የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴረሽን የኢትዮጵያን ህዝብ በሽተኛ አደረገው

 BY   Dawit Amare  እናንተ “የሚድያ አካላት በተለይ በእግር ኳሱ ዙሪያ እንሰራለን የምትሉ ” ሰዎች ደግሞ የኢትዮጵያን ህዝብን ገደላችሁት! ትናንት ሰኔ 09 2005 ዓ.ም በኢትዮጵያ ህዝብ እጅግ በጣም ልዩ ቦታ የሚሰጣት ቀን ናት/ነበረች/፡፡ ማለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ እስከዚያች ቀን ድርስ ታይቶ የማይታውቅና ብዙዎቻችን በቅርብ ይፈጸማልም ብለን ያልገመትነ ሥራ ተሰርቶ ነበረ… የሰው ደም በላብ አማካኝነት እንደ ፍሉሃ ሲንተከተክ ማየት በጣም ውሱን ጊዜ የሚከሰት ነው፡፡ በአጭሩ በመጠጥ ከሚሰከረው የበለጠ በደስታ የሰከሩት ብዙ ሚልዮኖች ኢትዮጵያዊን የኳስ እና የሀገር ወዳዶች ነበሩ፡፡

ምን ያደርጋል ከጊዜ ወድህ በቅርብ ዘመናት አወቅን በሚንለው ትውልድ ውስጥ የተፈጠረ አንድ ክፍተት ተከስቶዋል እሱም መረጃን በወቅቱና ለሚፈለገው አካል በትክክል አለመስጠትና የመደበቅ አባዜ ተጠናውቶናል፡፡ ከአሁን በኃላ ጥሬ መረጃ ስል / ዳታ/ ሚለውን እና ትርጉም ያለዉ መረጃ ስል ደግሞ /ኢንፎርሜሽን/ ማለቴ እንድታወቅልኝ፡፡ እኛ ዛሬ ላይ ያለነው አብዛኞቻችን ወደ ገንዘብነት የሚቀየረውን ጥሬ መረጃ ቀርቶ እኮ አባት የልጁን እድሜ እኮ የሚደብቅበት ጊዜ ላይ ነን ያለው፡፡ ይህ አባዜ ነው እንግድህ ሀገራችንን እና ህዝባችንን ያዋረደው፡፡ ጥሬ መረጃን በአግባቡ አለመያዝ የሚንሰራው ሁሉ የመጨረሳን ውጤት ብቻ እና ከገንዘብ ጋር ያለውን ሥራ ብቻ መሠራት አባዜ ይህንንም ለመፈጸም የሰውን ህይዎት እስከማትፋት የሚደርስ ፍላጎት የተጠናወተን፡፡ እስቲ የትናንቱን ደስታ በገንዘብ ተሚኑት የሚቀነሰብን 3 ነጥብንም የገብዘብ ዋጋ አውጡለት? እንግድህ ይህ ነው ጥሬ መረጃን መደበቅ የሚስከፍለው የመጨረሻ ትርጉም ያለውን መረጃ፡፡
እንደ እኔ ከሆነ የችግሩ ዋና ተጠያቂ አካል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴረሽን ይሆናል፡፡ ይህ ተቋሚ ግን በብዙ መልኩ የሚናወቅው ነው ለእኔ ግን የኳስ ተንታኞች፣ ባለሞያዎች ነን መረጃም እንዳላቸው ነጋ ጠባ ጆሮዋቻችንን በአውሮፓ ኳስ የሚያደነቁሩን የሚድያ ሰዎቸንን ነው የሚወቅሰው፡፡ ምንአለ አንድን የአውሮፓ ኳስ ከመጀመሩ 3 እና 4 ሰዓት በፊት ለጆሮ የሚሰቀጥቱ ቃላትን ከሚናገሩ ለሀገርና ለወገን የሚጠቅሚ የሚታደግ ስራ ብሰሩ / በጩሄት ብዛት ስራ/ቤት ብሥራ ኖሮ አህያ ቤት ትሰራ ነበረ ነው ያለው አንድ ፈላስፋ /እንድሉ፡፡ የአንድን ጠአውሮፓ ተጫዋች የተወለደበትን ቀን ከሰቶች ጋር ያለውን ግንኙነት ወዘተ ከሚዶሰኩሩ ሀገርን ከጥፋት የሚታደግ ሥራ ብሰሩበት ኖሮ፡፡ ደግሞ እኮ እነዚሁ ስዎችን ናቸው እኮ ያንን ሞቶ የገደለንን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴረሽን የሚወቅሱት ፡፡ ከእጅ አይሻል ዶማ እንደተባለው፡፡ የሚታየውንማ ማንም አይቶ መናገር ይችላል ዕድሉ ከተሰጠው፡፡
ማንም እኮ አጋጠሚውን አጥቶ ነው እንጅ ቲቪ/TV/ እና የተወሰኑ የመረጃ ሳይቶችን /መረብን/ አይቶ ማውራት ይችላል ቁምነገሩ ህይዎት/ኢንፎርሜሽን/ ማናገሩ ነው ፡፡ ለእኔ ሚድያ ማለት ትርጉም ያለው የመረጃ /ኢንፎርሜሽን/ ምንጭ ነው፡፡ ትርጉም ያለው የመረጃ ማለት ደግሞ ህይወት ነው በዘመናዊው ዓለም እና የኢትዮጵያ ሚድያዎች በተለይ በእግር ኳሱ ዙሪያ ሞያችን ነው ላላችሁት የኢትዮጵያን ሕዝብ ትርጉም ያለው የመረጃ በመከልከል ገደላችሁን በዚህም አፈርኩናችሁ በኩሙ ከሞተው እግር ኳስ ቀጥሎ፡፡ ደግሞ እኮ አያፍሩም ሕዝብን ለማሳሳት ከጥፈቱ በኃላ እገሌ ጋር ደውልኩ ምንናም ይሉናል በየማኅበረስብ ድህረ ገጾቹ፡፡ ጅብ ካለፈ ውሻ ጮኅ እንደሚባለው እተም ህይዎት የሆነ ትርጉም ያለው የመረጃ በሳቂ ውስጤ ግን አሮ፡፡
ባጠቃላይ ይህ የሚያመለክተው የመረጃ ምንጫቹ ምን እንደሆነ ነው የሚያሳየው፡፡ በሆነ አጋጣሚ ወይም በመተዋወቅ ያገኛችሁትን የመረጃ-መረብ ላይ ሚትለፈልፉ መሆናችሁን በደንብ ያሳብቅባችዋል፡፡ እንደ “ጋዜጤኛ” ትልቁን የዓለም እግር ኳስ ማኅበርን ረሳችሁት ውይም አታዩትም፡፡ አንድ ሐኪም በስህተት አንድን ስው ብገድል አንድ ሰው ውይም አንድን ቤተሰብ ነው የሚጎዳው፤ ለእንደእናንተ ሀገርን ላሳፈረው ለደገለው/ስሜቱን/ ምንድን ነው ፍርዱ? መለፍለፍ ጧት ተነስቶ እረ ማፈሪያ ናችው፡፡ ደግሞ እራሳችሁን ተጠያቂ ላለማድረግ ጥፋቱን ወደ ላላ በደሞተው ትገፋላችሁ፡፡ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴረሽን የኢትዮጵያን ህዝብን በሽተኛ አደረገው እናንተ “የሚድያ አካላት በተለይ በእግር ኳሱ ዙሪያ እንሰራለን የምትሉ ” ሰዎች ደግሞ የኢትዮጵያን ህዝብን ገደላችሁት!
ሌላውን ስህተታችሁን ልንገራችው እናንተ እኮ ዘረኞች ናችሁ፡፡ ዘረኝነት ለእኔ ያንድን ሰው/ማኅበረሰብ/ ሀገርን ባለው ባህሉ ፣ አነጋገሩ ፣ አመጋገቡ፣ቋንቋው ወዘተ የሚደረግበት ጫና ነው እንጂ በቆዳ ቀለም ብቻ አይደለም ዘረኝነት፡፡ ትናንት እኮ (ሰኔ 09 2005 ዓ.ም) ጨዋዎቹን የደቡብ አፍርካ ተጫዋቾችን ስም ላ ስታላግጡ ነበረ እኮ፤ እናንተ ያላችሁትን ቃላት እኔ መድገም አለፍልግም፡፡ ደግማችሁ አዳምጡት፡፡ ይህ ነው አንግድህ የአንድን ሰው ማንነቱን አለማክበሩ ጥፋቱ ዘረኝነቱ፡፡
የሚለምናችሁ ሚድያውን በግላጭ ስላገኛችሁት በህዝብ ላይ አታላግጡብን በሞያ እና በሥርዓት ተጠቀሙበት ሀገርንም ለሚገነባ ቁምነገር አውሉት ይኼ ነው የሚድያ እና የእውነተኛ ጋዜጤኝነት ሞያ፡፡ በመጨረሻ ከየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴረሽን ቀጥሎ እናንተም ለተፈጠረው ስህተት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂዎች ናቸው ስለዚህ ውዲያና ወድ ከመትዘባርቁ እና ደግማም ሌላ ስህተት ከሚትሰሩ የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ ሊትጠይቁት ይገባል እንድሁም የተከበሩና ጨዋውን የደቡብ አፍርካን ተጫዋቾችንም እንድሁ፡፡
ሁሌም መልካም ዕድል ለብሔራዊ ቡድናችን!!!!!!!
አመሠግናለው!
Advertisements

Posted on June 17, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: