ሼክ መሃመድ ሁሴን አል አሙዲ በህይወት አሉ

ሰሞኑን የጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር በተያያዘ መጥፋታቸው ሲነገርላቸው የነበረው እና ቀጥሎም ሞተዋል በሚል በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን መድረክ ሲነገር የቆየው የባለሃብቱ ሼክ መሃመድ ሁሴን አል አሙዲ በህይወት መኖራቸው ተረጋገጠ ። የባለ ብዙ ኩባንያ ባልተቤት እና የገቢ ምንጫቸው በአረብ አገር የሚገኘው የነዳጅ ኩባንያ እንደሆነ የሚነገርላቸው እኝሁ ባለሃብት በዚህ ሳምንት ውስጥ አዲስ አበባ ገብተው መታየታቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወሳል ።በዛሬው እለትም የጠቅላይ ሚንስትሩ አስከሬን ለማየት ወደ ቤተመንግስት አምርተው የህሊና ጸሎት አድርገው መመለሳቸውን የማለዳ ታይምስ ሪፖርተር ከስፍራው ዘግቦአል ።ሼኩ ምክንያቱ ምንም ባልታወቀበት ምክንያት ከወዳጃቸው ጠ/ሚንስትር ሞት በሁዋላ ያለመታየታቸው ብዙ ስጋትን በህብረተሰቡ ውስጥ ፈጥሮ እንደ ነበር የገለጸው የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ በአሁን ሰአት የህወሃት አባላት ክፉኛ ታመዋል እየተባለ አገር በሚታመስበት ወቅት እሳቸውም ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸውም ታምው ነበር፤ በህይወት አልፈዋል የሚለው በሃገርቤት እና እንዲሁም ኢሮጵ እና አሜሪካ ተሰራጭቶ መወራቱ እጅግ አሳሳቢ ሆኖ ነበር ።ይበልጥ በሼክ መሃመድ ሁሴን አላህሙዲ ስር የሚተዳደሩት ከ20.000 በላይ የሚጠጉት የኢትዮጵያ ሰራተኞች ከፍተኛ ውድቀት ውስጥ ሊገቡ ይችላል በሚል ስጋት ህብረተሰቡ ስጋታቸውን በግልጽ አንጸባርቀዋል። የሼክ መሃመድ ሁሴን አል አሙዲ በምርጫ 97 አ.ም የንብ ምልክት ያለበትን ቲ-ሸርት ለብሰው መታየታቸው ህብረተሰቡን አስከፍቶ የነበረ ቢሆንም ለሃገሪቱ የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት ስራ እና ደሃውን ህብረተሰብ ከስራ አጥነት ማላቀቃቸው ትልቁ ራእያቸው ነው ሲሉ አንዳን ወገኖች ገልጸዋል። ሆኖም ግን በሚድሮክ ኢትዮጵያ የወርቅ ማእድን ስራ በሚደረገው የሰራተኞች ጉልበት ብዝበዛ እና የወርቅ ማእድን ወደ ሌሎች ሃገሮች ቅድሚያ ተሰጥቶ መላኩ ደግሞ የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት ማራቆት ነው የሚሉም አልታጡም ። ይህም ሆኖ ግን በህዝብ ዘንድ መከበር እና መወደዳቸው እስካሁንም ድረስ እንደጸና ነው ።

ሼክ መሃመድ ሁሴን አል አሙዲ በህይወት አሉ

Posted on August 29, 2012, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: