Monthly Archives: April 2012

ሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣ ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል

april 30-2004
በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣ ሁለት የውጭ ሀገር ተወላጆች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል ሲል ኢሳት ዘገበ።
የገዳሙ አባቶች ለሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እስከ 200 ኪሎሜትር ርቀት የሚገኙ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ አካባቢው መትመማቸውን ተከትሎ ሁለት የውጭ ሀገር ተወላጆች መሞታቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ “ ከህዝብ ጋር አንጣላም” በማለት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል። የሟቾቹ እና አካባቢውን ለቀው የወጡት ምእርባዊያን ይሁኑ የቻይና ዜጎች አልታወቀም። Read the rest of this entry

ዛሬም እየተገደልን ነው… ሲደብር! (አቤ ቶኪቻው)

april 30-2004

ሰሞኑን ከተሰሙ አስደንጋጭ ዜናዎች ውስጥ የሚከተለው ይገኛል…

“በዛሬዉ እለት በአርሲ አሳሳ ከተማ የጁምአ ሰላት ከተሰገደ በኋላ ሼህ ሱዑድ በአንድ መስጂድ ዳዕዎ አድርገዉ ሲወጡ በፓሊስ በመያዛቸዉ፤ የአካባቢዉ ሙስሊም ህብረተሰብ “ሼሁ ለምን ይታሰራሉ ምንም ጥፋት አልፈፀሙም” በሚል ለማስለቀቅ ሲሞክሩ ከፓሊሶች ጋር በተፈጠረዉ አለመግባባት ፓሊስ በከፈተዉ ተኩስ እስካሁን ባለዉ መረጃ መሠረት አምስት(5) ሰዎች መገደላቸዉና ብዙ ሰዎች መቁሰላቸዉን የአካባቢዉ ምንጮች ገለፁ:: ከተገደሉት ሰዎች መካከል ሼህ ኸድር የሚባሉ ታላቅ አሊም እንደሚገኙበትም ምንጮች ጨምረዉ ገልፀዎል:: እንደሚታወሰዉ ሼህ ሱዑድ ሻሸመኔ በተካሄደዉ ስብሰባ ላይ “ኢህአዴግን ለሀያ አመታት ስንደግፈዉ ኖረን አሁን እንዴት አሸባሪ አክራሪ ብሎ ይወነጅለናል” በማለት የተሰማቸዉን ቅሬታ በስብሰባዉ ላይ ገልፀዉ እንደነበር የሚታወስ ነዉ:: Read the rest of this entry

በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣ ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል

Monday, April 30, 2012
ኢሳት ዜና:-

በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣  ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል የገዳሙ አባቶች ለሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እስከ 200 ኪሎሜትር ርቀት የሚገኙ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ አካባቢው መትመማቸውን ተከትሎ ሁለት ነጮች መሞታቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ እኛ ከህዝብ ጋር አንጣላም በማለት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል።
የሟቾቹ እና አካባቢውን ለቀው የወጡት ነጮች ምእርባዊያን ይሁኑ የቻይና ዜጎች አልታወቀም። ከ5ሺ ያላነሱ የአካባቢው ነዋሪዎች በዋልድባ ተገኝተው ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን፣ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላትም እርምጃ ለመውሰድ ፈርተዋል። ሁኔታው እጅግ አስፈሪ ነው፣ መንግስትና ህዝቡ ተፋጠዋል፣ የአካባቢው ወጣቶችም ወደ አካባቢው ለመጓዝ እየተመካከሩ ነው ሲል አንድ ጉዳዩን በቅርብ ሆኖ የሚከታተል ሰው ለኢሳት ገልጧል። Read the rest of this entry

የኢትዮጵያ ብሎጎች ምን ጻፉ?

Posted on April 29, 2012

የአሁኑን ሳምንት የኢትዮጵያ ብሎጎች ክለሳ ስሰራ ትልቁ ተግዳሮቴ የነበረው አብዛኞቹ ካሁን በፊት በዘዴ ወኪል ሰርቨርን በመጠቀም የማነባቸው  ብሎጎች አብዛኞቹ  ወኪል ሰርቨሮችም ጭምር ስለታገዱ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ድረስ ማንበብ አልቻልኩም ነበር:: ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ በወኪል ሰርቨሮች በኩል ማንበብ ያቃተኝን ጽሁፍ ከሀገር ውጪ ያሉ ወዳጆቼ  እንዳለ ገልብጠው በውስጥ የኢሜል አድራሻዬ  በኩል እንደ ቅጥያ ዶክመንት  ልከውልኝ ማንበብ ችያለሁ::  ሌሎች ያልታገዱ  አዳዲስ  ወኪል ሰርቨሮችንም እንድሞክራቸው ልከውልኝ መጠቀም ችያለሁ:: ስላጋጠመኝ ችግር  እና የሳምንቱ አብይ ጉዳይ ሆኖ የብዙ ብሎግ ጻሀፊያንን ትኩረት ስቦ ስለነበረው የብሎጎች እገዳ ይህችን ታህል  ካልኩ ሌሎች ምን እንዳሉ እስቲ ላቃምሳችሁ::  በፍቄን ላስቀድም በፌስቡክ ግድግዳው ላይ አጭር  ጽሁፍ አስነብቦ በብሎጉ ላይ ኢትዮጵያ መንግስት መጠላቱን የሚያሳብቁ ምልክቶች በሚል ርእስ የጻፈውን ጽሁፍ ትይይዝ አስቀምጧል:: ሙሉውን ጽሁፍ ትይይዙን ጠቅ በማድረግ ይከፈቱት አልከፍት ካሎት በፍቄ  በፌስቡክ ግድግዳው ላይ ያሰቀመጠውን ጽሁፍ በማንበብ ይሞክሩት: Read the rest of this entry

የመንግሥት ሌቦች አደራ-ቢስነትና ሕዝብ ኃላፊነት

Sun, 04/29/2012

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ስለመንግሥት ሌቦች እየተናገረ ነው፤ ሌቦቹን ግን እሱም አያውቃቸው፤ እነሱም እየሰሙት አይደለም፤ የመንግስት ሌቦች የተባሉት የሚግጡባቸው ዋናዎቹ መስኮች ታክስ፣ መሬትና የንግድ ውድድር መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጾአል፤ ከዚህም በላይ የተባሉትን የሌብነት መስኮች ከለምነት ወደበረሃነት ለመለወጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ኃላፊነት አለበት ያለ መሰለኝ፤ ሥልጣን ሳይኖር ኃላፊነት ከየት ይመጣል? እንግዲህ የፌዴራል ፖሊሱንና ሌላውን አልፎ፣ የደኅንነቱን ሰራዊት አልፎ፣ የጸረ-ሙስና ኮሚሽንን አልፎ፣ ዓቃቤ ሕግን አልፎ ሕዝብ እነዚያን ለምለም መስኮች ማድረቅ እንዴት ይችላል? Read the rest of this entry

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል በሚል የወጣውን መረጃ ተከትሎ ኤርትራ ውጥረት ውስጥ ገብታለች

Sunday, April 29, 2012

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል በሚል የወጣውን መረጃ ተከትሎ ኤርትራ ውጥረት ውስጥ ገብታለች፡፡ አስመራን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ከፍተኛ የሚሊተሪ እንቅስቃሴ መኖሩን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ላለፈው አንድ ወር ያህል ከሚዲያ የራቁት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከዚህ ዓለም በሞት ስለመለየታቸው በእርግጠኝነት የሚናገሩ የመኖራቸውን ያህል፣ አልሞቱም ግን ኮማ ውስጥ ገብተዋል የሚሉ ወገኖችም አልጠፉም፡፡
የኤርትራ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በበኩሉ አቶ ኢሳያስ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ‹‹ፕሬዚዳንቱ ሞተዋል›› የሚለውን የተሳሳተ መረጃ የሚያናፍሱትም ሲአይኤና ኢትዮጵያ መሆናቸውን እየገለጸ ይገኛል፡፡ በቴሌቪዥን የሚታየው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ምስል ግን ከወራት በፊት የተቀረጸ መሆኑን ታዛቢዎች ይገልጻሉ፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ መሞታቸው በሚነገርበት በአሁኑ ጊዜ አስመራ ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚታይ ሲሆን፣ አገሪቱን ማን ነው እየመራት ያለው የሚለው ጉዳይ ግን በግልጽ ሊታወቅ አልቻለም፡፡ Read the rest of this entry

በአፋር አንድ ወጣት ተገደለ ሶስት ቆሰሉ

Saturday, April 28, 2012    ኢሳት ዜና:-
በአፋር ክልል በዱብቲ ከተማ በህዝቡ እና በመንግስት ማካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ደም መፋሰስ እያመራ መሆኑን በተደጋጋሚ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ በዛሬው እለት የፌደራል ፖሊስ አባላት የ17 አመቱን የ7ኛ ክፍል ተማሪ የሆነውን አሊ ኡመር ሙሀመድን በሶስት ጥይት ገድለው በጓደኞቹ ላይ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ድ ብደባ ፈጽመዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች እና የቀበሌ አመራሮች ሳይቀሩ የልዩ ሀይል የፌደራል ፖሊስ አባላትን ልትጨርሱን ነው ወደ ዚህ የመጣችሁት በማለት ሲቃወሙዋቸው ነበር። ሟቹን ለመቅበር በጸሎት ላይ የነበሩ ሰዎችን የኢሳት ዘጋቢ ባነጋገረበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ ቁጣ እና ብስጭት በህዝቡ ዘንድ ይሰማ ነበር። Read the rest of this entry

በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ

Friday, April 27, 2012
ኢሳት ዜና:- 

በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ  22 ሰዎች መሞታቸውና በርካቶች መቁሰላቸው ተዘገበ።  እንደ ፍኖተ-ነጻነት ዘገባ በሁለቱ ክልሎች የድንበር ነዋሪዎች መካከል ለተፈጠረው ግጭት ምክንያቱ የቦታ ይገባኛል :
የአካባቢው ነዋሪዎች  እንደገለጹት ከሆነ “በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ልዩ ሥፍራው “ጊዳ ኪራሞ” እና “ጊዳ አያና” በተባሉ ወረዳዎች ለተነሳው ግጭት መንስዔው፤ አቤንቱ፣ ቄሎ እና ዋስኪ በተባሉ አካባቢዎች የተፈጠረ የይገባኛል ጥያቄ ነው፡፡ Read the rest of this entry

Salini spells out Impregilo merger plan

April 27, 2012
By Danilo Masoni

MILAN | Mon Apr 23, 2012 2:01pm EDT

MILAN (Reuters) – Italian builder Salini expects a possible merger with listed rival Impregilo (IPGI.MI) to create a national champion with sales of around $9.2 billion in 2015, its chief executive said on Monday, pointing to a special dividend if the plan succeeds.

Family-owned Salini, which posted 2011 revenue of 1.4 billion euros ($1.8 billion), has grown in recent years via acquisitions and expansion in markets such as Ethiopia, Kazakhstan, Nigeria and, recently, Denmark. Read the rest of this entry

International Press Institute World Press Freedom Heroes Condemn Imprisonment …

April 27, 2012
International Press Institute World Press Freedom Heroes Condemn Imprisonment of Journalist

Press Release

Vienna — Twenty general reporters who have been recognized as World Press Freedom Heroes by a Vienna-based International Press Institute (IPI) have cursed a Ethiopian government’s preference to jail Eskinder Nega and other reporters on terrorism charges, and called for their evident release. Read the rest of this entry

%d bloggers like this: