ነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሉግዲና በበረከት ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ።

1ነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በግንቦት 24-2005 ዓ.ም ከወያኔ መከላከያ ጋር በሉግዲ ባካሔደው ውጊያ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል። በግንቦት 25-2005 ዓ.ም በቀጠለው ውጊያ በሁመራ ልዩ ስሙ በረከት በተሰኘ ስፍራ ከአምባገነኑ አገዛዝ 35ኛ ክፍለጦር እና ከሚሊሻ ሰራዊት ጋር በተካሄደው ውጊ….ያ በተከታታይ በስምንት/8/ ዙር ፋታ የለሽና እልህ አስጨራሽ ውጊያ 148 ሙት፣ 374 ቁስለኛ፣ 31 ክላሽንኮፍ፣ጠመንጃ 47 የእጅ ቦንብ ፣2 ስናይፐር፣ 3 መትረየስና የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርኳል። በእለቱ በተካሄደው ውጊያ የአካባቢው ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ባሳየው ከፍተኛ ወታደራዊ ጀብድ መደነቃቸውንና ድርጅቱ ያለውን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ብቃት ያሳየ መሆኑን ገልፀው ፣ ወጣቶችም በዚህ ሃይል ጠላት ማሽመድመድ የሚችል ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል ሲሉ ተናግረዋል። ለስምንት ዙር ያህል በተካሄደው ውጊያ የአገዛዙ ቅጥረኛ ጦር ቁስለኞች ወደ ዳንሻ፣ ማይካድራ፣ ሁመራ የመሳሰሉት ቦታዎች በሚገኙ የጠላት የሕክምና ተቋማት ቁስለኞችን እየጫኑ ማጓጓዝ ላይ ተጠምደው እንደዋሉና ገሚሶቹ ከፉኛ በመቁሰላቸው ሕክምና እርዳታ ሳይጀመርላቸው መሞታቸው ታውቋል። ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በደረሰበት ድንገተኛ ጥቃት አከርካሪው የተሰበረው 35ኛ ክፍለ ጦር በድንጋጤና ፍርሃት ውስጥ ተሸብቦ በመጨነቅ ላይ በመሆናቸው የአካባቢውን ማህበረሰብ ያለስራው እየተንገላታ እንደሚገኝ ታውቋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አሁንም ቢሆን ወያኔው ለሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች መልስ ባለመስጠት አቋሙ የሚቀጥል ከሆነና ስለ አባይ ግድብ እያወሩ ሕዝብን ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ መግዛቴን እቀጥላለሁ የሚል ከሆነ በሁመራ ልዩ ስሙ በረከት እንዲሁም በሉግዲ በ35ኛ ክፍለ ጦርና በሚሊሻ ላይ የተወሰደው አኩሪ ወታደራዊ እርምጃ አይነቱን ቀይሮና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስታውቃል። በግንቦት 24 እና 25-2005 ዓ.ም በተካሄደው ውጊያ በድምሩ 192 ሙት 440 ቁስለኛ ቁጥራቸው የበዛ ተተኳሽ መሳሪያዎችን ከነትጥቃቸው በመማረክ የታሪኩ አካል የሆኑ ተዋጊ አርበኞች እንዳሉት እኛ ለሀገራችን ኢትዮጵያና ሕዝቧ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ፊት ለፊት በጠመንጃ አረር እየተፋለሙ እንደሚገኙና ትግሉ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚደረግ እንደመሆኑ መጠን የሁሉም ርብርብና ተሳትፎ አስፈላጊና የውዴታ ግዴታ በመሆኑ የአገራችን ችግር መፍትሔ ለመስጠት በአምባገነኑ የወንበዴ ቡድን በሆነው ወያኔ ላይ እንዝመት ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

Advertisements

Posted on June 4, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: