ሳዑዲ ዓረቢያ ለመሄድ የጤና ምርመራ ያደረጉ ከ20 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ውጤታቸው ተቀባይነት አጣ

Published On: Wed, May 30th, 2012
 Share This

ሳዑዲ ዓረቢያ ለመሄድ የጤና ምርመራ ያደረጉ ከ20 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ውጤታቸው ተቀባይነት አጣ source reporter

ለምርመራው 11 ሚሊዮን ብር በላይ ከፍለዋል

በቤት ሠራተኝነት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ለመሄድ በነፍስ ወከፍ 550 ብር እየከፈሉ የጤና ምርመራ ያደረጉ ከ20 ሺሕበላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ ‹‹የመረመሯችሁ የጤና ተቋማት የላኩት የምርመራ ውጤት ተቀባይነት የሌለውናየታገዱ ናቸው›› በመባላቸው፣ ውጤታቸው ተቀባይነት ማጣቱንና በችግር ላይ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያውያኑ ምርመራውን ካደረጉና ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ከከፈሉ በኋላ ውጤቱ ተቀባይነት እንደሌለውየገለጹላቸው ጽሕፈት ቤቱን ካዛንችስ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥርያ ቤት አካባቢ ያደረገው፣ ጋምካ(Gulf Countries Council Approval Medical Center Association) የተባለ በዓረብ ባህረ ሰላጤአገሮች የትብብር ምክር ቤት የተቋቋመ ተቋምና በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ ኤምባሲ መሆናቸውን ተመርማሪዎቹተናግረዋል፡፡

ያለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተሳትፎ ጋምካ የሚባለው ተቋም ሰባት የጤና ተቋማትን መርጦ ተጓዦቹ በተመረጡትየምርመራ ተቋማት ብቻ እንዲመረመሩ ይልካቸው እንደነበር ገልጸው፣ የምርመራ ውጤታቸውን ወደ ኤምባሲውሲወስዱ ‹‹የምቀበለው እኔ ከመረጥኩት የሕክምና ተቋም ብቻ የመጡትን ብቻ ነው›› በማለቱ በችግር ውስጥመሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ሌላው ጋምካ የተባለው ተቋም ስህተት ሠርቷል የሚሉት ተመርማሪዎቹ፣ ከኤምባሲው ጋር ሳይነጋገርና ሳያሳውቅ ዛክናሳይመን በተባሉ የሕክምና ተቋማት ምርመራ እንዲያደርጉ በማድረጉና ተጓዦቹ ምርመራ ጨርሰው ሰነዳቸውን ወደኤምባሲው ሲልኩ፣ ኤምባሲው ‹‹ሁለቱንም የሕክምና ተቋማት አላውቃቸውም አልቀበልም›› በማለቱ ገንዘባቸውበከንቱ መቅረቱን ነው፡፡

የተሻለ ሕይወትን ፍለጋ ድንበር ተሻግረው ለመሥራት፣ ቤተሰቦቻቸውንና ራሳቸውን ለማሻሻል ከተለያዩ የአገሪቱገጠራማ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የተለያዩ ችግሮችን ተጋፍጠው ለመሄድ ያደረጉት ጥረት ከንቱ መሆኑእንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡

ጋምካ የተባለው ተቋም በዜጐች ላይ እየፈጸመ ያለውን አላስፈላጊ ችግር በመቃወም የኢትዮጵያ የውጭ ሥራ ስምሪትአገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲዎች ግንቦት 14 ቀን 2004 ዓ.ም. ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ፣ ድርጊቱን ተቃውመውለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት አስታውቀዋል፡፡ ኤጀንሲዎቹ ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የተሳተፉትየኤጀንሲ ባለቤቶችና ተወካዮች ባሰሙት ተቃውሞ፣ ‹‹በጋምካና በሳዑዲ ኤምባሲ መካከል የድብብቆሽ ጨዋታ ያለይመስላል›› በማለት፣ ቀደም ብሎ ጋምካን ካደራጀው የዓረብ ባህረ ሰላጤ አገሮች ምክር ቤት በኩል በቀረበው ስሞታመሠረት፣ አገልግሎታቸው ተቋርጦ የነበሩ የሕክምና ተቋማትን ኤምባሲው ሥራ እንዲጀምሩ ማድረጉን በመጠቆምነው፡፡

የሕክምና ተቋማቱ ሥራ መጀመራቸውን የሰሙና ሰነዳቸው ታግዶ የነበሩ ዜጐች ሥራ ወደጀመሩት የሕክምና ተቋምትሲሄዱ፣ ጋምካ ስላስጠነቀቃቸው (የሕክምና ተቋማቱን) በድጋሚ ሥራ በማቆማቸው ዜጐቹ ችግራቸው ሊፈታላቸውአለመቻሉ ኤጀንሲዎቹን አስቆጥቷል፡፡ ከመንግሥትና ከሕዝብ የተሰወረ የጥቅም ግንኙነት በጋምካና በኤምባሲውመካከል ሳይኖር እንደማይቀር ግምታቸውን የተናገሩት ኤጀንሲዎቹ፣ ዋነኛ ተጠቂዎቹ እንጀራ ፍለጋ ከተለያዩ የአገሪቱክፍሎች የመጡ ዜጐች በመሆናቸው፣ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ እንዳለበትጠይቀዋል፡፡

መንግሥት ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመዋጋት ላይ እየሠራና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር እየመከረ ባለበትበአሁኑ ጊዜ፣ ጋምካ ዜጐችን ወደተከለከሉና ለሥራ ወዳልተፈቀዱ አገሮች እንዲሄዱ ዋና ተዋናኝ መሆኑን ኤጀንሲዎቹጠቁመዋል፡፡ ለአብነት ያህልም ወደ ኦማን ለመጓዝ ዜጐች ያደረጉትን የምርመራ ውጤት አሳይተዋል፡፡የሚመለከታቸው የመንግሥት መሥርያ ቤቶች በችግሩ ላይ ትኩረት በመስጠት ዜጐችን ከሕገወጥ ብዝበዛና የወንጀልድርጊት ይታደጓቸው ዘንድም አቋም ወስደው ኤጀንሲዎቹ ተለያይተዋል፡፡

ለሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ግልባጭ በማድረግ ለጋምካ ጽሕፈት ቤት፣ በኢትዮጵያ የውጭ ሥራ ስምሪትአገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲዎች ማኅበር አሠሪ ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ መዝገቡ አሰፋ የተላከው ደብዳቤእንደሚያስረዳው፣ በጋምካ አማካይነት በጤና ተቋማት የሚሰጠው የሕክምና ማረጋገጫ ሰነድ፣ ግልጽነትና ኃላፊነትየጐደለው ነው፡፡ ዜጐችን ለእንግልትና ላላስፈላጊ ወጪ እየዳረገ ነው፡፡ በመሆኑም በሚመለከተው የመንግሥት አካልየማያዳግም ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡ የማኅበሩን ፕሬዚዳንት አቶ መዝገቡ አሰፋን አነጋገርናቸው፣ ተቋሙየሚቆጣጠረው እንደሌለው ተናግረው፣ ብቃት የሌላቸውን ተቋማት በመምረጥ ዜጐችን አግባብ ያለው ሕክምና ሳያገኙበመላክ፣ በደረሱበት አገር ሲመረመሩ የተለያዩ በሽታዎች እየተገኙባቸው እንደሚመለሱና ለኪሳራ ከመዳረጋቸውምበተጨማሪ የአገርንም ስም የሚያስጠፋ ድርጊት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተደጋጋሚ አሠራሩን እንዲያስተካክል ቢጠየቅም ተቋሙ ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ፣ የሕክምና ተቋማቱከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ቢጠይቁም፣ እነሱም ምላሽ ባለመስጠታቸው የሚጠብቁት የመንግሥትን ምላሽ መሆኑንተናግረዋል፡፡ መንግሥት ዜጐቹ ገንዘባቸው የሚመለስበትን ወይም አግባብ ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ እንዲያደርግእየጠየቁ መሆኑን አቶ መዝገቡ ተናግረው፣ ምላሹ ከዘገየ አደገኛነቱን ጠቁመዋል፡፡ መንግሥት ጋምካ የሚባለውን ተቋምአግዶ የመንግሥትና የግል የሕክምና ተቋማትን እንዲያሰማራም ጠይቀዋል፡፡ ጉዳቱ ለቤት ሠራተኛነት የሚሄዱትንዜጐች ብቻ የሚነካ ሳይሆን፣ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ወስደው የሚሠሩትን ኤጀንሲዎችንም ጭምር መሆኑንጠቁመዋል፡፡

‹‹ከመንግሥት ፈቃድ ካገኘን በቅርቡ ከሌሎች አገሮች ጋር ሥራ እንጀምራለን ብለን እናስባለን፤›› ያሉት አቶ መዝገቡ፣ከጋምካ ጋር ግን እንደማይሠሩና ለዜጐች ዋስትና ከሚሰጡት ጋር ብቻ ለመሥራት በዝግጅት ላይ መሆናቸውንተናግረዋል፡፡ ከአይኦኤም ጋር የሚሠሩ የሕክምና ተቋማትንም ለመጠቀም ከአይኦኤም ጋር የመግባቢያ ሰነድለመፈራረም ጫፍ ላይ መድረሳቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የጋምካን ኃላፊዎች በጽሕፈት ቤት ተገኝተን ለማነጋገር ያደረግነውን ጥረት ‹‹ኃላፊው የሉም›› በሚል አልተሳካልንም፡፡በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ ኤምባሲንም ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ‹‹ስብሰባ ላይ ናቸው›› በሚል አልተሳካልንም፡፡ጉዳዩ በዋናነት የሚመለከተው የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን አነጋግረን፣ ችግሩ ከአቅም በላይ መሆኑንናሚኒስቴሩ ከሌሎች ከሚመለከታቸው መሥርያ ቤቶች

Posted on May 30, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a comment