በሁለት ወንድ ሕፃናት ላይ ግብረሰዶም በመፈጸም ወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ ምስክሮች ሳይሰሙ ቀሩ

በሁለት ወንድ ሕፃናት ላይ ግብረሰዶም በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረው በማረሚያ ቤት በሚገኙት የካራክተር ሆልማርክ አካዳሚ መምህራን ላይ፣ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሰኔ 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው ይሰማሉ ቢባልም ሳይሰሙ ቀርተዋል፡….

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 7ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ይሰማሉ ተብለው የነበሩት የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ምስክሮች መቅረብ ያልቻሉት፣ ምስክሮችን እንዲያቀርብ ትዕዛዝ የተላለፈለት የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ትዕዛዙ ዘግይቶ ሰኔ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. ስለደረሰው መሆኑን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ተጠርጣሪዎች በማረሚያ ቤት አንድ ላይ እንዲሆኑ እንዲታዘዝላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ በሚመለከት፣ ከማረሚያ ቤቱ ማብራሪያ ለፍርድ ቤቱ መላኩንና ማረሚያ ቤቱ ታራሚዎችን የሚይዘው በሚመቸው አኳኋን መሆኑን በመጥቀስ፣ ተጠርጣሪዎቹን በሦስት ቀጣናዎች ከፋፍሎ መያዙን አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል የተጠረጠሩበት ወንጀል እውነት መሆኑ ከተረጋገጠ ወደ ሌሎች እንዳይዛመት ለመጠንቀቅ መሆኑን መግለጹን ፍርድ ቤቱ ለችሎቱ ታዳሚዎችና ተጠርጣሪዎች አስታውቋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በዕለቱ ስለነበረው ሁኔታ አስተያየቱን ተጠይቆ፣ የምስክሮች መጥሪያ ለፖሊስ ኮሚሽኑ የደረሰው ሰኔ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. መሆኑን፣ ይኼም የሆነበት ምክንያት ፍርድ ቤቱ ሰኔ 5 ቀን 2005 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሲሰጥ ለቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ በማለቱና ትዕዛዙ ለቦሌ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት ተላልፎ ጊዜ በመውሰዱ መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል፡፡ በመቀጠልም ምስክሮቹን በስልክም እንደሚያገኛቸውና በቀጣይ ቀጠሮ ሊያቀርባቸው እንደሚችል አስታውቋል፡፡

የተጠርጣሪዎች ጠበቆች ለፍርድ ቤቱ መጀመሪያውንም ደንበኞቻቸው ንፁህ መሆናቸውን ማመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡ ክሱ እውነት ስላልሆነ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን ማቅረብ አልቻለም ብለዋል፡፡

ምስክሮቹን በስልክ እንደሚያገኛቸው ዓቃቤ ሕግ ስለተናገረ፣ ሌላ ሥራቸውን ትተው ሙሉ ቀን እንደሚጠብቁ በመግለጽ፣ ምስክሮቹ በስልክ ተጠርተው በዕለቱ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

ክሱ ተዘግቶ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን ሲያገኝ ሊያንቀሳቅስ እንደሚችል ወይም ደንበኞቻቸው እየተጉላሉና እየተጐዱ በመሆናቸው የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅ ጠበቆቹ ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን መስማት ሲጀምር ደንበኞቻቸው ንፅህናቸው እንደሚረጋገጥም ጠበቆቹ አክለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ የምስክሮች መጥሪያ ሰኔ 7 ቀን 2005 ዓ.ም. ወጪ መደረጉን፣ ነገር ግን ከዚያን ቀን ጀምሮ መድረስ አለመድረሱን ማረጋገጥ የዓቃቤ ሕግ ኃላፊነት እንደነበር በመግለጽ፣ ለፍትሕ አሰጣጥ ሲባል ፍርድ ቤቱ አንድ የመጨረሻ ቀጠሮ እንደሚሰጥ አስታውቆ ለሰኔ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ጠበቆች ለደንበኞቻቸው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በሚመለከት ፍርድ ቤቱ ብይን እንደሰጠበት በማስታወስ፣ በብይኑ ቅር የተሰኘ ይግባኝ ማለት እንደሚችል ገልጾ ችሎቱ ተጠናቋል፡፡

ethiopian reporter

Advertisements

Posted on June 23, 2013, in ETHIOPIA AMHARIC and tagged , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: