ይድረስ ለአለምነህ ዋሴ፣ የአሜሪካ « ሰይጣን» በአገራችን?

ከኢየሩሳሌም አርአያ  ዛሬ ጠዋት ከመኖሪያዬ ወጥቼ ጥቂት እንደተጓዝኩ ሁለት አሜሪካዊያን ወጣቶች ከፊት ለፊቴ ሲመጡ ተመለከትኩ። እጅ ለእጅ ተያይዘዋል…በጥንቃቄ ምስላቸውን ለማስቀረት ሞከርኩ።… ( ወንድ ከወንድ- ሴት ከሴት፣ እጅ – ለእጅ መያያዝና መተቃቀፍ ግብረ-ሰዶማዊነትን ያመለክታል በአሜሪካ)… ታዲያ ምንድነው?.. ትለኝ ይሆናል፤… ይህ «ሰይጣናዊ» የነአሜሪካ «ቁሻሻ» በአገራችን መስፋፋቱ አሳስቦኝ ነው። የ11 እና 10 አመት ታዳጊ ሕፃናት ቦሌ አካባቢ በሚገኝ ት/ቤት ዳይሬክተሩን ጨምሮ 6 አስተማሪዎች እየተፈራረቁ «ሰይጣናዊ» ድርጊት ሲፈፅሙ እንደከረሙ መስማት አያስጨንቅም?… ለትምህርት የላከው ልጅህ ያውም በአስተማሪዎች እንዲህ አይነቱ ርካሽ ተግባር ሲፈፀምበት ምን ይሰማኻል?… «14ሺህ ግብረሰዶማዊያን በኢትዮጲያ አሉ» ተብሎ በአንድ ወቅት የተነገረውን ስትሰማ ምን አልክ?…ምነው ቤቲ ላይ በረታህ?… እርግጥ ነው ቤቲ የሰራችው ከአገራችን ባህል ጋር የሚጣረስ ነው!! ይህ አያከራክርም። ግን ቤቲ አረብ አገር እንደሚሰቃዩት እህቶቻችን እጣ ቢገጥማት… ይህን ያክል ትጮህላት ነበር?… በቅርቡ አረብ አገር ቁልቁል ተዘቅዝቃ ደም እየተፋች ስትገረፍ የነበረችው (ጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ ለጥፎት ነበር) እህታችን ሰቆቃ የሚሳየውን ቪዲዮ አይተኸዋል?… እንኳን ልታየው ከቁም ነገር ከተኸዋል?… ከ10 አመት በፊት ሟቹ ጠ/ሚ/ር በአዲስ አበባ ያለውን ሁኔታ ሲገልፁ «ሶስት መቶ ሺህ ሴተኛ አዳሪዎች በከተማዋ አሉ» ብለው ነበር። ማን የፈጠረው ችግር ነው?… ቤቲ የዚሁ አካል አይደለችም?… ሌሎቹ አደባባይ ስላልወጡ ነው?… ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ፥ የምታገለግለው ስርአት ይህን ሁሉ ችግር እንደፈጠረ ጠፍቶህ አይደለም። በስደት ስለሚያልቁትና ስለሚሰቃዩት እህትና ወንድሞቻችን አንድም ቀን ትንፍሽ ሳትል… ቤቲ ላይ ዘመትክባት። ሃቁ ግን የኢኮኖሚ ድቀት የፈጠረው ነው!!… ስለ «ሰይጣናዊው» አደገኛ የባህል ወረርሽኝ ትንፍሽ አላልክም። ለምን?… ወገኖቼ የቱ ያስጨንቃል?…

Advertisements

Posted on June 18, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: