Monthly Archives: May 2012

ሁሴን! የተረሳ እስረኛ! (ከተስፋዬ ገ/አብ)

may 30.2012

ለመሆኑ ሁሴን ማነው? ስለ ሁሴን ታሪክ ያወቅሁት፣ “የቃሊቲ ምስጢሮች” በሚል ርእስ ወሰንሰገድ ገብረኪዳን በቅርቡ ያሳተመውን መፅሃፍ ሳነብ ነው። ወሰንሰገድ ዝዋይ እስር ቤት እንደገባ ነበር ከሁሴን ጋር የተዋወቁት። እንዲህ አወጉ፣ Read the rest of this entry

ጋዜጠኛ አበበ ገላው፣ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ተባብረው አገራቸውን ነጻ እንዲያወጡ ጥሪ አቀረበ

may 31,2012
አውራምባ ታይምስ (ዋሺንግተን ዲ.ሲ) – እኤአ ሜይ 18/2012 እዚሁ በዋሺንግተን ዲሲ በተዘጋጀው የምግብ ዋስትና ሲምፖዚየም ላይ በጠ/ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ላይ ግልጽ ተቃውሞ በመሰንዘር በመላው አለም በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተው ጋዜጠኛ አበበ ገላው፣ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ልዩነታቸውን ወደጎን አድርገው የአቶ መለስ ዜናዊን ስርዓት እንዲታገሉ ጥሪ አቀረበ ::
፡፡
‹ለ21 ዓመት ያህል የተሰቃየን ሰዎች አቶ መለስን ለጥቂት ደቂቃዎች እንዲደናገጡ በማድረግ ብቻ መቆም የለብንም›› የሚለው ጋዜጠኛ አበበ፤ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝባዊ አመጽ እንዲነሳ ሁሉም በጋራ መነሳት አለበት ሲል ለአውራምባ ታይምስ ገልጾአል፡፡ Read the rest of this entry

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከሦስት ዓመታት በኋላ ጡረታ እንደሚወጡ በድጋሚ አረጋገጡ

May 31, 2012

– የተዋጣለት ዴሞክራሲ አልገነባንም
– በሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊት የብሔር ተዋፅኦ ቢሻሻልም አመራሩ ግን ቀድሞ ከሕወሓት ታጋዮች አልተላቀቀም
– እየተገነቡ ባሉ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድቦች ላይ የምዕራብ አካባቢ ተቆርቋሪዎችን ተፅዕኖ ፈርተውታል

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከእንግሊዛዊው ጋዜጠኛ ሪቻርድ ዳውደን ጋር ከሰሞኑ ቃለ-ምልልስ አድርገው ነበር። ሪቻርድ ዳውደን የሮያል አፍሪካ ሶሳይቲ ዳይሬክተር ሲሆን፤ በጋዜጠኝነት በታላላቅ የእንግሊዝ ጋዜጦችና በዘኢኮኖሚስት መፅሔት የአፍሪካ ኤዲተር ሆኖ ሰርቷል። በአፍሪካ ዙሪያ መፅሐፍቶች ፅፏል። Read the rest of this entry

የብዙሃኑ ፍላጐት-የጥቂቶቹ መብት! (ሰሎሞን ተሰማ ጂ) (ከአ/አ)

Published On: Thu, May 31st, 2012

 የሀገራችንና የህዝቧ እጣ-ፈንታ አስደማሚና አሳዛኝ ቀልዶችን በተጫነ የጊዜ በቅሎ፣ ፈረስ፣ ግመል፣ አይሱዙና ካሚዮን ታጭቆ ወደ ግንቦት ሲገሰግስ አይታያችሁም? “አስደማሚና አሳዛኝ ቀልዶች” ሁሉ አስቂኝ አለመሆናቸውንስ ልብ አላችሁ? “እንከን የለሽ!” ተብሎ ከነበረው የ1997 ምርጫ በኋላ፣ “ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዉና ተዓማኒነት!” ያለው ምርጫ-በምድር ኢትዮጵያ ይደረጋል የሚለውን ልፈፋ የሰማችሁ ጊዜ ምን ተሰምቷችሁ ነበር? ዛሬስ፣ ስለምርጫው ምን ዓይነት ግንዛቤ ጨበጣችሁ? አንባቢያንን፣ በጊዜ የጋማ ከብቶች ጀርባ፣ በአይሱዙና በካሚዮን መጫኛ ላይ አሳፍሬ ወደተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች እወስዳቸዋለሁ፡፡ ለምን ጥያቄዎችን እንዳዥጐደጐድኩባችሁም የኋላ-ኋላ ታጤኑታላችሁ፡፡ (በመጀመሪያ ግን አንድ ሁለት ቀልዶች እነሆ ልበላችሁ፡፡ ቀልዶቹን የነገረኝን የሀረሩን ቀልደኛ-ኢሳያስ “ታክሲን” አመስግኑልኝ”፡፡) Read the rest of this entry

ታሪክ ያላነበቡ ታሪክ ሰሪዎችና፣ ታሪክ ያላነበቡት ታሪክ ዘካሪዎች፣ ጉድ አፈሉብን! (ለፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በተለይ) (ሰሎሞን ተሰማ ጂ.) (ከአ.አ)

Published On: Thu, May 31st, 2012
0. መግቢያ

ፍሬድርክ ቼ በደስታና በፈንጠዝያ የምፎልሉትን እንሰሳት ተጠጋና ጠየቃቸው። “ለምንድነው እንደዚህ ደስተኛ ልትሆኑ የቻላችሁት?” የሚል ነበር ጥያቄው። እነሱም ባንድነት፣ ባንድ ቃል መለሱለት። ምንም ሳይወያዩ፣ ምንም ነገር ሳይፎካከሩ፣ መንፍሳቸውም ሳይቀናና፣ አንዱም ሌላውን ሳይተች፣ ደመ-ነሳቸው በሚነግራቸው መሰረት፣ “ምንም ታሪክ (memory of things) ስለሌለን ነዋ!” አሉት። ከአፍታ በሁዋላ “ምን አላችሁኝ? እስኪ ድገሙልኝ?” ሲል ጥያቄዎቹን አጅጎደጎደባቸው። እነሱ ግን የሰጡት መልስ አጭርና አስገራሚ ነበር። “ምኑን ነው የምንደግምልህ?” የሚልና ክው አድርጎ የሚያስቀር መልስ። ሁሌም የሚደንቀኝ አይነት፣ “ቅስም-ሰባሪ” መልስ ይሉዋችሁዋል እንዲህ ያለው ነው-እንጂ! ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?
****** Read the rest of this entry

I will retire in 2015 and probably teach at the leadership academy: Meles Zenawi

Posted by  on May 31, 2012

By Richard Dowden
 
RAS Director Richard Dowden interviewed Ethiopian Prime Minister Meles on May 12th 2012. What follows is a selection of quotes from the interview on subjects ranging from democracy to the demise of Muammar Gadaffi and ‘land grabbing.’ To read Richard’s full analysis of the current state of Meles’ Ethiopia click here.
MelesZenawi and Richard Dowden

 

 

On the suggestion that, as a ruler from a minority, he is rushing the development of Ethiopia as fast as possible into order to stay in power
We are making progress on the economic front though not necessarily according to the standard orthodox prescription, so people think there must be something wrong… Read the rest of this entry

ሳዑዲ ዓረቢያ ለመሄድ የጤና ምርመራ ያደረጉ ከ20 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ውጤታቸው ተቀባይነት አጣ

Published On: Wed, May 30th, 2012
 Share This

ሳዑዲ ዓረቢያ ለመሄድ የጤና ምርመራ ያደረጉ ከ20 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ውጤታቸው ተቀባይነት አጣ source reporter

ለምርመራው 11 ሚሊዮን ብር በላይ ከፍለዋል

በቤት ሠራተኝነት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ለመሄድ በነፍስ ወከፍ 550 ብር እየከፈሉ የጤና ምርመራ ያደረጉ ከ20 ሺሕበላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ ‹‹የመረመሯችሁ የጤና ተቋማት የላኩት የምርመራ ውጤት ተቀባይነት የሌለውናየታገዱ ናቸው›› በመባላቸው፣ ውጤታቸው ተቀባይነት ማጣቱንና በችግር ላይ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ Read the rest of this entry

በሚድሮክ ወርቅ እና በሻኪሶ ህዝብ መካከል ያለው አለመግባባት ድርጅቱን አደጋ ላጥ ጥሎታል ተባለ

Wednesday, May 30, 2012

ኢሳት ዜና:-

ንብረትነቱ የሼህ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲ የሆነውና በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር የሚገኘው ሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ በሻኪሶ አካባቢ ሕገወጥ ሠፈራ ይቁምልኝ ሲል ሲያካሂድ የነበረው ሙግት በፊዴራልና የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት በኩል ተገቢውን ትኩረት ባለማግኘቱ ቢዝነሱ ሥጋት ላይ መውደቁን ምንጮች ጠቆመዋል፡፡
 
ሚድሮክ ወርቅ በሻኪሶ ለገደንቢ አካባቢ ሰዎች ተደራጅተው አነስተኛ ከተማ በመመሥረት ግልጽ ዘረፋ እየፈጸሙብኝ ነው ሲል ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አቤቱታ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ኩባንያው እንደሚለው የተደራጁ ዘራፊዎች ሕጋዊ በሆነ ይዞታው ውስጥ በመግባት በቁፋሮ የወጡ ድንጋዮችን ወስደው በመከስከስ ወርቅ አምራች ነን የሚሉ ናቸው ብሏል፡፡ድርጊቱ በመስፋፋቱም አካባቢው በድንጋይ ክምር በመሞላቱ “ሮክ ሲቲ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።
 
የሼሁ ኩባንያ ድርጊቱን እንዲያሰቆሙለት በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታ አቅርቦ አጥጋቢ ምላሸ እንዳልተሰጠው በዚህም ምክንያት ቢዝነሱ ጭምር አደጋ ላይ መውደቁን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ኩባንያው በአካባቢው ያለውን የወርቅ ማእድን እየዘረፈ ፣ ነገር ግን ለሻኪሶ ህዝብ ምንም ያስገኘለት ጥቅም የለም በሚል ምክንያት ከሁለት አመት በፊት የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ዝርፊያው መባባሱ እየተነገረ ነው። Read the rest of this entry

Judges sentence Charles Taylor to 50 years for supporting Sierra Leone rebels in civil war

Published On: Wed, May 30th, 2012
 

By Associated Press, Updated: Wednesday, May 30, 6:46 AM Read the rest of this entry

በ35 ሺህ ብር ወጪ የተሰራው የመለስ ዜናዊ ግዙፍ ምስል ከአዋሬ አደባባይ ተሰረቀ

may 30,2012

በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ግዙፍ ምስል ባልታወቁ ሰዎች መሰረቁ ተገለፀ፡፡ በኢሳያስ ማስታወቂያ ታትሞ የተተከለው የአቶ መለስ ምስል “በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደደፈረ ጀግና” የሚል መፈክር የያዘ እንደነበር የድርጅቱ ባለንብረት አቶ ኢሳያስ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ተናግሯል፡፡
Read the rest of this entry

%d bloggers like this: