ኢቲቪ ሰው ምን እንደሚለውም ያውቃል። ታዲያ ሰምቶ እንዳልሰማ ለምን ይሆናል?

በኢሳ አብድሰመድ/ by IssaAbdusemed

ወያኔዎች ጭንቅ ጥብብ ብሏቸዋል ህዝቡን ለማደናገር የሞከሯቸው አሳፋሪ ድርጊቶች አልያዝላቸው ብሎ ሕዝቡ አደባባዩን በመሙላቱ በመደናገጣቸው ምክንያት ፕሮፓጋንዳው ሁሉ ጠፍቶባቸዋል…..መንግስት ስራው ሊሆን የሚገባው በአማኞቹ መካከል ክፍተት ለመፍጠር የእምነቱ  አስተምህሮ ሳይገባቸው አብያተክርስትያናት ላይ ክብሪት የሚለኮሱትን ይህ አንባገነናዊ ድርጊት በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይም ተግባራዊ በመደረጉ ምዕመናኑ የመንግስትን ድርጊት በመቃወም ከአንድ አመት ለበለጠ ጊዜ ጠንካራ ሰላማዊ ትግል አድርገዋል፤ እያደረጉም ይገኛሉ፡፡  ሰዎች በማደን ፍርድ ፊት ቢያቀርባቸው ያለው ነገር የተፈጠረው ነገር በረገበ ነበር ፤ ይህን ማድረግ ሲገባው ይህን  ፤ ከውጭ በብር የሚረዱ ሰዎች  እንደሆኑ ደርሶባቸው ሳለ ችግሩን ለህዝቡ ገልጾ ውጤቱን ግን መግለጽ ሲሳነው ተመልክተናል ፤ ግልፅ የመብት ጥያቄዎች ብልሀት የተሞላበት ምላሽ መስጠት ያቃተው የኢህአዴግ መንግስት እየወሰዳቸው ያሉት ኢህገመንግስታዊ እርምጃዎች ያሳስቡናል፤ በሙስሊሙ ሕብረተሰብ ላይ እየደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ለመድረሱ አሁንም መፍትሄ ሊመጣ  የሚችለው መንግስት ከእምነት ተቋማት ላይ እጁን ሙሉ በሙሉ በማንሳት ነጻ ጋዜጠኞችን በመፍታት   ፤የህዝብእና የአገሪቱን ሃብት እና ንብረት የዘረፉ ባለስልጣናትን  አጋልጦ ፍርድ ቤት በማቅረብ ትክክለኛ ቅጣታቸውን ሲያገኙ ለማህበረሰቡ ያሳይ ፤ ሙስሊሙም ሆነ  ክርስትያኑ የውስጥ ችግሩን በራሱ አካላት እንዲፈታ ያድርግ ፤ በሁለቱም ወገን ተከሰቱ የተባሉ ችግሮች ህዝብ ፊት በማቅረብ ማህበረሰቡን በማወያየት የመፍትሄ አቅጣጫዎቹን ህዝቡ ራሱ እንዲያመላክት ያድርግ ፤ ያለፉትን መልካም ተሞክሮዎች በመውሰድ የማዳበር ስራ የሃይማኖት አባቶች እንዲሰሩ መንገዱን ያመቻች ፤ ከዘመናት በፊት የተደረጉ የእምነት ነጻነት ገፋፈዎችን ነገ ዳግም እዳይፈጠሩ የማድረግ ስራ ይስራ: በአገራችን የነጻ ሚዲያዎች መስፋፋት ይኑር ብዙዎቻችን የኢቲቪን መደጋገም፣ ማጋነን፣ ማጣመም፣ ማሰልቸት እንደ አንድ ትልቅ ችግር እንቆጥራለን።

ያንን ከበቂ በላይ ብዙ ጊዜ አስረድተናል። ግን ደግሞ አይሰለቸንም፤ አዲስ ነገር በመጣ ቁጥር ተመልሰን  ስለዚሁ ነገር እንነጋገራለን። ለመሆኑ ይህንኑ ችግር የምንለውን ነገር ኢቲቪን የሚቆጣጠሩት ሰዎች እንዴት የሚያዩት ይመስላችኋል? እንደችግር  ቢያዩት ኖሮ እስከዛሬ ይቀይሩት ነበር። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ይህን ነገር የሚያዩት ሊያሳኩት ለሚፈልጉት አላማ
ሲባል እንደሚከፈል ዋጋ ነው። ስለዚህ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንዲሉ ኢቲቪ ይህን ጠባዩን እንዲቀይር ከጠበቅን እየተሳሳትን ያለነው እኛው ነን። ስኬታማ የሆነለትን መንገድ ለምን ይቀይራል? ኢ.ቲ.ቪ ከበሩ ላይ እንኳን የሚፈፀመውንም ተግባር ቀጥታ እንደወረደ የማስተላለፍ ችሎታ የለዉም የውሸት ሚደያ ነው :: ሰማያዊ ፓርቲ እንኳአን በ ኢትቪ በር ላይ ያደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ቀረጻውን ለማድበስበስ ቢሞክርም ሃቁ ግን ይህን ይመስል ነበር ወዳጆቼ??  ምን አይነት የቴክኒክ ችግር  አጋጥሟቸዉ ይሆን ይችን እንኳ በመቅረፅ ድምፅ መመዝገብ ያቃታቸዉ ??

(ምንም የመብት ጥያቄ በቁጥር መወሰን ባይኖርበትም) የመንግስት ባለስልጣናትና ደጋፊዎቻቸው የቁጥር ጨዋታ ውስጥ በመግባት ሊያሳንሱትና ሊቀንሱት የፈለጉትን ሰልፈኛ እንደ ረጋ ውሀ ተከማችቶ ይመልከቱት፦

youtube https://www.youtube.com/watch?v=KB34Q2NqlmU]

በመጨረሻም ሰማያዊ ፓርቲ ያስተላለፈው መልክት እስከ ፫ ወር ለኢትዮዽያ ህዝብ በቂ መልስ እስካልሰጠ ድረስ የተቃውሞ ሰልፉ አንደሚቀጥል ገልፀዋል::

ቸር ያሰማን     ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር

Advertisements

Posted on June 4, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: