ኢህአዴግ መበጠስ ያልቻለው ሰንሰለት!!!

ጊዜው የጋራ ሃላፊነትን ለመወጣት ለሚተሳሳቡና ለጋራ ጥቅሞቻቸው መከበር ውጤት ለሚያስመዘግቡ እንጂ ለጥቂት ግለኛ ሆዳሞች እንዳልሆነ እስከ መጨረሻው በመፅናት ታሪክ እንሰራለን!!!! ህዳር 9 ከማለዳው አንስቶ ወደ ቃሊቲ የጎረፈውን በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ህዝበ ሙስሊምን በማስተናገድ ታላቅ አርዓያ የሆናችሁ ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶችን እጅግ በጣም እያመሰገንን በዚህ ድንቅ ተግባራችሁ ትቀጥሉ ዘንድ ለማታወስ እንወዳለን፡፡ በእሁዱ ያልታሰበ መስተግዷችሁ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያን ወገኖቻችንን እንዳኮራችሁ ሁሉ ከሀገር ውጪ በአሜሪካና አውሮፓ በመካከለኛው ምስራቅና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በዚህ የአንድነትና የወገንተኝነት ስሜታችሁ ትርጉም ያለውን ስራ በመስራታችሁ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለፅ ቃላት አልበቃ ያላቸው መሆኑን በተለያዩ ድህረ-ገፆችና በጣም ብዙዎች በእጅ ስልክ መልዕክት እያደረሱን ይገኛሉ፡፡ በሰላምና መቻቻል በፍቅርና አክብት ለዘመናት አብሮ የኖሩትን የአንድ እናት ልጆችን ለማነካከስና ለማባላት የኢህአዴግ መንግስት ያደረገው ጥረት ገና ከጅምሩ የከሸፈ ቢሆንም እንኳ የእሁዱ የቃሊቲ ትእይንት ግን የኢህአዴግን ሸፍጥ ዳግም ላለመስማትና ላለማየት ጉድጓድ ምሶ ህዝበ ክርስቲያኑና ህዝበ ሙስሊሙ ድንጋይ ጭኖበታል ያሉ ሚሊዮኖች ናቸው፡፡ ይህን ሰብአዊ ወገናዊና ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ እንዳለብን ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ያሉ ወንድምና እህቶች በጥብቅ ያሳሰቡን ሲሆን የዚህ ትውልድ የመጀመሪያውና ትልቁ ሃላፊነትም ይህ መሆን እንዳለበት ሁሉም አስምረውበታል፡፡ እኛም ህዝበ ሙስሊሞች ከዚህና ለዚህ ምክንያት በሆነው የእሁዱ መቼም በማንረሳው ውለታችሁ ተነሳስተን በተራችን የህዝበ ክርስቲያን የእምነት አባቶች ባነሱት የእምነት ቦታችን አይደፈር ጥያቄአቸው ምክንያት በግፍ እንደታሰሩት ኮሚቴዎቻችን ከዋልድባ ገዳም ታፍሰው ለእስር ለተዳረጉት ንፁሃን የሀይማኖት አባቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ወደ ቀድሞ ህይወት መመለስና ለመብታችሁ መከበር በምታደርጉት ጥረት ከጎናችሁ እንደምንቆም ለመግለፅ እንወዳለን ፡፡ የኢሳት(ESAT)፣ቪኦኤ(VOA) እና የዶቼቬሌ(DW) ጋዜጠኞችን እጅግ በጣም እናደንቃችኋለን እናከብራችኋለን፡፡ህዝቡ በሚከፍለው ግብርና ከውጪ በሰበብ አስባቡ በሚለምኑት የሚተዳደሩት የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ጆሮ ዳባ ልበስንና አይኔን ግንባር ያድርገውን ተረት በእውን ሲያሳዩን እናንተ ግን ለወገናችሁ እና ለሙያችሁ ያላችሁን ክብርና ታማኝነት ለመግለፅ የምታደርጉት ጥረትና መስዋትነት ሰማንያ ሚልዮን ህዝብ በሚኖርባት ሀገር አንድ እንኳ የህዝብን ብሶት የሚያሰማ ሚዲያ በሌለበት አንድ ለእናቱ ሆናችሁ የሰራችሁትን መልካም ስራ በቃላት መግለፁይከብዳል……..፡፡ ለህዝባቸው ነፃነትና ሰብአዊ መብት መከበር በመታገላቸው ለእስራትና ለእንግልት ሲብስም ለስደትና ለሞት የተዳረጉትንና እየተዳረጉ ላሉት ሁሉ በአጠቃላይ ለወገኖቻቸውና ለሀገራቸው መልካም በማሰባቸው የሆኑትን ሁሉ ሆነው የከፈሉት መስዋትነት በከንቱ አይቀርም፡፡የሀይማኖት፣የሰብአዊ መብት ማህበራት፣ጋዜጠኞችና እንዲሁም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የጋራ የሆነውን የፍትህ እጦት ጩኸታችን መልስ የሚሆነውን ውጤት ኢንሻአላህ በቅርቡ እጅ ለእጅ ተያይዘን በአንድነት ወደ ተፈላጊው ውጤት እንደርሳለን፡፡ የአንድ ፓርቲ ሳይሆን የህዝብ ሀገር የሆነችን ኢትዮጵያ ለማየት ጓጉተናል፡፡ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት!!!!!!!!!!!!!! ነፃነት ለሙስሊሞች! ነፃነት ለክርስቲያኖች! ነፃነት ለፕሬስ ውጤቶች! ነፃነት ለሰብአዊ መብት ማህበራ! ነፃነት ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች! posted by Aseged Tamene

Posted on November 21, 2012, in ETHIOPIA ENGLISH and tagged . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: