ስብሐት ነጋ የቀድሞ የህወሓት አመራር አባላትን እያደራጁ ነው

TPLF power broker, Sibehat Nega

 

አውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) – የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ መስራችና የድርጅቱ የሞራልና የፍልስፍና አባት ተደርገው የሚወሰዱት አቶ ስብሐት ነጋ በ1993 ዓ.ም ክፍፍል ወቅት ከድርጅቱ የተሰናበቱ አባላትን አንድ በአንድ በማነጋገር ድርጅቱ በአዲስ መልክ ህልውናውን እንዲያጠናክር በማደራጀት ላይ እንደሚገኙ የአውራምባ ታይምስ አስተማማኝ ምንጮች ከአዲስ አበባ ገልጸዋል፡፡

‹‹መለስ እራሱን ብቻ ሳይሆን ሀወሓትንም ጭምር ገድሎ ነው የሞተው››Nየሚሉት ስብሐት ነጋ ‹‹በትጥቅ ትግሉ ወቅት የጎላ ድርሻ የነበራቸውና ችግርና መከራን ተጋፍጠው ህወሓት ውስጥ በጽናት የዘለቁ አመራሮች ወደ ጎን ተገፍተው፤ ዛሬ ድርጅቱ የእነ አዜብ መፈንጫ ሆኗል››Nማለታቸውን ጠቅሰው ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ ከመለስ ህልፈት በኋላ የስልጣን ሽግግሩ ዋነኛ አመቻች ሆነው የወጡትና በስብሐት ዘንድ በጥርጣሬ የሚታዩት የኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦን ከጥቂት የካቢኔ አባላት ጋር በመሆን ኃይለማሪያም ደሳለኝ ወደ ስልጣን እንዲመጡ ሰፊ የቤትስራ እንደሰሩ የጠቀሱት ምንጮቻችን የበረከት አላማም ከኃይለማሪያም በስተጀርባ ካሉ ወሳኝ ሰዎች መካከል ዋነኛው በመሆን አዲሱን ስርአተ መንግስት መቆጣጠር ነው ብለዋል፡፡ እንደ ምንጮቻችን ገለጻ የእነ በረከት እቅድ የምዕራባዊያን ድጋፍ ቢኖረውም በሰራዊቱና በደህንነት ውስጥ ግን ያን ያህል የድጋፍ መሰረት የለውም፡፡

አቦይ ስብሐት ከአቶ መለስ ህልፈት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀድሞው የህወሓት አመራር አባላት ጋር የተገናኙት ቦሌ ከሜጋ ህንጻ ጀርባ በሚገኘው የአቶ መለስ ወንድም (ኒቆዲሞስ ዜናዊ) መኖሪያ ቤት ሲሆን እስካሁን በደረሰን መረጃ መሰረት አቶ ስብሐት ከጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳይ፣ አበበ ተክለሀይማኖት፣ ተወልደ ወልደማሪያም፤ ቢተው በላይ፣ አብርሀ ማንጁስና ከሌሎችም ጋር ተወያይተዋል፡፡ አቦይ ስብሐት እነዚህን ወገኖች ሲያነጋግሩ አባይ ጸሐዬ፣ ሀሰን ሽፋ፣ አርከበ ዕቁባይ፣ አባይ ወልዱ፣ ቴዎድሮስ ሐጎስና ሌሎች በሀላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙ አንጋፋ የህወሃት ሰዎችን ከጎናቸው በማሰለፍ ነው፡፡

ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው ወገኖች እንደሚሉት በረከትና ስብሐት በየፊናቸው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተለይ ከመለስ ቀብር በኋላ በድርጅቱ ውስጥ የ1993 ዓ.ም አይነት ክፍፍል ሊፈጥር የሚችል ቢሆንም ሰራዊቱ ግን የእነ አቦይ ስብሐትን ጎራ በመደገፍ ኃይለማሪያምን አሰናብቶ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እስከማስቀመጥ ሊሄድ ይችላል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ለሁለቱም ቡድኖች መከፋፈል እንደ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ እየተጠቀሰ ያለው የኃይለማሪያም ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሳይሆን ከኃይለማሪያም ጀርባ ባለው መጋረጃ ውስጥ ያለውን ጠረጴዛ
የመቆጣጠር ጉዳይ ነው፡፡

በእነዚህ ወገኖች እምነት አሁን የሚፈጠረው ክፍፍል ከ1993ቱ የሚለየው ክፍፍሉ በህወሓትና በሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል የሚፈጠር በመሆኑና እንደ 1993ቱ ሰዎችን በማሰርና በማባረር ችግሩን ለመፍታት መሞከር የአገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥለው ይችላል ብለዋል፡፡

Posted on August 28, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: