ኢትዮዽያውያን ታላቅ ተቃውሞ ሰልፍ በኖርዌ ኦስሎ በ ኢሳ አብድሰመድ by Issa Abdusemed

የዚሁ ሰላማዊ ሰልፉ አላማና መነሻው የዓማራውን ህዝብ እና የሙስሊም ወንድሞቻችንን መብታቸው ይከበር በሚል ሲሆን የጥላቻ መርዝ እየረጨ እንዳንተባበር እኛን ሆድና ጀርባ አድርጎ ለያይቶ እየገዛን የምንኖረው እስከመቼ በሚል የተዘጋጀ ነው ቁጥራቸው ከ200-300 የሚገመት በተለያየ ዕድሜ ክልል የሚገኝ ህዝብ እንደተሳተፈበት የተደረገው ይህ የተቃውሞ ሰልፍ ከኦስሎ… ሴንተራል ሰቴሽን በተለምዶ (የነብሩ ሃውልት ካለበት) በመነሳትና የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ እና በማሰማት በመጀመሪያ ያመራው ወደ ኖርዌይ ፓርላማ ሲሆን ቀጥለውም ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ የወያኔን TPLF ጨቋኝ እንደሆነና ዜጎችን የዘር ግንዳቸውን በማጥፋት ከመኖርያቸው በማፈናቀል ባመለካከታቸው ብቻ እንደሚገርፍ እንደሚያስር እንደሚያሰቃይና እንደሚገደልም በመግለጽ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ዛሬ በዓለማችን ዙሪያ ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለሰብኣዊ መብትና ለዲሞክሲ ስርዓት መከበር ህዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዞው፣ መድፍና ታንክ ሳይበግራቸው እምቢ ለነፃነቴ ብለው አደባባይ በመውጣት በጉልበት ስልጣን ወንበር ላይ ተቀምጠው ለዘመናት ሲጨቁኑና ሲገሉ የነበሩ አምባገነናዊ ስርዓቶች በህዝባዊ ዓመፅና በተባበረ ክንድ ሳይወዱ በግድ ከስልጣናቸው ዓውርደው ሲጥሉዋቸው በዓይናችን እያየን ነው።DSC_0162 oslo1አስተዳደጋችንም ሆነ አኗኗራችን፣ ማህበራዊ ተሳትፎአችን በእድር በእቁብና በጋብቻ በማንኛውም ማህበራዊ ተሳትፎአችን ሳንለያይ ሀዘናችንም ሆነ ደስታችን አብረን የምንካፈል፣ “ዓለም ያደነቀን ድንቆች ደማችን አንድ የሆነ ኢትዮዽያዊ ህዝቦች ነን, አያሌ የገበሬ ልጆች ለመብት ለነጻነት ሲሉ በከፈሉት የሕይወት መስዋዕትነት ተረማምዶ አወጣሁት ባለው ህገ መንግስት ምዕራፍ 2 አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ 3 እና ምዕራፍ 3 አንቀጽ 27 መሠረት መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባና የዜጎች የእምነት ነጻነትን እንደሚያከብር በግልጽ ቢያስቀምጥም ገና ስልጣነ ወንበሩን ከተቆጣጠረ እለት ጀምሮ የሃይማኖት ተቋማትን በመዳፈር በተለይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና በሙስሊም ኢትጽያውያን የዕምነት መሪዎች ከህገ ሃይማኖትና ከምዕመናን ፈቃድና እውቅና ውጪ የራሱን ተወካዮች በግድ በማስመረጥ በቀጥታ የዕምነት ተቋሞቹን በፖለቲካ መዋቅሩ ስር በማድረግ በሃገራችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የዘር ማጥፋት የእምነት ነጻነት በመዳፈር ላይ ይገኛል።

የወያኔ አገዛዝ ከዚህም በላይ ሃይማኖትን በሃይማኖት ላይ በማስነሳት በስውር ሴራ በመጠቀም ለብዙ ዜጎች ሞት ስደትና ለቤተክርስቲያናት እና ለቤተ መስጊድ መቃጠል ምክንያት በመሆን ለሺህ ዘመናት በሰላምና በፍቅር በኖረው ሕዝባችን ላይ መለያየትን በማንገስ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም በየግዜው በተላላኪዎቹ አማካኝነት ሲያካሂድ የቆየው ሠይጣናዊ ተንኮል አልበቃ ብሎት የዓማራውን ህዝብ በግብረ ኣበሮቹ ሆድ አደሮች እየተጠቃ ነው :: ይህም በሌሎች የዓማራ ባልሆኑ ነግዶች የዓማራው ህዝብ ሆን ብሎ እንደጠላት እንዲታይ እየተደረገ ነው :; ስለሆነም በአማራው ህዝብ ላይ እየተሰነዘረው ያለው ጥቃት መቆም አለበት ;;IMGP0096 ታዲያ እኛ ኢትዮጵያውያን በጀግኖች አባቶቻችን በከፈሉት ክቡር መስዋእትነት ማንነታችንን ጠብቀን ለጥቁር ዓለም ሁሉ የነፃትና የአልገዛም ባይነት ተምሳሌት ሆነን ታፍረንና ተከብረን የኖርነውን ያህል ዛሬ በተለያዩ ቦታዎች የዲሞክራሲና የነፃነት ብርሃን በሚፈነጥቅበት የሰለጠነ ዘመን እንዴት ወደኋላ ወደ ጨለማ ዘመን ተመልሰን የባርነት ተምሳሌት ለመሆን በቃን? በዜጎቻችን ላይ እየደረሰው ያለው አፈና በሀገሪትዋ ያለው ሁኔታ ራሱ ተናጋሪ ሆኖ ሳለ በአንድ አምባ ገነናዊ መንግስት አገዛዝ ስር ወድቀን፣ በየተራ እየተመታን፣ በረሃብ አለንጋ እየተገረፍን፣ ዘላለም የበይ ተመልካችና የውጭ እጅ ጠባቂ ሆነን እስከመቼ እንኖራለን? ወያኔ በመካከላችን የጥላቻ መርዝ እየረጨ እንዳንተባበር እኛን ሆድና ጀርባ አድርጎ ለያይቶ እየተገዛን የምንኖረው እስከመቼ ነው ? በማንኛውም መንገድ ታግለን መብታችንን ለማስከበር ለመነሳት ካልቆረጥን በስተቀር ከዚህ በላይ የቀረው እንደ ጥንታዊው የባሪያ አሳዳሪ ስርዐተ ማህበር በቁማችን መሸጥ ብቻ ስለሆነ ለመብትና ነጻነታችን እንዲሁም ለሃይማኖታዊ ስርዐታችን መከበር የሚያስፈልገውን ዋጋ ለመክፈል መቁረጥ ይኖርብናል

ፀሀፊውን ለማግኘት issaabdusemed@gmail.comm     ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር

Posted on April 18, 2013, in ETHIOPIA ENGLISH and tagged , , , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: