Monthly Archives: November 2011

የ መለስ ዜናዊ ሚስጥሮች …..በተስፋዬ ገ/አብ14 Nov For PDF file please click here: YeZenawi-Misteroch

 በየእለቱ አዳዲስ ዜናዎች እንሰማለን። ለአብነት “ስዩም መስፍን በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነ” የሚለው ተራ ዜና ነበር። “ስዩም ተወረወረ” ብለን ያመንንም ነበርን። ስዩም ሌላ ተልእኮ እንደተሰጠው ለመረዳት፣ የቻይናና የወያኔን የንግድ ስምምነቶች ማስላትና አንዳንድ አንጓዎች ብቅ እስኪሉ መጠበቅ ያስፈልግ ነበር። አባይ ፀሃዬ የስኳርና የጨው ሚኒስትር ሆኖ ሲሾም ብዙ ስላቆች አንብቤ ነበር። የአባይ ፀሃዬን አንገት የስኳር ጆንያ ውስጥ በመክተት ያላገጡ ሜዲያዎችም ነበሩ። ሆኖም የስዩምም ሆነ የአባይ ምደባዎች ቀጣዩን የወያኔ ዋና ዋና እቅዶች ጠቋሚ ነበሩ። የስዩምን ሹመት ተከትሎ፣ የወያኔ ባለስልጣናት ልጆች ለትምህርት ወደ ቻይና ተላኩ። እነዚህን ልጆች በኮሚኒስታዊ አስተሳሰብ አደራጅቶ ማዘጋጀት የሽማግሌው የትርፍ ጊዜ ተልእኮ መሆኑ እየተሰማ ነው። ወያኔ የጦር መሳሪያ በብዛት እየገዛና እያመረተ ነው። ጦር መሳሪያ የማከማቸቱ እውነተኛ አላማ ምን ይሆን? በአባይ ጉዳይ የግብፅን ጦር ለመመከት? ይሄ የተበላ እቁብ ሆኖአል። ትግራይን ለመገንጠል ቆርጠው ወስነው፣ በሹክሹክታ እንደሚሰማው TDF (Tigray Defense Force) የተባለውን ይፋ ያልሆነ መስሪያ ቤት በምስጢር እያደራጁ ይሆን? የህወሃት ሰዎች ትግራይ በጠላት ተከባለች ብለው ማመናቸው ወይም እንዲታመን መፈለጋቸው የችግሩ ማእከል ይመስላል። Read the rest of this entry

ማርዮ ሞንቲና አዲሱ ካቢኔያቸው

የአቶ መለስ የሽብር ትንታኔ “ከጠፍሮ ማሰር” እስከ “ቁራ ጩኸት”

 

አቶ መለስ ትላንት ፓርላማ ነበሩ። ከልማት እና ልማታዊነት ጋራ የተያያዙትን ጥያቄዎች በተለመደው ካድሬያዊ ስብከታቸው ቀዝቀዝ ባለ ስሜት ሲያብራሩ ነበር። ከሽብርተኝት ጋራ ተያይዞ ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ግን እልህ፣ ቁጭት፣ ድንፋታ፣ ዛቻ እና ማስፈራርያ የታከለበት ንግግር አስደምጠዋል። ጋዜጠኞቹም ኾኑ ፖለቲከኞቹ ወንጀለኞች ናቸው ሲሉ ደምድመው ተናግረዋል። በፍርድ ቤት በተጠርጣሪነት ተይዞ ጉዳዩን የሚከታተልን ግለሰብ ከወዲሁ ወንጀለኛ ሲሉ ያለመጠራጠር […]

by Admin | 7:50 pm

 

 

አቶ መለስ ትላንት ፓርላማ ነበሩ። ከልማት እና ልማታዊነት ጋራ የተያያዙትን ጥያቄዎች በተለመደው ካድሬያዊ ስብከታቸው ቀዝቀዝ ባለ ስሜት ሲያብራሩ ነበር። ከሽብርተኝት ጋራ ተያይዞ ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ግን እልህ፣ ቁጭት፣ ድንፋታ፣ ዛቻ እና ማስፈራርያ የታከለበት ንግግር አስደምጠዋል። ጋዜጠኞቹም ኾኑ ፖለቲከኞቹ ወንጀለኞች ናቸው ሲሉ ደምድመው ተናግረዋል። በፍርድ ቤት በተጠርጣሪነት ተይዞ ጉዳዩን የሚከታተልን ግለሰብ ከወዲሁ ወንጀለኛ ሲሉ ያለመጠራጠር ተናግረዋል። በአንጻሩ ግን መረጃ ሳይዙ ጻፉ ያሏቸውን ጋዜጠኞች “ጋጠ ወጦች” ሲሉ ዘልፈዋቸዋል። ከሽብርተኝነት ጋራ በተያያዘ ያደረጉት ሙሉ ንግግር ከዚህ በታች ያለው ነው።

“በቅርቡ ስለታሰሩ ሰዎች ከጸረ ሽብር ሕግ ጋራ ተያይዞ የተነሳው ጥያቄን በተመለከተ ወደ ዋናው ጥያቄ ከመግባቴ በፊት፤ ጋዜጦች ነገሩ በፍርድ ቤት ከመታየቱ በፊት ተከሳሾቹ ነጻ ናቸው ብለው ፈርጀዋል። እና መንግሥት የተፋጠነ ክስ ባለመመሥረቱ ለእንደዚህ ዐይነቱ ችግር አስተዋጽ አበርክቷል ተብሎ ጥያቄው ላይ ተቀምጧል ይኼ ስህተት ነው።

ጋዜጠኞች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ ክሱን ሳያውቁ፤ ማስረጃውን ሳይሰሙ፤ በጭፍን ነጻ ናቸው ብለው መፈረጃቸው፣  ይኼን ማውጣታቸው ክሱ በወቅቱ ስላልተመሠረተ የተፈጠረ አይደለም። የጋዜጠኝነት ሀሁ የማይገባቸው ወይም እንዲገባቸው የማይፈልጉ ጋጠ ወጦች ስለኾኑ ብቻ ነው። መንግሥት በሕግ በተቀመጠው ቀነ ቀጠሮ፣ በሕግ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እነዚህን ሰዎች ለፍርድ ያቀርባቸዋል፤ እያቀረባቸውም ነው። የጋዜጠኛ የመጀመርያ ስነ ምግባር የሁለቱን ወገኖች አስተያየት መስማት ነው። ነገሮችን በጥሞና ማጥናት ነው። ማስረጃዎችን መፈተሽ ነው። ይኼን ሳያደርጉ ዘሎ አለመጻፍ፤ አለመናገር ነው፤ የጋዜጠኝነት ስነምግባር የሚጠይቀው ይኼን ነው። ይኼን ስነ ምግባር አልፈው የሚንጣጡ ጋዜጠኞች ካሉ ችግሩ የራሳቸው ነው። የሚንጣጡ ጋዜጠኞች ካሉ ችግሩ የራሳቸው እንጂ ለፍርድ ቤት ማቅረብ ላይ መዘግየት ስለታየ አይደለም። እዚህ ላይ ግልጽ መኾን ያስፈልጋል።

ወደ ዋናው ጉዳይ ለመመለስ ባሁኑ ሰዓት በአገራችን የሚካሄደው የሽብር እንቅስቃሴ ሦስት ዋና ዋና ተዋንያን አሉት። አንደኛው እና ዋናው ሻዕቢያ ነው። የኤርትራ መንግሥት ነው። የዚህ ቡድን አቋም ምን እንደኾነ ሕብረተሰቡ የሚያውቀው ይመስለኛል። ያንን መደጋገም የሚያስፈልግ አይመስለኝም። አቋሙ አልተቀየረም፤ አሁንም፣ ዛሬም፣ ትላንትም ከትላንት በስተያም ይኼንኑ የማተራመስ ስትራቴጂ፣ ይኼንኑ የሽብር ስትራቴጂ ይዞ ነው እየሠራ ያለው።

ሁለተኛው ሻዕቢያ በቀጥታ የሚያሰማራቸው ነጭ ለባሾች ናቸው። አልሸባብን ይመለከታል፣ ራሱን ግንቦት ሰባት ብሎ የፈረጀውን ቡድን ይመለከታል። ኦነግን ይመለከታል፣ ኦብነግን ይመለከታል። ይኼ ፓርላማ ሽብርተኛ ብሎ ያስቀመጣቸው ድርጅቶች በሙሉ መናኸሪያቸው አሥመራ ነው። አሥመራ በተቀየሰው ስትራቴጂ መሠረት ነው የሚንቀሳቀሱት፤ ከአሥመራ በሚሰጣቸው ገንዘብ ነው የሚንቀሳቀሱት፣ ከአሥመራ በሚቸራቸው መሣርያ ነው የሽብር ተግባሩን የሚያከናውኑት። እነዚህ ሁለቱ በጣም የታወቁ ተዋንያን ናቸው።

ሦስተኛዎቹ ተዋናዮች ለእነዚህ ሽፋን የሚኾኑ በሰላማዊ መንገድ እንሠራለን ብለው፤ ያወጁ ድርጅቶች ናቸው። ቅድም ሲነሳ እንደነበረው መድረክ የተባለው ድርጅት በሰላማዊ መንገድ መሥራት ያምናል። ወሳኝ ነው ብሎ ያምናል ተብሏል፤ ጥሩ ሐሳብ ነው። ክፋቱ አንዳንድ የመድረክ መሪዎች (ስለ አባላት ብቻ አይደለም የማወራው) አንዳንድ የመድረክ መሪዎች ከእነዚህ ከሻዕቢያ ነጭ ለባሾች ጋራ በመተሳሰር በሕጋዊ ፓርቲ ሽፋን የእነ ኦነግ፣ የእነ ኦብነግ፣ የእነ ግንቦት ሰባት አባላት እና አስፈጻሚዎች ኾነው እየሠሩ ነው። በተጨባጭ!!!

አሁን የታሠሩ ሰዎች አሉ፤ እነዚህ የታሰሩ ሰዎች የአሸባሪ ድርጅቶች አባላት በመኾናቸው ብቻ አይደለም የታሰሩት፣ የአሸባሪ ድርጅት አባላት ስለመኾናቸው ፍርድ ቤት ሊያሳምን በሚችል ማስረጃ ስላረጋገጥን ነው የታሠሩት። የእነዚህ የሽብር ድርጅቶች አባላት መኾናቸውን የምናውቃቸው፣ እያወቅናቸው፤ እያወቅን፣ እያየን እንዳላየን ዝም ብለን የምናልፋቸው ግን ከእነርሱ በላይ ናቸው ቁጥራቸው። ዝም ብለን እያየን፣ እያወቅን፣ ማ የምን ድርጅት አባል መኾኑን በደንብ እያወቅን፣ ያላሰርንበት ምክንያት ምንድን ነው ቢባል ሁለት ምክንያት ነው። አንደኛው ሰዶ ማሳደድ ውስጥ ከመግባት የምንወስደውን ርምጃ በአደጋው ልክ ብናደርገው፣ በአደጋው ልክ ማለት፤ የኾነ የአሸባሪ ድርጅት አባል ኾኖ በተጨባጭ ወደ አደጋው ሊያደርስ ሥራ ካልሠራ፣ አባል መኾኑ ራሱ ወንጀል ቢኾንም በተጨባጭ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ካልገባ ሰዶ ማሳደድ አያስፈልግም፤ ረጋ ብለን እንየው።

ሁለተኛው አሸባሪ መኾኑን እያወቅን እኛ ማወቃችን ብቻ በቂ አይደለም። በፍርድ ቤት ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ መቻል አለብን። በፍርድ ቤት ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ከሌለን የትም ቦታ አንደርስም። በዚህ ምክንያት በፍርድ ቤት ሊቀርብ የሚችል ማስረጃ ስላላገኘንባቸው ዝም ያልናቸው አሉ። ማስረጃ እስኪገኝ ድረስ ዝም ያልናቸው አሉ። እስካሁን ከታሰሩት ግን የአሸባሪ ድርቶች አባላት ለመኾናቸው አሳማኝ ማስረጃ የሌለበት አንድም ሰው አልታሠረም። አንድም፤ ሰሞኑን ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። እነዚህን ሰዎች ለማሰር ብንፈልግ፣ ዓላማችን እነዚህን ሰዎች ማሰር ቢኾን ኖሮ ስለ ሽብር ስለምናምን ማውራት አያስፈልገንም ነበር። ብዙዎቹ እነዚህ ሰዎች በምህረት የተለቀቁ ናቸው። በምህረት ሲለቀቁ የገቡት ቃል አለ። ይቺን ቃል ተላልፈን ከተገኘን ምህረቱ ይሰረዛል፤ እስር ቤት እንገባለን የሚል ፈርመው ነው የገቡት። በቅድመ ኹኔታ  ነው የተፈቱት፤ እያንዳንዳቸው በየቀኑ የገቡትን ቃል እያፈረሱ ነው የሚውሉት። በሚሰጡት መግለጫ፣ ሁሉንም ጥፍር አድርገን እስር ቤት ማስገባት እንችላለን። ሕጉ ይፈቅድልናል። እነሱ ራሳቸው የፈረሙት ሰነድ ያረጋግጣል። ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን፣ በሕገ መንግሥቱ የተደራጁትን ተቋማትን አከብራለሁ፣ ምን አረጋለሁ፣ ምን አረጋለሁ ብለው ቃል የገቡት በየቀኑ ሲሽሩት መዐት ማስረጃ አለ፤ በየጋዜጣው። ፍርድ ቤት መሄድ አያስፈልግም፤ በቀጥታ ወደ ይቅርታ ቦርድ ተወስደው ይቅርታ የተሰጠበትን ሥርዐት ጥሰዋል አልጣሱም የሚለውን ማረጋገጥ ብቻ ነው። ይኼን ማረጋገጥ በጣም ቀላል ነው። ይኼን በማረጋገጥ የመድረክን ከፍተኛ ክፍል፣ አመራሩን ማስገባት እንችላለን እስር ቤት። ስለ ሽብር ስሌላ ሳናወራ። ይኼን አላደረግንም። ይኼን ያላደረግንበት ምክንያት አሁንም በሂደት እየረገቡ፣ እየገባቸው ይሄዳል። ሰዶ ከማሳደድ እንቆጠብ። ከግለሰቦች ጋራ አታካራ መግባት አያዋጣንም፤ አጠቃላይ ኹኔታውን እንይ፣ አጠቃላይ ሥርዐቱን ጥቅም እናስቀድም በሚል ነው። አለበለዚያ እነዚህ ድርጅቶች በተለይ የተወሰኑ የመድረክ አባል ድርጅቶች ውስጥ ያሉ አመራሮች፣ ማ የየትኛው አሸባሪ ድርጅት አባል እንደኾነ በዝርዝር ነው የምናውቀው። በምናውቀው ልክ ርምጃ አንወስድም!!! በምናውቀው ልክ ርምጃ ያልወስደነው ቅድም እንደገለጽኩት ነው።

በተመሳሳይ አንዳንድ ጋዜጠኞች ከየትኛው የአሸባሪ ድርጅት ጋራ እንደሚገናኙ፣ ምን ዐይነት መመርያ እንደሚሰጣቸው፣ ምን ዐይነት አቅጣጫ እንደሚቀየስላቸው፣ እናውቃለን። እያወቅን በምናውቀው ልክ ርምጃ አልወሰድንም። በተመረጠ አኳኋን ግን ርምጃ ወስደናል። እነዚህ ሰዎች ምን እንደሠሩ፣ እንዴት እንደሠሩ፣ በጣም በቂ ማስረጃ አለን። ባለፈው ጊዜ ሻዕቢያ የተወሰኑ የኦነግ ሰዎችን ልኮ አዲስ አበባን ባግዳድ አደርጋለሁ ብሎ በሚንቀሳቀስበት ወቅት ተመሳሳይ ጥያቄ ተነስቷል። ነገር ግን በእጃችን የነበረው ማስረጃው ስፍር ቁጥር የሌለው ማስረጃ ነበር፤ ፈንጁም ትጥቁም ምኑም በሙሉ በእጃችን ነው የገባው።

አሸባሪዎቹ ከኤርትራ ሐላፊዎች ጋራ የሚያደርጉት ግንኙነት ጭምር በእጃችን ነው የገባው። ይህን ማስረጃ ነው ለተባበሩት መንግሥታት አሳልፈን የሰጠነው። የተባበሩት መንግሥታት በዚህ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ ነው (ለምሳሌ አንዱ ጠመንጃ ከሮማንያ የተገዛ፤ የኤርትራ መንግሥት ከሮማንያ የገዛው መኾኑን አጣርቶ መሣርያው ከኤርትራ መንግሥት ብቻ ነው ሊሸጥ የሚችለው፤ ቁጥሩ አለ ምኑ አለ፤ የተሠራው ሮማንያ እንደኾነ አረጋገጡ፣ ጠየቁ ሮማንያ ለኤርትራ ይኼን መሣርያ በዚህ ጊዜ ሸጥንላቸው ብለው ሰነዱን አመጡ፤ በዚህ ሰንድ ላይ ተመስርተው የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያን በሽብር ለማተራመስ ሠርቷል ብለው የተባበሩት መንግሥታት ተቆጣጣሪ አካል ነው በይፋ ሪፖርት ያደረገው። በእንደዚህ ዐይነት መረጃ ላይ የተመሠረተ ሥራ ነው እየሠራን ያለነው።

እነዚህም ተመሳሳይ ማስረጃ አላቸው። ሰሞኑን ለፍርድ ይቀርባሉ፤ ለነገሩ ለመጀመርያ ጊዜ ፍርድ ቤት ከቀረቡ ቆይተዋል፤ ነገር ግን ክሱ በቅርቡ ይመሠረታል ብዬ ነው የምገምተው፤ እና ጉዳዩ በተከታታይ የሚታይ ይኾናል ማለት ነው። ስለዚህ ከዚህ ጋራ በተያያዘ ምህዳር ለማጥበብ፣ ምን ለማድረግ ምን ለማድረግ እየተባለ የሚደረገው ጨኸት የቁራ ጩኸት ነው። በትክክል በዚህ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች ግልጽ መልእክት ነው ለማስተላለፍ የምፈልገው። ማሰር ብንፈልግ ከመጠን በላይ በቂ ምክንያት አለን። ለማሰር ማ የየትኛው ድርጅት አባል እንደኾነ በዝርዝር እናውቃለን። ስለታገስን ያላወቅን የሚመስላቸው ካሉ እየተሳሳቱ ነው። መርጦ ርምጃ መውሰድን ስለመረጥን ብቻ ነው። ምናልባት መንግሥት ማስረጃ አይኖረም ይኾን ወይ ብለው በንጽሕና የሚጠራጠሩ ካሉ ደግሞ ትንሽ ይታገሱ። አንድ ሁለት ሳምንታት ይታገሱ፤ ማስረጃ እስኪቀርብ ድረስ። አሳማኝ ማስረጃ ሳይዝ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ አይገባም። ባለፈው ጊዜ እንደነበረው ሁሉ አሳማኝ ማስረጃ ይዞ ነው የሚገባው። የሚሠሩት ድራማ በዝርዝር መገለጹ አይቀርም። ለነገሩ የቁርጥ ቀን ሲደርስ ከዚያ በፊት ሲፎክር የነበረ ሰው በሙሉ እንደፎከረ ይቀጥላል ማለት አይደለም። ቁርጥ ቀን ሲደረስ፣ በማስረጃ እጅ ከፍንጅ ሲያዝ መዝፈን የሚጀመር ሰው ይኖራል፤ ስለዚህ ዘፈኑም ፉከራውም በዝርዝር ይቀርባል። ትንሽ ትዕግስት ብቻ ነው የምንጠይቀው።

 

መንግስት በእስልምና ሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት በጊዜ ካልተገታ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠረው መዘዝ ተጠያቂ ነው ሲሉ በካናዳ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊሞች ገለጡ

ህዳር 4 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-መንግስት በእስልምና ሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት በጊዜ ካልተገታ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠረው የሙስሊሞች መከፋፈልና በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ላይ ለሚያመጣው መዘዝ ተጠያቂ ነው ሲሉ በካናዳ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊሞች ገለጡ::

ኦክቶበር 30፣ በቶሮንቶ አካባቢ የሚኖሩ በርካታ ሙስሊሞች ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ ባወጡት መግለጫ ፤ ”  የኢትዮጵያ መንግስት በፌደራል ሚኒስትሩ ቢሮ አማካኝነትና ሕዝብ ባልወከላቸው ግለሰቦች በሚመራውና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጠቅላይ ምክር ቤት ተብሎ በሚጠራው ቡድን አስተባባሪነት፤ በጥመቱና ከእስልምና መንገድ በመልቀቁ በዓለም ባለ የሙስሊሙ ኡላማወች  የተረጋገጠበትን የአሕባሽን አመለካከት፤ የመላ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መርህ እንዲሆን የሚደረገውን ጫና በጽኑ ተቃውመዋል።”

ሙስሊሞቹ ሰፊ ወይይት ካደረጉ በሁዋላ ባወጡት መግለጫ “መንግስት በሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም፣ የሙስሊሞች ጠቅላይ ጉባኤ ወይም መጅሊሱ የአህባሾች መሰባሰቢያ እንጅ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ እምነት ብሶትና ፍላጎት አንጸባራቂ ባለመሆኑ መሪዎቹ ተሽረው ህዝብ በነጻ ምርጫ በመረጣቸው መሪዎች እንዲተኩ፣ መንግስት ችግር ፈጣሪ የሙስሊም ሀይሎች አሉ በሚልባቸው አካባቢዎች ከሀይማኖቱ ምሁራን፣ ከሙስሊሙ ሙያተኞች፣ እንዲሁም ከተለያዩ አገር ውስጥና ውጭ ካሉ የሙስሊም ድርጅቶችና የሙስሊም ማህበራት መሪዎች የተውጣጣ ስብሰባ እንዲጠራ” ጠይቀዋል።

መንግስት ” በሀይማኖቶች አለመቻቻል በአለም ታዋቂ ከሆነችው ሊባኖን አገር ሊቆች አመጣሁላችሁ ማለቱ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ብቻ ሳይሆን ለአገራችን ልእልና ደፋሪ ተግባር መሆኑ ታውቆ እንዲታረም እንጠይቃለን “፣ የሚሉት ሙስሊሞች፣ በአጠቃላይ የመንግስት እንቅስቃሴ የዜግነትን መብት የሚገፍ በመሆኑ አጥብቀው እንደሚቃወሙት ባወጡት መግለጫ ላይ ጠቅሰዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሰካም።

ፍትህና ዲሞክራሲ በሌለበት አገር አልኖርም በሚል ምክንያት አንድ መምህር ራሱን በእሳት አጋዬ

ኢሳት ዜና:- በዋካ ከተማ ነዋሪ የሆነው መምህር የኔሰው ገብሬ   የስድስት ወረዳዎች ባለስልጣናት በአንድነት ተሰባስበው በቅርቡ በዋካ የተፈጠረውን ችግር በሚወያዩበት ወቅት፣  በራሱ ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ እየተቃጠለ ወደ ስብሰባ አዳራሹ ገብቷል።

መምህሩ ራሱን እያነደደ ወደ ውስጥ ሲገባ የተመለከቱት የወረዳ ባለስልጣናት በመደናገጣቸው ከመምህሩ ለመራቅ ጥረት ያደርጉ ነበር ተብሎአል።

ምሁሩ በከተማው ውስጥ ከሚታወቁት በሳል ምሁራን መካከል አንዱ ነው የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎቹ፣  “ፍትህ እና ዲሞክራሲ በሌለበት አገር መኖር ሰልችቶኛል፣ በዚህ ሁኔታ በህይወት መቀጠል አዳጋች ነው” በማለት ይናገር እንደነበር ገልጠዋል።

መምህሩ በፖለቲካ አቋሙ ምክንያት ከስራ ተባሮ እንደነበር፣ በሁዋላም ወደ ስራ ለመመለስ ተደጋጋሚ ሙከራ አድርጎ እንዳልተሳካለት ታውቋል። በዋካ ከተማ ያለው ውጥረት አሁንም እንዳለ ሲሆን፣ በቅርቡ ለኢሳት መረጃ ሰጥተዋል ተብለው በጥርጣሬ የተያዙት ሰዎች አንዳንዶቹ በዋስ መለቃቀቸውም ታውቋል።

በአካባቢው የተሰማራው ልዩ ሀይል ግን አሁንም ከስፍራው አለመልቀቁን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በዋካ ከተማ ከወረዳና መብት ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ “የህዝቡ ጥያቄ ፍትሐዊ ቢሆንም፣ መንግስት ግን አስፈላጊውን መልስ ሊሰጥ አልቻለም” በሚል ምክንያት፣ የቶጫ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ፈቃዱ ወልደሩፋኤልና  ፣ የዞኑ አቃቢ ህግ የሆኑት አቶ ከበደ ካሳ በራሳቸው ፈቃድ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Ethiopians: November is to remember!

Prof. George Ayittey on ESAt and Addis Dimts Radio host Abebe Belew says supporting ESAT is key for change
Watch videos
Tamagne B. and Birtukan M.
( Watch videos)
Flag on Badme
Who killed Hayelom? (Last part) (Updated)

Commentary
By Alemayehu G Mariam; Nov 14, 2011

Nov 14, 2011

ጋዜጠኞች በ3 ተከፍለው ክትትል ይደረግባቸዋል

 

by Admin | 1:40 am | Leave a comment

በኤሊያስ ክፍሌ ፋይል የኢሳት ኢንትርቪው በአቃቤ ሕግ ማስረጃነት ቀረበ

(ሙሉ ገ. እና ኤፍሬም ካሳ)
በአቶ በረከት ስምዖን የሚመራው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ውስጥ በህትመት ሚዲያ ዘርፍ ፍቃድ አውጥተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ የብዙኀን መገናኛ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞችን በሦስት ከፍሎ እንደሚከታተላቸው ታወቀ። ጋዜጠኞቹና ገዘባዎቻቸው “አዎንታዊ/ገንቢ”፣ “አሉታዊ/አፍራሽ” እና “አማካይ” በሚል መመደባቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡ በዚህ የአቶ በረከት መደብ ውስጥ በዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ኢትዮጵያዊያንና በኢትዮጵያ የተመደቡ የሌሎች አገራት ጋዜጠኞችም ተካተዋል ብለዋል፡፡

Read more

Thanks for the honor Prime Minister

Sunday, November 13, 2011 @ 07:11 AM ed

By Abebe Gellaw

Dear Prime Minister Ashebir Zenawi,

First of all, I would like to thank you profusely for including me in the latest roll call of patriots and freedom fighters. I am extremely humbled for the honor. Though I have not done enough to deserve one of your highest medals of good citizenship and patriotism, I assure you that the honor will inspire me to do even more to accomplish what is expected of me more effectively and efficiently.

I must also thank you for the free global promotion you have given me and others. I am pleased to report back to you that I have received not condolences, but numerous congratulatory messages from across the world.

Prime Minister Ashebir, I should, however, suggest that the list of honorees be expanded to include more deserving patriots and the criteria be more logical. People like me have not done enough to be in this prestigious roll call of freedom fighters.

I am not complaining Prime Minister, but I would like to point out that the coveted list should not be compiled by corrupt thugs, drug addicts, drunkards and sycophants like Shimelis Kemal, Bereket Simon, Getachew Assefa, Genenew Assefa, Birhan Hailu, Tewodros Beharu and Million Assefa…, people who are held in great contempt as they have sold out their souls and conscience for a few dinars. In spite of the fact that these low-life thugs will do whatever you tell them to do, I believe that for the sake of the integrity of the honor list, these people should not be allowed to arbitrarily pick unrelated honorees while they are high on drugs, khat and alcohol. These vultures of yours have been undermining your wisdom and credibility by advising you to correct your mistakes with screaming blunders.

I am not complaining Prime Minister Ashebir because I still feel greatly privileged to be on your list of honorees. But I need to tell you that the latest list includes people who have already received the highest honor your government, i.e. TPLF, confers on any patriot. We were already told, via your Kangaroo court, that Dr. Birhanu Nega, Andargachew Tsigie and Mesfin Aman had already received martyrdom status. They were supposed to have been sent to report back to Almighty Creator. Why was it necessary to bring them back to life to award them another honor? How many times can they face your respected Kangaroo Court? It is neither fair nor logical. There are also those who were given lifetime fellowship like Fasil Yenealem, Ephrem Madebo and Andualem Andargie. I think fresh undergraduate honorees like me should not have been placed in a class of highly experienced senior honorees without being given an orientation.

Another thing that I need to point out is that the list of deeds appeared to be copied from the previous honor sheets. Terrorism, espionage, treason, conspiracy and the other deeds listed publicly appeared to be on one menu directly copied from another one. How could your fertile imagination fail you and recycle the same thing again and again? I am not complaining but you guys appear to be suffering from brain freeze.

I have to be honest with you Prime Minister Ashebir that of all the things you listed down in the file, I am not amused with your effort to link me and other Ethiopians with Shabia, your former mentor. How can you be so ungrateful to the people that trained and armed you to fight against Ethiopia and its people? By the way, you are more related to Eritrea than anyone of the people you put in the honor list. Isn’t Eritrea the land you claim to have freed from Ethiopian colonialism and made it a land of abundant liberty and freedom? Isn’t it your mother’s country? It is absurd to relate anyone in the streets to your motherland that you should keep to yourself. I, for one, seek neither assistance nor citizenship from your Eritrean cousins.

Let me also tell you that I am not a member of any political parties. If I decide to join a political group, rest assured that I will apply to become a member of the Tigray People’s Liberation Front because unlike the puppets it is the only organized political group in Ethiopia that has real power, fortune and leverage. But as you know, I don’t qualify to be a member of the TPLF because I do not pass the genetic test. That means I will never be a member of any political group until the ethnic apartheid you have been building is dismantled for good.

I am not complaining, but during the 2005 election turmoil, your roll call of honorees was ridiculed globally. You might have forgotten but those, who were in the honor list for “treason” and “genocide”, were five VOA broadcasters, aged university professors including Prof. Getachew Haile, journalists, activists and lawyers. Many of them are still in exile but whatever they say and write seems to haunt you and give you constant nightmares. We must feel sorry for you because your paranoia has reached an unprecedented level.

Prime Minister Ashebir Zenawi! William Gaddis once said: “Stupidity is the deliberate cultivation of ignorance.” I do not understand how a man of your caliber is so predictable all the time that you repeat the same mistake time and again. You have been toiling hard to make yourself an object of ridicule. You may remember that famous character called Mamo Kilo.

Because of his unforgettable acts, there is no character as enduring as Mamo Kilo, a dim-witted country boy. His endless creativity, quick thinking and most of all absurdities, have made him widely popular. Mamo Kilo gets everything wrong and never learns from his mistakes. In fact, his way of correcting mistakes is making more absurd blunders that make him a laughingstock.

By all account, there is only one man that has been overtaking Mamo Kilo’s place as a master of absurdities. Despite your best efforts to appear smart, erudite and serious, not to mention mingling with famous leaders, your ridiculous actions have made you the uncontested king of absurdity in Ethiopia. Your place is history is not just for being an evil dictator, From your courts to parliament, from your cabinet to electoral board, your endless absurdities have ensured your infamy not only locally but across the globe.

Mr. Prime Minister, as you have honored so many patriots, Ethiopians will permanently honor you in their history as a terrible dictator in par with Mussolini and the adult version of Mamo Kilo.

Mr. Prime Misery, you are a shame to humanity, a shame to Ethiopia and more specifically to the people of Tigray. Your fictitious charge sheets don’t scare anyone except having the usual effect of degrading yourself, your “parliament”, kangaroo courts and the very concept of law and order…. Your moronic injustice and outrageous lies will only bring your downfall ever closer… Your downfall will inevitably be as resounding as Gaddafi’s. This must be terrorizing and terrifying to you and Azeb.

Shame on you Mr.Prime Terrorist Ashebir Zenawi! Please don’t forget to add my words to the charge sheet because I am telling the truth, the whole truth, nothing but the truth…. Keep on lying in the name of justice. Your fate is quite predictable.

Free all the innocent men and women you have taken hostage.

Victory to Ethiopia!

Thanks for the honor Prime Minister

 

Dear Prime Minister Ashebir Zenawi–First of all, I would like to thank you profusely for including me in the latest roll call of patriots and freedom fighters. I am extremely humbled for the honor. Though I have not done enough to deserve one of your highest medals of good citizenship and patriotism, I assure you that the honor will inspire me to do even more to accomplish what is expected of me more effectively and efficiently.

Hope for East Africa. Fundraising Dinner for the Famine

Created on Tuesday, 27 September 2011 23:53 By Amane Wako Oromia Youth Association Presents ( HAWII) . 3On October 8th, 2011, Oromia Youth Association is holding its annual fundraising dinner in order to bring aid to the humanitarian crisis unfolding in East Africa. Many people throughout the world know of the tremendous starvation that is killing millions, specifically in Ethiopia and Somalia.We as the youth have a responsibility to do whatever we can to aid people in desperate need of assistance Read the rest of this entry

%d bloggers like this: