በደቡብ አፍሪካ በአቡነ ያዕቆብ ላይ ተቃውሞ ለማሰማት መዘጋጀታቸውን ምዕመናኑ ገለጹ

(ዘ-ሐበሻ) በደቡብ አፍሪካ የሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ሊቀጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ም ዕመናኑ ከፍተኛ
ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ በስፍራው ለሚገኘው የዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ዘጋቢ ገለጹ። አዲስ አበባ ስድስተኛውን
ፓትርያርክ ለመምረጥ የሄዱት አቡነ ያዕቆብ ወደ ጽረ አርያም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ሲመለሱ ተቃውሞውን ለማድረግ
እንደተዘጋጁ የገለጹት ምእመናኑ ሊቀጳጳሱ የቤተክርስቲያን አንድነትን ካሰናከሉት የወያኔ ጳጳሳት ጎን በመቆማቸው
እንደሚያወግዟቸው ነው የገለጹት።
በ1997 ዓ.ም የቅድሥት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ በነበሩበት ወቅት ተማሪዎቹ የአድማ በመቱበት ወቅት ለመንግስት
በመሰለል የተማሪዎቹ ተቃውሞ እንዲረግብ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ እንዳደረጉ የሚገነገርላቸው አቡነ ያዕቆብ በደርግ
ስርዓት የባሀር ሃይል መቶ አለቃ እንደበሩ የሚያውቋቸው ወገኖች ይናገራሉ። ይህን ተቃውሞ በማርገብ ለመንግስት
ያላቸውን ታማኝነት በማሳየታቸው በ1998 ዓ.ም ሃምሌ ስምንት በደቡብ አፍሪካ ሊቀጳጳስ ሆነው የተሾሙት አቡነ
ያዕቆብ በተለይ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ወደ ደቡብ አፍሪካ ተመላልሰው ሲታከሙ ለዋሉት ውለታ
ሕይወታቸው ከማለፉ በፊት የአፍሪካ አህጉር ሊቀጳጳስ ተብለው በሱዳን፣ በጅቡቲ እና በኬንያ ያሉ አብያተ
ክርስቲያናትን እንዲቆጣጠሩና እንዲሾሙ ተደርጓል ያሉት የዘ-ሐበሻ ውስጥ አዋቂዎች የአቡነ ያዕቆብ ዓለማዊ ሥምም መቶ
አለቃ አስማማው እንደሚባል ነግረውናል።
የደቡብ አፍሪካው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ እንዳለው የወያኔን ሥርዓት ጥለው በተሰደዱ የደቡብ አፍሪካ ምእመናን ገንዘብ ወደ
ኢትዮጵያ በመሄድ የቤተከርስቲያን አንድነት እንዳይሳካ ካደረጉት የሃገር ቤቱ የወያኔ ደጋፊዎች ጋር አብረው
መወገናቸው በተለይ በደቡብ አፍሪካ በሚገኘው የጽረ አረአያም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ምእመናን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን
በማስከተሉ ሕዝቡ በአንድ ላይ ተቃውሞውን ለማሰማት ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ አማኞች በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል ሊደረግ የነበረው
እርቀ ሰላም የሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ተልከው አሜሪካ የሄዱት ተደራዳሪ አባቶች ሳይመለሱና የ እርቁን ውጤት ሳይሰሙ
የመንግስትን ፍላጎት ለማሟላት 6ኛ ፓትርያርክ መምረጣቸው እንዳስቆጣቸው በተለያዩ መንገዶች በመግለጽ ላይ ናቸው።

ይህን ጉዳይ ተከታትለን እንደምናቀርብ ከወዲሁ እንገልጻለን።

Advertisements

Posted on March 5, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: