ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በ88 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

 

በከፍተኛ የስኳር እና የልብ በሽታ ሲሰቃዩ የቆዩት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በ 88 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው እየተዘገበ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ዜናውን ይፋ እንዳላደረገው ታውቆአል:: በኢሃዴግ መንግስት ዘመን ለረጂም የስልጣን ሂደት ካከናወኑት መካከል አንዱ ሲሆኑ እስከዛሬ ለነበራቸው የስራ አገልግሎት ዘመን በኢሃዴግ ተመስጋኝነትን አትርፎላቸዋል በተለይም የኢሃዴግ አስተዳደር የሚፈልገው የሚቃወመውን ሳይሆን ቁጭ ብሎ የሚደግፈውን አካል ስለሆነ ይህንን ደገሞ እርሳቸው በከፍተኛ ደረጃ የተካኑ መሆናቸው ግልጽ ነበር ። ለፕሬዚዳንትነት በተመረጡ በነጋታው ³መቶ አለቃ አትበሉኝ´ በማለት በውትድርና ያገኙትን ማ ዕረግ ከራሳቸው ላይ የገፈፉት ግርማ ላለፉት 11 ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት መምራታቸውና የሥራ ጊዜያቸውን አጠናቀው ከሥልጣን ለመውረድ የስድስት ወራት ዕድሜ የቀራቸው መሆኑ ይታወቃል: ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በጠና ታመው ኮሪያ ሆስፒታል መግባታቸውን  ባለፈው ሳምንት መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን; ኮሪያ ሆስፒታል .

 

ያስገባቸው ሕመም ጉንፋን ቢጤ ነውና ለክፉ አያጋልጣቸውም እየተባለ በመንግስት ሰዎች ሲነገር ቆይቷል:: በአሁን ሰአት የፕረዚዳንት ግርማ ሞት የወያኔን ባለስልጣናት እንዳሰደነገጣቸው ተገልጦአል። ከቀዳዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመን ጀመሮ ለስልጣን ሩጫ ሲዋትቱ የነብሩት ፕረዚዳንት ወልደ ጊዮርጊስ በውትድርና አገልግሎት ረዘም ላለጊዜ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በደርግ መንግስትም ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው ሰው ነበሩ። ከ11 ዓመት በፊት በፕሬዚዳንትነት ስልጣን  እንደተመረጡ; በከፋ ሕመም ተጋልጠው ወደ ሳኡዲ ለህክምና ሄደው የነበሩት ፕሬዚዳንት ግርማ በተደጋጋሚ ላለፉት 11 ዓመታት ለበርካታ ጊዜያት የሆስፒታል ኢመርጀንሲ ክፍሎችን ጎብኝተዋል ባሳለፍነው ሳምንትም በነበሩበት ሆስፒታል በከፍተኛ የጥበቃ ሃይሎች እየታገዙ የህክምና አገልግሎት በመከታተል ቢያሳልፉም እርሳቸው ግን ከመሞት ወደሗላ ሊሉ አልቻሉም ። ፕረዚዳንት ግርማ በአስራአንድ አመታት ውስጥ በሃገሪቱ የሚላኩትን ልኡካን በማስተናገድ ስራ ተጠምደው  እና የጋርዮሽ ስራ ፊርማዎችን ሲያጸድቁ፣ ሲፈርሙ፣ እንዲሁም ተፈርመው የተላኩትን ብቻ ሲቀበሉ የነበሩ የገዢውን ፓርቲ አገልጋይ እንደነበሩ ይታወሳል።

ዝርዝር ዘገባ ይዘን እንቀርባለን

Posted on March 13, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. 1 Comment.

  1. በጣም ነው ያዘንኩት ………….
    ጌታ ነፍሳቸውን በ ገነት እንዲያኖራቸው ጸሎቴ ነው

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: