዝቦች ሰላምና ዕድገት ግድ የማይሰጣቸው ሐይሎች ለተንጋደደ የፖለቲካ ፍጆታ ሲሉ የትግራይ ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለየ ተጠቃሚ እንደሆነና የችግሮች ሁሉ ምንጭ እንደሆነ አድርገው በማቅረብና በመስበክ የጥቃቱ ሰላባ እንዲሆን አድርገውታል።»
ቀጥሎም

«በመራራው የ17 ዓመታት ትግል የትግራይ ህዝብ ከ60,000 በላይ የሂወት ከ170,000 በላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ከፍሎ ውድ ልጆቹን እንደ አብርሃም በግ ለመስዋዕትነት ያቀረበውን ሕዝብ ፍፁም ዘረኛ በሆነ የትምክህት ሃይሎች የተደጋጋሚ ጥቃቶች ሰለባ መሆኑ በጣም ያሳፍራል።»

በማለት የወያኔ ሰላዮች በመደፈራቸው የተሰማውን ቁጭት ገልፆ፣ ተጎጂዎች ላላቸው ወያኔዎች ካሣ እንዲከፈሉ፣ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸምባቸው ጥበቃ እንዲደረግላቸው፣ በጥፋቱ ተሳትፈዋል የሚባሉት ወገኖች ለሕግ እንዲቀርቡና የማያዳግም ርምጃ እንዲወሰድባቸው ይጠይቃል። «መንግሥት» ለሚወስደው ርምጃም «ከጎኑ እንደሚቆሙ» ገልጸዋል።

ከላይ የአውሮፓ የትግሬዎች ማኅበር (የአውሮፓ የወያኔ ቅርንጫፍ ማለቱ ይቀላል) ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ሀሳቦች እንፈትሽ። « ለዓመታት ሲጠነሰስ የቆየ ጥላቻ» የሚለውን ሐረግ ምን ለማለት እንደሆነ እንመርምር። ምርምራችን ትክክለኛ ውሳኔ ላይ እንዲያደርሰን «ጥላቻውን ማን ፈጠረው? ለምንስ ተፈጠረ? እንዴትስ ተፈጠረ?» የሚሉትን ጥያቄዎች አንስተን ተገቢና ትክክለኛ መልስ ማግኘት አለብን። በኢትዮጵያ ነገዶች መካከል ጥላቻና መጠራጠር እንዲፈጠር ያደረገው የትግሬ-ወያኔ ነው። ይህ አጥፊ ቡድን በ1968 ዓ.ም. ባውጣው ፕሮግራም «ዐማራው የትግራይ ሕዝብ ጠላት ስለሆነ ትግሬ ተደራጅቶ ዐማራውን ማጥፋት አለበት» በማለት ሕዝቡን የሰበከ፣ ያደራጀ፣ የመራና የፈጀ መሆኑ ግልጽ ነው። ወያኔ ከትግራይ ምድር ሲወጣ፣ ሌሎችን ነገዶች አደራጅቶ በዐማራው ላይ እንዲዘምቱ ማድረጉን የኢሕዲን(ብአዴን)፣ ኦሕዴድ፣ ደሕዴግ እና መሰሎቹ ቋሚ ነቃሾች ናቸው። በነዚህ ትብብር የአገሪቱን አስተዳደር በነገድ ሸንሽኖ ሕዝቡን ሆድና ጀርባ ያደረገው ወያኔ ነው። የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምትን ሕዝብ የፈጀ ወያኔ ነው። ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ በጉልበት ጠቅሎ ሕዝቡን ጦም አዳሪ ያደረገው ወያኔ ነው። በወልቃይት ጠገዴ ለም መሬቶችን ከዐማራዎቹ ነጥቆ ያሰፈረው ትግሬዎችን ነው። እናንተ ሰዎች፣ የለየላችሁ ከሃዲዎች ካልሆናችሁ በስተቀረ «አልተደረገም» አትሉንም። ዳሩ ግን ክህደት የዘር ይመስል፣ የወያኔ ሰዎች ፍፁም ከሃዲዎች ናችሁና ከእናንተ ዕውነት አንጠብቅም። እነዚህ የሕይዎት፣ የመብት፣ የኢኮኖሚ፣ የባህልና የማንነት ነጠቃዎች ጥላቻን መፍጠራቸው የታወቀ ነው። ጥላቻ ደግሞ አመጽን መፍጠሩ ዲያሌክቲካዊ ሂደቱ ነው። ጎንደርም የሆነው ይኸው ነው። « አሸዋ ላይ ፈሶ ጤፍ አይታፈስም፣ ምን ጊዜ ቢረዝም ቂም አይበሰብስም» ነውና ባህላችን ተጀመረ እንጂ፣ ሒሣብ ገና አልተወራረደምና በዚህ ሊገርማችሁ አይገባም። «ወንድ ልጅ፣ መቼ ይሞታል ቢሉት፣ የሠራውን የረሳ ዕለት» እንደተባለው በጎንደር ሕዝብ ላይ በተናጠል፣ በዐማራው ነገድ ላይ በጥቅል የሠራችሁትን ሁሉ አቀፍ በደል ረሳችሁት እንዴ? እናንተ ብትረሱት እኛ የችግሩ ሰላባዎች ምንጊዜም አንረሳውም። የወያኔ አረመኔአዊ ሥራ እንርሳህ ብንለውም አይረሳምና!

ሌላው አሳዛኙ ነገር ይህ የአውሮፓ የትግሬዎች ማኅበር የገለጠው፣ እነርሱ በዘረፉት የአገርና የሕዝብ ሀብት ቁንጣን ይዟቸው ሲያገሱ፣ ብዙኃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከቆሻሻ ገንዳዎች የተጣለ ትርፍራፊ በወረፋ እንደሚበላ፤ ምሳ፣ ቁርስና እራት በቤተሰብ በወረፋ የሚመገብ፤ ያም «ትንሽ አላቸው» በሚባሉ ቤተሰቦች ነው። ከሁሉም በላይ ከ15 ሚሊዮን በላይ የሆነው ሕዝብ ለርሃብ ተጋልጦ ለልመና ተዳርጎ ባለበት ወቅት፣ «ስልጣን እንጂ የሃገር፤ የሕዝቦች ሰላምና ዕድገት ግድ የማይሰጣቸው ሐይሎች ለተንጋደደ የፖለቲካ ፍጆታ ሲሉ የትግራይ ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለየ ተጠቃሚ እንደሆነና የችግሮች ሁሉ ምንጭ እንደሆነ አድርገው በማቅረብና በመስበክ የጥቃቱ ሰለባ እንዲሆን አድርገውታል።» በማለት ያሰፈሩት ሀሳብ ወያኔዎች የቱን ያህል ካለራሳቸው ጥቅም በቀር ለአገርና ለሕዝብ መብትና ጥቅም ደንታ ቢስ ስግብግብ ፍጡሮች መሆናቸውን ያሳያል። ለመሆኑ ከመንጋደድ አልፎ የወደቀ ፖለቲካ የሚያራምደው ማነው? በ21ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ላይ ሆኖ፣ የጎሣ ፖለቲካ አባቱ ማነው? ለዘር የበላይነት የሞተው ማነው? ከላይ «ስድሣ ሺህ ሞቱ፣ መቶ ሰባ ሺህ ቆሰሉ» የተባሉት እኮ፣ የትግሬን ጥቅም ለማስከበር ነው። የምናየውም ይኸው ነው። ወያኔ ወይም ትግሬ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን፣ ዐማራንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን አጥፍቶ፣ የትግሬን የበላይነት ለማንገሥ የተደራጀና ያለ እንጂ፣ ለሕዝብ ነፃነት፣ ዕኩልነት፣ አንድነትና ብልጽግና የቆመ ድርጅት አለመሆኑ፣ ከጅቡቲ መቀሌ፣ ከሱዳን መቀሌ የሚገነባው የባቡር ሐዲድ፣ ትግራይ ውስጥ የተገነቡት ዩኒቨርስቲዎች፣ ኮሌጆች፣ ሆስፒታሎች፣ ክሊኒኮች፣ ፋብሪካዎች፣ የተዘረጉት አውራ መንገዶች፣ የተገነቡት ከተሞች ወዘተርፈ አፍ አውጥተው ይናገራሉ። «የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አልተጠቀመም» የሚሉ ወገኖች «ተጨፈኑ እናሞኛችሁ» የሚሉ ብቻ ናቸው። ወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የደህንነትና የፋይናንስ ተቋሞቹ በነቂስ በትግሬ ልጆች የተያዙ ናቸው። ባጭሩ የአገሪቱ ቢሮክራሲ ከዘበኛ እና የጽዳት ሠራተኛ ጀምሮ እስከ ሚኒስተር ያሉት ቦታዎች በወያኔ አባሎች የተሞሉ ናቸው። አገሪቱ አሉኝ ከምትላቸው 65 ጄኔራል መኮንኖች መካከል 61ዱ ትግሬዎች ናቸው። ከዚህ ወዲያ ለሥልጣንና ለጥቅም መስገብገብ ምን አለ? ማለት ያለባችሁ ደረቁ ሐቅ፣ «ወያኔ የሞተውና የተደራጀው ለትግራይ ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም ነው» ብትሉ ተፈርታችሁ ዕውነትም በመናገራችሁ ተወዳችሁ ትከበሩ ነበር። ውሸት ያስንቃል፣ ያዋርዳል እንጂ፣ አስከብሮም አስፈርቶም አያውቅም።

ሦስተኛ፦ የሰሜን አሜሪካ የትግሬዎች ማኅበር ፦
ይህ ማኅበር በበኩሉ በጁላይ 14/ 2016 «በጎንደር ከተማ በተፈጠረው ረብሻ በማስመልከት ከትግራይ ተወላጆች ማሕበር በሰሜን አሜሪካ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ» በሚል ርዕስ በተጻፈ፣ በጎንደር ከተማ የተከሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ በቁጥጥር ሥር ለማዋል «መንግሥት» የወሰደውን የተቀናጀ የአፈና እርምጃ አሞግሶ፦

«–ቀጣይ እና ውጤታማ እንዲኾን የፌደራል እና የክልሉ መንግሥቶች የህዝባችንን ሰላም ለማስፈን አበርትተው እንዲሰሩ ጥሪአችን እናቀርባለን። መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንዲቀጥልና የሁከትና ብጥብጡ መሪ ተዋናዮች–ማለትም “በሕጋዊ ጥያቄ“ ሽፋን እና ስም ሕገወጥ ድርጊት ሲያከናውኑ መንግሥት የደረሰባቸው አካላት- በቁጥጥር ስር ውለው በአፋጣኝ ወደ ፍርድ እንዲያቀርባቸው እንጠይቃለን።» ይላል።

ይህ መግለጫ ከላይኞቹ የሚለየው፣ በቀጥታ የወያኔው አፈቀላጤ የጌታቸው ረዳ አባባል ግልባጭ መሆኑ ነው። በዚህ የትግሬዎች ማኅበር አገላለጽ፣ የሕዝብ ሰላም ማለት የወያኔ ሰላም ማግኘት ነው። አጥፊዎች ከተነኩ፣ ገዳዮች ከተገደሉ፣ በዝባዦችና ሌቦች ንብረታቸው ከወደመ «ሰላም ተናጋ» ይሉናል። የአምስት ሚሊዮን ዐማሮች ሕይዎት ሲጠፋ፣ ንብረታቸውን ተዘርፈው ሲባረሩ ለነርሱ ሰላም ነው። ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ «ወያኔ አገር እያጠፋና ሕዝብ እየበደለ ይኑር» የሚል በመሆኑ፣ በየትኛውም መልኩ የዐማራው ነገድ የሚገዛው አይሆንም። መግለጫው ግን አንድን ሐቅ ፍንትው ብሎ እንዲታይ ያደረገ በመሆኑ ይበል የሚባል ነው። «ትግሬና ወያኔን ለዩ» ለሚሉ ወገኖች፣ በማያሻማ መልኩ ወያኔ ማለት ትግሬ፣ ትግሬ ማለት ወያኔ እንደሆነ ሁነኛ መልስ ሰጥቷል።

አራተኛ፦ አብርሃ ደስታ፣ አስራት አብርሃም እና ሙሉዓለም ገብረመድኅን የተባሉት፦

እኒህ ሰዎች በየግላቸው «ለምን ወያኔ ይነካል» በሚል ስሜት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ያሰሙት ስሞታ ከፍ ሲል በተጠቀሱት መግለጫዎች በተሰጡት መልሶች የሚካተት በመሆኑ ዝርዝር ውስጥ መግባቱ መደጋገም ስለሚሆን ማለፉን መርጠናል። ሆኖም ግን «የወያኔ ተቃዋሚ ነው» የሚባለው አብርሃ ደስታ ያሰማው ተቃውሞ ማንነቱን በጥብቅ እንድንፈትሽ የሚገፋፋ ሆኖ አገኝተነዋል። ይህ ሰው ለሁለት ዓመት ታሥሯል። ባጭር ጊዜ መፈታቱ በራሱ ጥርጣሬ ላይ የሚጥል ነው። ምክንያቱም ከእርሱ የከፋ ያልጻፉትና ያልተናገሩት አንዱዓለም አራጌና እንስክንድር ነጋ ዐማሮች በመሆናቸው ብቻ የ18 ዓመታትና የዕድሜ ልክ እስረኛ ሲሆኑ፣ እርሱ ከሁለት ዓመት እሥራት በኋላ መፈታቱ ለወያኔ ባለው ቀረቤታና ስስ ልብ እንደሆን እንድናጤን አድርጎናል። በጥንቃቄ ከመረመርነው፥ መታሰር በራሱ የቁርጠኛ ተቃዋሚነት መስፈርት አይደለም። ለስለላና ለተለያዩ ሥራዎች ሰዎች በተቃዋሚነት ስም ይታሰራሉና። በሌላም በኩል ትክክለኛ ተቃዋሚው፣ ከዳዊት ከበደ፣ ከአብርሃም ያየህ፣ ከስየ አብርሃ እና ከነጋሶ ጊዳዳ ትምህርት መውሰድ ያሻዋል እንላለን።

የጎንደር ሕዝብ ጭቆናው፣ አፈናው፣ እስራቱ፣ እንግልቱ፣ ውርደቱ ከሚሸከመው በላይ በመሆኑ፣ ክንዱን በጨቋኞች ላይ አንስቷል። ይህ ክንድ፣ በአሉባልታና በዛቻ አይዝልም፤ አይታጠፍምም። የሚዝለውና የሚታጠፈው፣ ዕውነተኞቹ የትግራይ ልጆች፣ በጎንደር ሕዝብና በዐማራው ላይ ወያኔ የፈጸመውን ይህ ቀረው ያልተባለ ግፍና በደል አምነው፣ ዳግም እንዳይደገም ወያኔን በማውገዝ፣ ከጎኑ ሲቆሙ ብቻ ነው። ይን ሲሆን፣ ጎንደሬው፣ ከሁሉም በላይ ዐማራው፣ የይቅርታ ባህሉ እጅግ የዳበረ በመሆኑ፣ «ባለፈው ይብቃ» የማለት አቅሙ የጎለበተ ስለሆነ፣ ዕምነቱም ስለሆነ፣ በዳዮቹ የሠሩትን ጥፋት ከልብ ካመኑ፣ በይቅርታ አብሮ ለመኖር አይቸገርም። በዛቻና በማስፈራራት ግን፣ ከእንግዲህ ወዲያ ጎንደሬው «አፈርኩ» ብሏልና ባለፈው መልኩ ክብሩና መብቱ ተገፎና ተረግጦ መኖር የማይችል መሆኑን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። በማስጠንቀቂያው መሠረት ከጎኑ መቆም፣ ካልሆነም የሚሰነዝረውን ለመቀበል መዘጋጀት ነው። ምርጫው የወያኔና የትግራይ ሕዝብ ነው።

በዚህ ረገድ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ እስካሁን እንዳደረገው ሁሉ፣ ዐማራው በአንድ አዕምሮ አስቦ እንደሠራዊት በመትመም፣ ሊያጠፉት የተሰለፉትን ኃይሎች እንዳመጣጣቸው በመመከት፣ ወያኔና አጫፋሪዎቹ እንደሚሉት «ፈሪ፣ እና ሽንታም» አለመሆንክን በተባበረው ክንድህ የጎንደርን ምሳሌ በመከተል ወያኔና አጋሮቹን ልታሳያቸው ግድ ከሚልህ ምዕራፍ ላይ የደረስክ መሆንክን አውቀህ፣ ለማይቀረው የነፃነት ጉዞ ትጥቅህን እንድታበረታ ጥሪ እናቀርባለን!

የወልቃይት የጠገዴ፣ የጠለምት፣ የሑመራ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ የመላው ዐማራ ሕዝብ ጥያቄ ነው

ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ሑመራ ዐማራ ነው!

ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት  እሑድ ሐምሌ ፲፯ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም.  ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፲፰

%d bloggers like this: