Monthly Archives: December 2011
በግለሰቦች መብት የዓለም የመጨረሻዋ አገር፣ ኢትዮጵያ
On Friday, December 30, 2011 10:02 PM.
ባለፈው ጊዜ ሌጋተም የተባለው ድርጅት የ 110 አገሮችን የብልጽግና ደረጃ ሲያጠና ሰንብቶ ባወጣው ሪፖርት ላይ በ አጠቃላይ ውጤት ኢትዮጵያ እንደተለመደው ወደ መጨረሻው ሆና 108 ኛ ወጥታለች:: እንዲህ አይነቱ የመጨረሻ አካባቢ ውጤት የተለመደ በመሆኑ እምብዛም አልተገረምን:: Read the rest of this entry
የበረከት መጽሐፍ
On Friday, December 30, 2011 10:02 PM.
ተስፋዬ ገብረአብ This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it
የበረከትን መጽሐፍ አነበብኩት …
በእውነቱ ህትመቱ ቆንጆ ነበር። ሽፋኑ እንደ ሃብታም ጉንጭ ይለሰልሳል። ከቻርልስ ዲክንስ ታዋቂ መጽሐፍ የተኮረጀ ቢሆንም ርእሱም ቢሆን አሪፍ ነው – የሁለት ምርጫዎች ወግ። የበረከትን መጽሐፍ ያሳተመው መሐመድ አሊ አልአሙዲ የተባለው ነጋዴ መሆኑን ፍትህ ጋዜጣ ላይ አንብቤ ነበር። መጽሐፉ 314 ገፆች እና 10 ምዕራፎች ይዞአል። ዋጋው 90 ብር ነው። Read the rest of this entry
Ethiopia: የኦነግ ስብሰባ በሚኒሶታ(ለመጀምሪያ ጊዜ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተጋበዘ)
On Friday, December 30, 2011 03:30 AM.
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እሁድ ጃንዋሪ አንድ በሚኒሶታ ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዲገኝ ጥሪ አቀረበ:: እሁድ ጃንዋሪ አንድ በኪሊ ኢን ሆቴል ሴንት ፖል በሚደረገው በዚሁ ስብሰባ ላይ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድምቹ ጋር በጽናትና በአንድነት የሚታገልበትን ሁኔታ ያበስራል ተብሎ ይጠበቃል:: ሚኒሶታ በሰሜን አሜሪካ ካሉ ስቴቶች የኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ተወላጆች ቁጥር በአንደኝነት የምትቀመጥ ሲሆን በዚህ ስብሰባ ላይ ለመታደም ከሌሎች ታላላቅ ስቴቶች ሁሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን እንደሚመጡ ይጠበቃል:: ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የመጡ የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ምንጮች እንደሚናገሩት ከሆነ እሁድ ጃንዋሪ አንድ በአዲሱ ዓመት ኦነግ አዲስ ብስራት ለኢትዮጵያውያን አለው:: Continue reading →
አቡጊዳ – የአቃቤ ሕግ መረጃ እነእስክንድር ሰላማዊ እንጂ ሽብርተኞች እንዳልሆኑ በገሃድ አረጋገጠ !
On Friday, December 30, 2011 03:37 PM.
በአዲስ አበባ የጉርሻ ምግብ መሸጫ ቤቶች እየተስፋፉ ነው ተባለ
dec 30/12/2011

ኢሳት ዜና:-ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው በአዲስ አበባ ከተማ አንድ እና ሁለት የነበሩት የጉርሻ ምግብ መሸጫ ቦታዎች በተለያዩ ክፍለ ከተሞችም እየተስፋፉ ነው።
በመርካቶ ብቻ ሶስት የጉርሻ ምግብ መሸጫ ቦታዎች መኖራቸውን የዘገበው ፎርቹን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በፒያሳ፣ ስድስት ኪሎና ሌሎች ቦታዎችም የጉርጫ ምግብ መሸጫ ቦታዎች መቋቋማቸውን ዘግቧል። Read the rest of this entry
አቡጊዳ – ከሳሞራ የኑስ ጋር የማይስማሙ ጄነራሎች ተባረሩ !


አቡጊዳ – ከሳሞራ የኑስ ጋር የማይስማሙ ጄነራሎች ተባረሩ !
On Thursday, December 29, 2011 02:23 AM.
አገር ዉስጥ የሚታተመዉን ካፒታል ኢትዮጵያ የተሰኘዉን የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ጠቅሰን፣ ወደ ሶስት መቶ የሚሆኑ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መኮንኖች ስራቸዉን እንዲለቁ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል። ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ እንደሚጠቁመዉ ከስራ እንዲሰናበቱ ከተደረጉት መኮንኖች መካከል ጄነራል ሳሞራ የኑስ እና ከርሳቸው ጋር ቅርበት ያላቸዉ ሞኮንኖች እንዳልተነኩ ለማወቅ ችለናል። Read the rest of this entry
christmas attacks in Nigeria
on.dec28/12/12
LAGOS, Nigeria—Attacks across Nigeria by a radical Muslim sect killed at least 39 people Sunday, with the majority dying on the steps of a Catholic church in a massive explosion after Christmas Mass.
Elsewhere, a bomb exploded amid gunfire in the central Nigeria city of Jos and a suicide car bomber attacked the military in the nation’s northeast as part of an apparently coordinated assault by the sect known as Boko Haram. Read the rest of this entry
ትግል በአስመራ በኩል፣ ክፍል ሁለት ምላሽ ለዶ/ር ብርሃኑ
On Wednesday, December 28, 2011 01:59 AM.
ግርማ ካሣ This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it
መግቢያ
ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ከግንቦት ሰባቱ መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ባደረገው ቃለ-ምልልስ ካነሳቸው ነጥቦች መካከል የኤርትራ ጉዳይ ይገኝበታል። ኤርትራን በተመለከተ ዶ/ር ብርሃኑ ከተናገሩት የምጋራቸው በርካታ ነጥቦች አሉ። በተለይም የኤርትራ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ትልቅና ስር የሰደደ ታሪካዊ ትስስር እንዳለው፣ በርግጥ በኢትዮጵያ ሕዝብ የተመረጠ ለሕዝብ ፈቃድ ተገዢ የሆነ መንግስት ቢኖር፣ ከኤርትራ ጋር ያለውንም ሆነ ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት በጣም እንደሚቀል በመግልጽ የሰጡትን አስተያየት፣ ምናልባት ከአምባገነኖቹ በስተቀር የማይጋራው ሰው አለ ብዬ አላስብም። Read the rest of this entry