ዜናን በጨዋታ፤ የተሜን ድምፅ ሰማሁት!

የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ መንግስት ተመስገን ደሳለኝን ከተቆለፈበት እስር ቤት በነፃ አሰናብቶታል። ቆይ በቅንፍ እናሳምራት፤ (ተስፋ የተጣለበት የኃይለማሪያም ደሳለኝ መንግስት ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ጀግናውን ተመሰገ ደሳለኝን ከእስር ፈቶታል…! ነሐሴ 22 ሁለት ሺህ አራት አመተ ምህረት!)

ግድ የላችሁም ዝም ብለን ተስፋ እናድርግ ቀጣዩ ቀን ጥሩ ሊሆን እንደሚችል እንገምት። እርግጥ ነው ባለፈው ጊዜ መለስ ሞቱ ሲባል ስቀሀል ተብሎ የአንድነት ቤሄራዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዘርይሁን ገብረ እግዚአብሄር ድብደባ እንደደረሰበት ሰምተናል፤ እርግጥ ነው እነ ርዮት አለሙም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ጋር ተያይዞ በ120 ብር የሚሸጥ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሀዘን የሚገልጥ “ቲሸርት” ግዙ ተብለው እምቢኝ በማለታቸው ጥርስ እንደተነከሰባቸው አንብበናል፤ እርግጥ ነው ምሽት ቤቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞተው እንዴት ዘፈን ከፈታችሁ ተብለው እየታሰሩ ቡና ቤታቸውም እየታሸገባቸው እንደሆነም ነጋሪዎቻችን ነግረውናል። ይሄንን ይሄንን ስንሰማ የሰብአዊ መብት ጥሰቱ ከበፊቱመው በላቀ መልኩ ሊቀጥል ነውን…!? ብለን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት እኩል እየሆነ ላለው ነገር አዝነናል።

ዛሬ የሰማነው የምስራች ደግሞ አዲሱ መንግስት ተስፋ የሚጣልበት ይሆን!? የሚያስብል ነው። ተመስገን ደሳለኝ ከተከሰሰበት ማስረጃ አልባ ክስ በነፃ ተለቋል።

የተሜን ድምፅ ዛሬ ሰማሁት። ቅድም ይፈታል የሚለውን ዜና እንደሰማሁ አንድ ግር ያለኝን ጥያቄም ጠየኩት፤ “አቃቤ ህግ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ስል ክሱን አቋርጫለሁ ነው ያለው። ተጨማሪ ምርመራ ምንድነው…?” ተሜም መለሰልኝ… “እንግዲህ ደም እና ሽንት እንደሆነ እንጃ እኔ በነፃ መለቀቄን ነው የማውቀው” አለኝ። (በሳቅ መሞት!)

ትላንት ኃይለማሪያም ሆይ ቶሎ ና! ብዬ ነበር። እጅግ ወዳጃችን የሆነው የሰብአዊ መብት አክቲቪስቱ ዘሪሁን ተስፋዬ እንዳለኝ ከሆነ “ይሄ የተሜ ውሳኔ መቶ ብር ቀምቶ አስር ሳንቲም የመመለስ ያኽል ነው” ብሎኛል። “እንደ ዘርሽ አባባል ገና ዘጠና ሳንቲም ይቀረናል። ይሄውም መመለሱ በጣም ተስፋ ሰጪ ነው። በቀጣይም ቀሪዎቹ እንዲመለሱልን እንጠይቃለን። ያኔ ሁላችንም በአንድ ድምፅ ኃይለማሪያም ሆይ ቶሎ ና! እንላለን” ብሎኛል።

Posted on August 28, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: